Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊምክትል ከንቲባው የእሳት አደጋን በተጠናከረ ሁኔታ ለመከላከል ሔሊኮፕተር በቅርቡ እንገዛለን አሉ

ምክትል ከንቲባው የእሳት አደጋን በተጠናከረ ሁኔታ ለመከላከል ሔሊኮፕተር በቅርቡ እንገዛለን አሉ

ቀን:

ለኮሚሽኑ በ171 ሚሊዮን ብር 26 ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ተገዙለት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዙሪያ በብዛት የሚገኙት የባህር ዛፍና የፅድ ዛፎች በቀላሉ የሚቀጣጠሉ ከመሆናቸውም በተጨማሪ በከተማው ውስጥ እየተገነቡ ያሉ ሕንፃዎች ሰማይ ጠቀስ በመሆናቸው፣ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ቢከሰት ለማጥፋት ወይም ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ስለሚሆን አደጋውን በተጠናከረ አቅም ለመከላከል በቅርቡ ሔሊኮፕተር እንደሚገዛ ምክትል ከንቲባው አስታወቀ፡፡  

ምክትል ከንቲባው ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ይኼን የተናገሩት እሑድ ግንቦት 18 ቀን 2011 ዓ.ም. በዓለም ላይ በአሁኑ ጊዜ በአገልግሎት ላይ የሚገኙና ዘመናዊ አሜሪካ ሠራሽ ናቸው የተባሉ 26 የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎችን ቁልፍ፣ ለእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ባስረከቡበት ወቅት ነው፡፡

- Advertisement -

አስተዳደሩ በመደበው 171 ሚሊዮን ብር ወጪ አሥር ፋየር ትራኮች፣ አሥር ብረሽ ትራኮች (ሙሉ ትጥቅ ያላቸው ተሽከርካሪዎች) እና ስድስት ኮማንድ ካሮች (የተቋሙ ኃላፊዎች አደጋ ወደ ደረሰበት ሥፍራ የሚሄዱበት) በአጠቃላይ 26 የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎችን ቁልፍ የተረከቡት፣ ኮሚሽነሩ ኮማንደር አህመድ መሐመድ ናቸው፡፡ የከተማውን መስፋፋትና እየተሠሩ ያሉ ሕንፃዎች ርዝማኔን በመጠቆም፣ ሔሊኮፕተር እንደሚያስፈልጋቸው ምክትል ከንቲባውን በመጠየቃቸው ግዥው በቅርቡ እንደሚፈጸም ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡

የሰው ልጅ ከተሽከርካሪና ከሔሊኮፕተር በላይ መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባው፣ የአስተሳሰብ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ሔሊኮፕተር መግዛት ቀላል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

‹‹በመንግሥት በጀት የመግዛት አቅም አለን፣ ማዘዝም እንችላለን፤›› ካሉ በኋላ፣ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽንና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር በሚቀጥለው በጀት ዓመት መግዛት እንደሚቻል በልበ ሙሉነት ተናግረዋል፡፡ በቅርቡ አሜሪካ ለጉብኝት ሄደው በዚሁ ላይ ከከንቲባዎች ጋር መነጋገራቸውንና የእሳት አደጋ ማሽነሪዎች ሊሰጧቸው ቃል መግባታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ተቋሙ እንደ አዲስ በአዋጅ ሲቋቋም በደንብ መጠናከር እንዳለበት ታሳቢ ተደርጎ መሆኑን ተናግረው ከተማዋ ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት፣ የአፍሪካ መዲና፣ በርካታ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች የሚካሄዱባትና ቱሪስቶችን የሚስቡ ትልልቅ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ከመሆኑ አንፃር፣ ልዩ ጥበቃ ማድረግ ተገቢና አስፈላጊ በመሆኑ የኮሚሽነሩ ጥያቄ ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

‹‹በራስ በጀት መግዛት ቢያቅተን እንለምናለን፣ ልመና ደግሞ እየተሳካልን ስለሆነ ችግር የለም፤›› ያሉት ምክትል ከንቲባው፣ ጭንቀታቸው ለአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ሳይሆን፣ በዙሪያዋ ላሉ ከተሞች ጭምር በመሆኑ የጥያቄውን አስፈላጊነት አስምረውበታል፡፡ ከወር በኋላ ክረምት እንደሚገባ ጠቁመው ያለፈው ዓመት ክረምት እንዴት እንዳለፈ በማስታወስ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር የጋራ ግብረ ኃይል በማቋቋም የጎርፍ ማስወገጃ ቦታዎችን እያስተካከሉ፣ ቱቦዎችን እየቀበሩና እያፀዱ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽኑን ደግሞ በሁሉም ነገር ማጠናከርና ዝግጁ ሆኖ እንዲገኝ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ኮሚሽኑ ለከተማው ነዋሪዎች አቅምና ተስፋ በመሆኑ በየክፍላተ ከተሞች ቶሎ ምላሽ መስጠት በሚችልበት ሁኔታ መደራጀት እንዳለበትና አደጋ፣ እሳትና ጎርፍ ምን እንደሆነ የሚያውቅ ባለሙያም አስፈላጊ መሆኑን ምክትል ከንቲባው አስረድተዋል፡፡ ለራሳቸው ነፍስ ሳይሳሱ ለሌላው ሕይወት የሚደርሱ ሠራተኞች ስላሉ፣ አስተዳደሩ በነዋሪዎች ስም ምሥጋናውን እንደሚያቀርብላቸውም ተናግረዋል፡፡ የሚፈልገውን ሎጂስቲክስ በሙሉ ማሟላት ከከተማው አስተዳደር አቅም በላይ እንዳልሆነም ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...