Friday, June 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ በጠየቀው ዋስትና ላይ ንግድ...

የቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ በጠየቀው ዋስትና ላይ ንግድ ባንክ ተጨማሪ መረጃ ጠየቀ

ቀን:

የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ የወጣባቸው ከ18 ሺሕ በላይ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ለደረሳቸው እንዳይተላለፉ በመታገዳቸው ምክንያት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ በጠየቀው የዋስትና ጥያቄ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጨማሪ ማብራሪያ ጠየቀ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሚያዝያ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት በጻፈው ደብዳቤ እንዳሳወቀው፣ ኢንተርፕራይዙ እ.ኤ.አ. ማርች 31 ቀን 2019 ድረስ ያለበት ዋናው ብድር ከ19.5 ቢሊዮን ብር በላይ ነው፡፡ በዚህ ገንዘብ ላይ በየቀኑ 9.5 በመቶ ወለድ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚከፍልና ይኼንንም ለተቋሙ ማሳወቁን፣ በደንበኞች ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘገየ ኤልያስ ተፈርሞ ለፍርድ ቤት የተላከው ደብዳቤ ይገልጻል፡፡

ፍርድ ቤቱ በየቀኑ ይከፈላል የተባለው ወለድ ዕጣ ከወጣባቸው ወይም ወደፊት ዕጣ ከሚወጣባቸው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በቀጥታና ሙሉ በሙሉ የሚገናኝ መሆን አለመሆኑን መጠየቁን ጠቁሞ፣ የኢንተርፕራይዙ የክፍያ ምንጭ ቤቶቹ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

በመሆኑም ቤቶቹን በማስተላለፍ የሚገኘው ገቢ በቀጥታ ለኢንተርፕራይዙ መሆኑን ጠቁሞ፣ ነገር ግን በአንድ ዓመት ውስጥ ሊደርስ የሚችለውን የወለድ መጠን ለማሥላት ተጨማሪ መረጃ (የገንዘቡ መጠን) የሚያስፈልገው መሆኑን አስታውቋል፡፡

ፍርድ ቤቱም ንግድ ባንክ በሰጠው ምላሽ ላይ አስተያየት ለመጠባበቅ ለግንቦት 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...