Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለምስክርነት የተጠሩትን አምባሳደር ለማስመጣት የጉዞ ወጪያቸውን አልሸፍንም አለ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለምስክርነት የተጠሩትን አምባሳደር ለማስመጣት የጉዞ ወጪያቸውን አልሸፍንም አለ

ቀን:

በከባድ የሙስና ወንጀል ለተከሰሱ ግለሰብ በመከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩትን በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ሽፈራው ጃርሶን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ለማድረግ፣ የትራንስፖርት ወጪ ለመሸፈን ፈቃደኛ እንዳልሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፍርድ ቤት ተናገረ፡፡

ሚኒስቴሩ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት እንዳስረዳው፣ በመከላከያ ምስክርነት መጠራታቸውን የሚገልጸውን መጥሪያ እንዲደርሳቸው ልኳል፡፡ ነገር ግን አምባሳደሩ በችሎት ተገኝተው የመከላከያ ምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ለማድረግ፣ የትራንስፖርት ወጪያቸውን መሸፈን እንደማይችል ገልጿል፡፡

አምባሳደር ሽፈራው በመከላከያ ምስክርነት የቆጠራቸው ክሳቸው በተቋረጠበት ዕለት ሕይወታቸው ማለፉ የተነገረው፣ የስኳር ኮርፖሬሽን የአገዳ ተክልና የፋብሪካ ግንባታ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በነበሩት ተስፋዬ አበበ (ኢንጂነር) የክስ መዝገብ የተካተቱት ወ/ሮ ሳሌም ከበደ ናቸው፡፡

- Advertisement -

ክሱ የወንጀል በመሆኑ ምስክርነቱ መሰጠት እንዳለበትና የመከላከያ ምስክሩ ሳይቀርቡ ቢቀሩ፣ በተከሳሿ ላይ የሚደርሰው ከባድ የመብት ጥሰት መሆኑን የተከሳሿ ጠበቃ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡ ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ እንዲረዳም የመከላከያ ምስክሩ ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ፍርድ ቤቱ በድጋሚ ትዕዛዝ እንዲሰጥ አሳስበው፣ ምስክሩ ከቀረቡ በኋላ የሚቀርበውን ወጪ ዝርዝር ፍርድ ቤቱ ተመልክቶ ትዕዛዝ ከሚሰጥበት በስተቀር በትራንስፖርት ወጪ ተሳቦ መቅረት እንደሌለባቸው የወ/ሮ ሳሌም ጠበቃ ተከራክረዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም በሰጠው ትዕዛዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአቶ ሽፈራው መጥሪያ መላኩን ቢገልጽም ስለመድረሱ ያቀረበው ማረጋገጫ የለም፡፡ መጥሪያው እንዴት እንደተላከ ግልጽ ባለመሆኑና የትራንስፖርትም ወጪ እንደማይከፍል በማሳወቁ፣ መጥሪያውን በድጋሚ ልኮ መድረስ አለመድረሱን በማጣራት ግንቦት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲቀርብ ድጋሚ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ወ/ሮ ሳሌም ከበደ የተከሰሱት ከ12.1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሊገነባ ተጀምሮ ከነበረው፣ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የኦሞ ኩራዝ አምስት ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ጋር በተያያዘ መሆኑን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ የፋብሪካውን 85 በመቶ ወጪ የውጭ ፋይናንስ በማፈላለግና የብድር ስምምነት ውል በማድረግ ለመገንባት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት አውጥቶት የነበረውን ዓለም አቀፍ ጨረታ ለመሳተፍ ፍላጎት ካሳዩ አምስት የቻይና ኩባያዎች ውስጥ ሁለት ኩባንያዎች ቻይና ላይት ኢንዱስትሪያል ኮርፖሬሽንና ቻይና ናሽናል ሄቪ ማሽነሪ ኮርፖሬሽን ፋይናንሱን አፈላልገው፣ ፋብሪካውን ለመገንባት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመው ነበር፡፡

ነገር ግን ወ/ሮ ሳሌምና ሌሎች በሕገወጥ ድለላ ሥራ ላይ የተሠማሩ ናቸው በተባሉና በክሱ በተካተቱ ግለሰቦች አማካይነት በዓለም አቀፉ ጨረታ ያልተሳተፈ፣ ‹‹ጃንዚ ዳንግሊያን ኢንተርናሽናል ኢንጂነሪንግ ኩባንያ – JJIEC የተባለ የቻይና ኩባንያ በጨረታው እንደተሳተፈና እንዳሸነፈ በማስመሰል፣ ከ12.1 ቢሊዮን ብር በላይ ይፈጃል የተባለውን ኦሞ ኩራዝ አምስት ስኳር ፋብሪካ ለመገንባት የመግባቢያ ውል በወቅቱ ከነበሩ የኮርፖሬሸኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓባይ ፀሐዬ ጋር እንዲፈራረሙ ማድረጋቸው በክሱ በዝርዝር ተገልጾ ይገኛል፡፡

ውሉ እንዲፈጸም የተደረገው የኮርፖሬሽኑንና በወቅቱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር (ገንዘብ ሚኒስቴር) ኃላፊዎችን ያውቃሉ በተባሉትና ሕገወጥ ደላሎች ብሎ ዓቃቤ ሕግ በክሱ የጠቀሳቸው ወ/ሮ ሳሌም ከበደን ጨምሮ፣ በክሱ የተካተቱ ግለሰቦች አማካይነት መሆኑንም ክሱ ያብራራል፡፡ ግለሰቦቹ የተለያየ መጠን ያለውና በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በኮሚሽን ሲያገኙ፣ መንግሥት ደግሞ በግዥ መመርያው መሠረት የተመረጡት ኩባንያዎች ፋይናንስ የማፈላለጉን ሥራ ሠርተው ቢሆን ኖሮ በተሻለና በቀነሰ ብድር ውሉን መፈጸም ይችል የነበረ ቢሆንም፣ ያ እንዳሆን በማድረጋቸው ለጉዳት መዳረጋቸውንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሮ አቅርቧል፡፡

ዓቃቤ ሕግ የሰዎችና የሰነድ ምስከሮችን አቅርቦ ካሰማና ካስረዳ በኋላ የክርክር ሒደቱን የሚመራው ፍርድ ቤት ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ማስመስከሩን ገልጾ፣ ወ/ሮ ሳምና ሌሎች ክሳቸው ያልተቋረጠላቸው ተከሳሾ እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...