Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናከስንዴ ግዥ ጋር በተያያዘ 668.2 ሚሊዮን ብር ጉዳት አድርሰዋል በተባሉ የመንግሥት ኃላፊዎች...

ከስንዴ ግዥ ጋር በተያያዘ 668.2 ሚሊዮን ብር ጉዳት አድርሰዋል በተባሉ የመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ክስ ተመሠረተ

ቀን:

ለገበያ ማረጋጊያ ከ2010 ዓ.ም. እስከ 2011 ዓ.ም. (ወሩና ቀኑ አልተጠቀሰም) በተፈጸመ የ400,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ ጋር በተያያዘ፣ በመንግሥት ላይ ከ688.1 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ አሥር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ኃላፊዎች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዋና ዓቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ቀደም ብሎ ባስታወቁት መሠረት ተከሳሾቹ በቁጥጥር ሥር ከመዋላቸው በፊት የምርመራው ሥራ በመጠናቀቁ፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በተከሳሾቹ ላይ ከአንድ ጊዜ በላይ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሳይጠይቅ የምርመራ መዝገቡን ለዓቃቤ በማስረከቡ፣ ዓቃቤ ሕግም ባልተለመደ ሁኔታ ክሱን በፍጥነት መሥርቷል፡፡ በመሆኑም የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይገዙ ዳባ፣ የግዥ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብርሃኑ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሸን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መንግሥቱ ከበደ፣ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የግዥ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን በትረ፣ የግዥ አፅዳቂ ኮሚቴዎች አቶ ሰለሞን አይኒማር፣ አቶ ዮሴፍ ራፊሶ፣ አቶ ተክለ ብርሃን ገብረ መስቀል፣ አቶ ትሩፋት ነጋሽ፣ አቶ ዘሪሁን ስለሺና አቶ ጀንሴ ገደፋ ላይ ዓቃቤ ሕግ ክሱን አቅርቧል፡፡

ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንዳብራራው ለገበያ ማረጋጊያ 400,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ለመግዛት ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቷል፡፡ ጨረታውን ሻከል ኤንድ ካምፓኒ የተባለው የፓኪስታን ድርጅት በ96.4 ሚሊዮን ዶላር አሸንፎ፣ ታኅሳስ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ኩባንያው በ15 ቀናት ውስጥ ማስያዝ ያለበትን የውል ማስከበሪያ ለማክበር ጥረት በማድረግ ላይ እያለ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፓኪስታን ባንኮች ጋር ግንኙነት እንደሌለው ገልጾ፣ የሚመጣውን የባንክ ዋስትና እንደማይቀበል ማስታወቁን አክሏል፡፡ ኩባንያው ለውል ማስከበሪያው ከሌላ ሦስተኛ አገር ባንክ ዋስትና ለማምጣት ወይም በውላቸው አንቀጽ 47(3) ላይ ከተሰጡ ሦስት አማራጮች አንዱን እስከሚያቀርብ ድረስ፣ የውል ማስከበሪያ ቀኑ እንዳያልፍ ክፍያ ሳይፈጸምለት ስንዴውን በነፃ እንዲያስገባ ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡

- Advertisement -

ችግሩ የተፈጠረው ጨረታውን ያሸነፈው ኩባንያ እንዳልሆነና በውሉ መሠረትም አማራጭ የቼክ ዋስትና ሰነድ አቅርቦ እያለ፣ ተከሳሾቹ በመንግሥት ግዥ መመርያ አንቀጽ 29(4) እና በውሉ አንቀጽ 17.1(a)፣ 17.3 እና 20(1) መሠረት ተጨማሪ ቀናት መስጠት እየቻሉ ወይም በግዥ መመርያው አንቀጽ 29.3 (ሐ) መሠረት ኩባንያው የውል ግዴታውን መወጣት እንዲችል ሕጋዊ የሆነ ዕገዛ በማድረግ የውል አፈጻጸሙ የተሳካ እንዲሆን የማድረግ ኃላፊነት ቢኖርባቸውም፣ በ15 ቀናት ውስጥ ‹‹የውል ማስከበሪያ አላቀረበም›› በማለት ውሉ እንዲቋረጥ ማድረጋቸውን አስረድቷል፡፡

የግዥ አፅዳቂ ኮሚቴ የነበሩትና ከላይ በስም የተጠቀሱት ተከሳሾች ደግሞ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በመጠባበቂያ ክምችት ያለው ስንዴ አነስተኛ መሆኑንና እጥረት በመከሰቱ፣ በአስቸኳይ የግዥ ሒደት እንዲከናወን ባሳሰበው መሠረት ጥር 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሁለተኛ ጊዜ ከወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ ጋር በተያያዘ የተከሰሱ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ ተከሳሾቹ ፕሮሚሲንግ ኢንተርናሽናል የተባለው ድርጅት ጋር በጥቅም በመመሳጠርና 400,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥን እንዲያሸንፍ በማድረግ 525,422,741 ብር በመንግሥት ላይ ጉዳት እንዲደርስ፣ በኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ተጓጉዞ ቢሆን ኖሮ ማግኘት የሚችለውን 129,515,705 ብር በማሳጣት በአጠቃላይ 688,206,629 ብር ጉዳት በማድረሳቸው፣ በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የስንዴ ዱቄትና የዳቦ እጥረት እንዲከሰት በማድረግ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ መሆን በፈጸሙት የመንግሥትን ሥራ በማያመች አኳኋን መምራት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ በዓቃቤ ሕግ ቀርቦባቸዋል፡፡ ክሱ ተነቦላቸውና ዋስትና ተከልክለው የክስ መቃወሚያ ካላቸው ለመጠባበቅ ለግንቦት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እስከዚያው በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...