Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልየምሥራቅ ኦርቶዶክስ ፋሲካ

  የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ፋሲካ

  ቀን:

  የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በሚከተሉት የ‹‹ጁሊያን›› ካላንደር መሠረት የትንሣኤ በዓለም ከኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ጋር ሚያዝያ 20 ቀን 2011 ዓ.ም. እያከበሩ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምትገኝበት የኦሬንታል ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት የኤርትራ፣ ግብፅ (ኮፕቲክ)፣ ሶርያ፣ አርመን፣ ህንድ ኦርቶዶክሶችም እንደየ ሥርዓታቸው እያከበሩ ነው፡፡ ሳምንቱንም በልዩ ልዩ መንፈሳዊ መሰናዶዎች ያከብሩታል፡፡

  “ፋሲካ” የሚባለው ትንሣኤ፣ በፀደይ ወቅት ከምትታየው ሙሉ ጨረቃ በኋላ የሚከበር ነው፡፡ ትንሣኤ እግዚእ ኢየሱስ ተሰቅሎና ሙቶ፣ ከሙታንም ተለይቶ የተነሳበትን ዕለት ያመለክታል፡፡ የተሰቀለውና የሞተውም በአይሁድ ፋሲካ (ፍሥሕ) ጊዜ ሲሆን፣ የተነሳውም ከአይሁድ ፍሥሕ በኋላ በመጀመሪያው እሑድ ነው፡፡ የአይሁድ ፋሲካ ሁልጊዜ የሚወለው በፀደይ ወቅት የመጀመርያ ሙሉ ጨረቃ በሚታይበት ዕለት ነው፡፡ የዚህም ማስረጃው በኦሪት እንደሚከተለው ተጽፏል፡- “በመጀመርያው ወር ሲመሽ በአሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው፡፡”

  በሰሙነ ሕማማት፣ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ቤተ ክርስቲያን በየዕለቱ በመገኘት ሕማማቱን ያስባሉ፣ ሥርዓተ አምልኮን ይፈጽማሉ፡፡ ማኅበረ ምዕመኑ ከሚሳተፍባቸው ዕለታት መካከል ሆሣዕና (የዘንባባ እሑድ)፣ ምክረ አይሁድ የተፈጸመበት ረቡዕ፣ ዓርብ ስቅለትና ቀዳም ሥዑር ናቸው፡፡ በቅዳሜ እኩለ ሌሊት በሚኖረው ቅዳሴ ለመሳተፍ ምዕመናን ሻማና ጧፍ ይዘው ይገኛሉ፡፡

   የግሪክ ኦርቶዶክስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ካህን አባ ባስልዮስ ሂክማን ለሁቲቪ እንደገለጹት፣ ‹‹እኩለ ሌሊት ሲሆን የቤተ መቅደሱ በር ይከፈታል፣ ይህም የመቃብሩ መከፈትን ይወክላል፡፡ ካህኑ ሻማውን አብርቶ ይዞ ይወጣል፡፡ ‹ኑ ከሙታን ተለይቶ የተነሳው የዘላለማዊ ብርሃን ክርስቶስን ብርሃን ተቀበሉ› ይላል፡፡››

  በሌሎች የምሥራቅ ትውፊቶች እንቁላልን ቀይ ቀለም የሚቀቡት የክርስቶስን ደም እንዲወክል ነው፡፡ በሌላ በኩልም የእንቁላሉን ራስጌና ግርጌ እየያዙ ትንሣኤውን ያውጃሉ፡፡ በራስጌው የያዘው ‹‹ክርስቶስ ተነሥቷል›› ሲል በግርጌ የያዘው ‹‹በእውነት ተነሥቷል፤›› ይላል፡፡

  ዓርብ ምሽት ሚያዝያ 11 ቀን 2011 የተጀመረው የአይሁድ ፋሲካ፣ ሚያዝያ 19 ምሽት ያበቃ ሲሆን፣ በማግሥቱ ሚያዝያ 20 የትንሣኤ በዓል ውሏል፡፡ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ የትንሣኤ በዓልን የሩሲያ ኦርቶዶክስ፣ የግሪክ ኦርቶዶክስ፣ የሰርቢያ ኦርቶዶክስና ሌሎችም እያከበሩት ነው፡፡

  በዓለም ዙሪያ የኦርቶዶክስን ፋሲካ የሚያከብሩ ከሩብ ሚሊዮን በላይ ምዕመናን አሉ፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...