Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናበስብሰባ አዳራሾችና በተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረ የሽብር ጥቃት በቁጥጥር ሥር መዋሉን ጠቅላይ...

በስብሰባ አዳራሾችና በተቋማት ላይ ሊደርስ የነበረ የሽብር ጥቃት በቁጥጥር ሥር መዋሉን ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ

ቀን:

በዓለም ላይ በሽብርተኝነት ከተፈረጁ አሸባሪ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በስብሰባ አዳራሾችና ተቋማት ላይ ሊፈጸም የነበረ የሽብር ጥቃት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡

የሽብር ጥቃቱ ሊፈጸም የነበረው ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ መሆኑን፣ ድርጊቱም ከሽፎ የአሸባሪ ቡድኑ በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መሆኑን፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ አስታውቀዋል፡፡

አቶ ብርሃኑ እንደገለጹት፣ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የሽብር ጥቃት ሊፈጸም ነበር፡፡ የሽብር ቡድኑ ከውጭ አሸባሪ ድርጅቶች ጋር በመሆን የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈጸም ቦታ መምረጡን፣ የተመረጡ ቦታዎችን ፎቶ በማንሳትና የሽብር ተግባሩ የሚፈጸምበትን ሥልት በመቀየስ ላይ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

ቡድኑ የተለያዩ መታወቂያዎችን፣ የውጭ አገር ፖስፖርቶችንና የተለያዩ መጠቀሚያ መሣሪያዎችን በማዘጋጀት ጥቃቱን ለመፈጸም በዝግጅት ላይ እያለ የአገሪቱ የደኅንነት ተቋም ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር እንዳዋሉት ገልጸዋል፡፡

ወንጀሉ ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው በመሆኑ ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያስፈልገው የተናገሩት ዋና ዓቃቤ ሕጉ፣ ምርመራው ሲጠናቀቅ በግልጽ ይፋ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡

የሽብር ወንጀሉ ቢፈጸም ኖሮ በአገሪቱ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት አሁን መገመት እንደማይቻል ተናግረው፣ ሽብር የሚፈጸምባቸው ቦታዎች በፎቶ የተደገፉ፣ የተለያዩ የስብሰባ አዳራሾችና የተለያዩ ማዕከሎች ከመሆናቸው አንፃር ጉዳቱ ከፍተኛ ይሆን እንደነበር ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...