Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናዕጣ በወጣባቸው የ40/60 ቤቶች ውል እንዳይፈጸምና አዲስ ዕጣ እንዳይወጣ ዕግድ ተጣለ

ዕጣ በወጣባቸው የ40/60 ቤቶች ውል እንዳይፈጸምና አዲስ ዕጣ እንዳይወጣ ዕግድ ተጣለ

ቀን:

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ የወጣባቸውን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ዕጣ የወጣላቸው ዕድለኞች ክስ ከተመሠረተባቸው መንግሥታዊ ተቋማት ጋር ውል እንዳይፈጽሙ ዕግድ ጣለ፡፡ በቀጣይም ዕጣ የሚወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ካሉና ዕጣ ለማውጣት ፕሮግራም ከተያዘ፣ ተለዋጭ ትዕዛዝ እስኪሰጥ ድረስ ታግዶ እንዲቆይም ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን የሰጠው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ቅድሚያ በዕጣ ለማግኘት፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ውል በመፈጸም መቶ በመቶ ክፍያ የፈጸሙ 98 ግለሰቦች 597,529 ብር የዳኝነት ከፍለው ባቀረቡት ክስ ምክንያት ነው፡፡

ግለሰቦቹ ክስ የመሠረቱት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ላይ ነው፡፡

- Advertisement -

ከሳሾች በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 154 እና 205 ድንጋጌ መሠረት በቃለ መሃላ አረጋግጠው ባቀረቡት ክስ እንደገለጹት፣ ከተከሳሾች በውልና በመመርያ ያገኙትን መብት በመጣስ እነሱ ቅድሚያ በከፈሉት ገንዘብ የተሠሩትን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከውልና መመርያ ውጪ አነስተኛ ክፍያ ለከፈሉ ግለሰቦች ዕጣ እንዲወጡ አድርገዋል፡፡ ድርጊቱን በመቃወም ክስ አቅርበው በመታየት ላይ እያለ ቤቶቹን ዕጣ ለደረሳቸው ግለሰቦች ሊተላለፉ መሆናቸውን ስለደረሱበት፣ ክርክር ተሰምቶ ውሳኔው እስከሚታወቅ ድረስ ፍርድ ቤቱ ዕግድ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ቤቶቹ ቢተላለፉ የማይተካ ጉዳት እንደሚደርስባቸውም አክለዋል፡፡ በመሆኑም የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ የወጣባቸው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በማንኛውም ሁኔታ ለዕድለኞች ሳይተላለፉ እንዲቆይ ጠይቀዋል፡፡ ዕጣ ያልወጣባቸውም ቤቶች ላይ የዕጣ ማውጣት ፕሮግራም እንዳይካሄድ ዕግድ እንዲሰጥላቸውም አመልክተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም የከሳሾችን አቤቱታ ተመልክቶ ዕድለኞች ቤቱን ሊረከቡ አይገባም የሚለውን የከሳሾችን አቤቱ እንዳልተቀበለው ገልጾ፣ ተከሳሾች መንግሥታዊ ተቋማት ከዕድለኞቹ ጋር ውል እንዳይዋዋሉና ቀጣይ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ እንዳይወጣ ዕግድ ጥሏል፡፡

ፍርድ ቤቱ መጋቢት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤት የከሳሾችን የክስ አቤቱታ ከሰማ በኋላ ቤቶቹ ለዕድለኞች አይተላለፉ የሚለውን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉን በመንገር፣ ስመ ሀብቱ (የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ) ሳይተላለፍ ታግዶ እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣም የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ በመከተል፣ ‹‹ዕጣ የወጣባቸው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለ ዕድለኞች እንዳይተላለፉ የቀረበው ዕግድ ጥያቄ ተቀባይነት አላገኘም፤›› በሚል ርዕስ ዜናውን የዘገበ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ በጽሑፍ በሰጠው ትዕዛዝ የተለየ ሐሳብ በማሥፈሩ ከላይ እንደቀረበው ተስተካክሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...