Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናበቻይና መንግሥት የታሰረችውን ኢትዮጵያዊት ጓደኛ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አዋላት

በቻይና መንግሥት የታሰረችውን ኢትዮጵያዊት ጓደኛ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አዋላት

ቀን:

የስቅላት ቅጣት የሚያስቀጣውን ኮኬን የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ ይዛ በመገኘቷ የቻይና መንግሥት የያዛት ናዝራዊት አበራ፣ ለመያዟ ምክንያት መሆኗ የተነገረላትን ጓደኛዋን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አዋላት፡፡ ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ ዕፅ ቻይና ውስጥ የተገኘበት ማንኛውም ሰው በስቅላት ይቀጣል፡፡

የናዝራዊት አብሮ አደግና የቅርብ ጓደኛዋ እንደሆነች የሚነገርላት ወ/ሪት ሥምረት ካህሳይ በቁጥጥር ሥር የዋለችው፣ ሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. በፌዴራል ፖሊስ መሆኑ ታውቋል፡፡ ሥምረት በቁጥጥር ሥር የዋለችው ሰለሞን ፀጋዬ ከሚባል ጓደኛዋ ጋር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ሥምረት ለአብሮ አደጓና ጓደኛዋ መታሰር ምክንያት የሆነችው፣ ከሦስት ወራት በፊት ናዝራዊት ወደ ቻይና ስትሄድ እዚያ ለምታውቃቸው ሰዎች ሻምፖ እንድትሰጥላት በሰጠቻት መያዣ ዕቃ ውስጥ፣ ኮኬን የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ በመክተት በመስጠቷ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡

- Advertisement -

ሥምረት ከጓደኛዋ ጋር አብረው ወደ ቻይና ለመሄድ እየተዘጋጁ ሳሉ የቤተሰብ አባል ሞቶባት መሄድ ባለመቻሏ ከብራዚል የመጣ ሻምፖ እንደሆነ ነግራት፣ ቻይና  ለምታውቋቸው ሰዎች እንድትሰጥላት በመስጠት እሷ ሳትሄድ መቅረቷም ተጠቁሟል፡፡ ናዝራዊት ቻይና ስትደርስ በተደረገ ፍተሻ ኮኬን የተሰኘውን አደንዛዥ ዕፅ ይዛ በመገኘቷ በቁጥጥር ሥር ውላ ክሷን እየተጠባበቀች ነው፡፡

 ድርጊቱን አውቃና ሆን ብላ የፈጸመችው ሳይሆን፣ ጓደኛዋ በፈጠረችው ስህተት መሆኑን ቤተሰቦቿና በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ መንገዶች ለቻይና መንግሥት ለማሳወቅ እየጣሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካይነት ጉዳዩን ለማጣራ ጥረት እያደረገ መሆኑን፣ ቻይና በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶችም እንድትጎበኝ እያደረገ መሆኑን መግለጹም ይታወሳል፡፡

ሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. የናዝራዊትን ጓደኛ የፌዴራል ፖሊስ ከጓደኛዋ አቶ ሰለሞን ፀጋዬ ጋር በቁጥጥር ሥር ሲያውላቸው፣ በአቶ ሰሎሞን ቤት ከብራዚል ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ወደ ቻይና ለመላክ የተዘጋጀ አደንዛዥ ዕፅ መገኘቱም ተገልጿል፡፡

በመሆኑም በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የተቋቋመ የምርመራ ቡድን ከብራዚል ተነስቶ በኢትዮጵያ ወደ ቻይና ከሚጓጓዘው አደንዛዥ ዕፅ ሽያጭና የሚገኘውን የገንዘብ ዝውውርን ጨምሮ፣ ሌሎች ወንጀሎችንም የማጣራት ሥራ መጀመሩ ተጠቁሟል፡፡ ናዝራዊት በቻይና መንግሥት በተያዘች ወቅት፣ እዚህ ደግሞ ፖሊስ ሳምራዊትን በቁጥጥር ሥር አውሎ በዋስ መልቀቁ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...