Tuesday, May 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናበዲሲፕሊን ጥፋት የታገዱት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የመሠረቱትን ክስ...

በዲሲፕሊን ጥፋት የታገዱት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የመሠረቱትን ክስ አሻሻሉ

ቀን:

በፌዴራል ዳኞች አስተዳደር የዲሲፕሊን ጥሰት ፈጽመዋል ተብለው ከዳኝነታቸው እንዲታገዱ የተላለፈባቸው የነበሩት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ አየለ ዱባ፣ የታገዱበትን የዲሲፕሊን ጥፋት በተመለከተ ሪፖርተር ጋዜጣ ባቀረበው ዘገባ ስማቸውን እንዳጠፋባቸው በመግለጽ የመሠረቱትን ክስ አሻሻሉ።

 የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የዲሲፕሊን ጥሰት ፈጽመዋል ያላቸውን የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ አየለ ዱባ ከዳኝኘት በማገድ፣ የሾማቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከዳኝነት እንዲያነሳቸው ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ፣ ሪፖርተር ጋዜጣ ሆነ ብሎ በማዛባት ጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ.ም. መዘገቡንና በዚህ ዘገባም ጋዜጣው ስማቸውን እንዳጠፋ በመግለጽ ጥር 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ክስ አቅርበዋል።

ዳኛው ለመሠረቱት ክስ ምክንያት የሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ በተባለው ቀን ‹‹ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ደረቅ ቼኮችን የፈረሙ ተጠርጣሪዎችን የለቀቁ ዳኛ እንዲሰናበቱ ተጠየቀ›› በሚል ርዕስ ያወጣው ዘገባ ሲሆን፣ ዘገባው የሚመለከታቸው ዳኛው አቶ አየለ ዱባ በመሠረቱት ክስ ጋዜጣው ባወጣው ዘገባ የደረቅ ቼኮቹ የገንዘብ መጠን በፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ዳኛው እንዲሰናበቱ ለፓርላማ ባቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ የሌለና እጅግ የተጋነነ መሆኑን በመጥቀስ ከሰዋል።

- Advertisement -

የዳኞች አስተደደር የዲስፕሊን ጥፋት ፈጽመዋል በማለት ባስተላለፈው ውሳኔ ላይ የተጠቀሰው የደረቅ ቼኮቹ የገንዘብ መጠን አምስት ሚሊዮን አራት መቶ አርባ ሁለት ሺሕ ብር ሆኖ ሳለ፣ ጋዜጣው ባወጣው ዘገባ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ በመግለጽ በጉባዔው የውሳኔ ሐሳብ ላይ የሌለና ከእውነት የራቀ መረጃ በማውጣት በጋዜጣው አንባቢ ማኅበረሰብና በሌሎች ላይ የተዛባና የተሳሳተ አስተያየት በመፍጠር የዳኛውን ስም የማጥፋት ተግባር ሪፖርተር ጋዜጣ፣ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅና የጋዜጣው ኤዲተር እንደፈጸሙባቸው ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት ክስ አመልክተዋል።

 በተጨማሪም የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ውሳኔን ለፓርላማ እንደቀረበ የውሳኔ ሐሳብ አድርጎ አዛብቶ በመዘገብ የዳኛውን ስም በማጥፋታቸው፣ ዘገባው እንዲታረምላቸውና ለደረሰባቸው የህሊና ጉዳት አንድ መቶ ሺሕ ብር ካሳ እንዲወሰንላቸው አመልክተዋል።

ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ሪፖርተር ጋዜጣ እንዲሁም ዋና አዘጋጅና የጋዜጣው ኤዲተር ተብለው የተጠቀሱት ግለሰቦች ለቀረበባቸው ክስ የጽሑፍ መልስ ከእነ ማስረጃው የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ለፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር እንዲያቀርቡ፣ እንዲሁም ለቃል ክርክር ሚያዚያ 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በአካል እንዲገኙ ጥሪ አቅርቧል።

በዚሁ መሠረት ተከሳሾች ለቀረበባቸው ክስ የጽሑፍ መልስ ለፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር አስገብተዋል።

ይሁን እንጂ ለቀረበው ክስ የተሰጠው የጽሑፍ ምላሽ በሕጉ አግባብ መሠረት የደረሳቸው ከሳሽ ለችሎት ክርክር የተሰጠው ቀጠሮ ከመድረሱ በፊት ክሳቸውን በመቀየር ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ያቀረቡትን ክስ፣ የሪፖርተር አሳታሚ በሆነው የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽንስ ሴንተር ላይ አድርገዋል። በተጨማሪም ዘገባውን አቅርበዋል ብለው በጠቀሷቸው ሁለት የጋዜጣው ባልደረቦች ላይ ያቀረቡትን ክስ በመቀየር፣ ክሳቸውን በጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ላይ በማድረግ አስተካክለው አቅርበዋል።

ዳኛው ፈጽመዋል በተባሉበት የዲሲፕሊን ጥሰት ምክንያት ከዳኝነት እንዲሰናበቱ ለፓርላማ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ የተመለከተው ፓርላማው፣ ጉዳዩን በዝርዝር እንዲመለከተው ለሕግ ፍትሕና ዴሞክራሲያዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶ የነበረ ሲሆን፣ ቋሚ ኮሚቴው የምርመራ ውጤቱን እስካሁን ለፓርላማው በይፋ መደበኛ ስብሰባ ላይ አላቀረበም። ቋሚ ኮሚቴው ጉዳዩን በተመለከተ የደረሰበትን ድምዳሜ በጽሕፈት ቤት የሰጠው ውሳኔ ስለመኖሩ ለኅትመት እስከተገባበት ሰዓት ድረስ ለማጣራት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...