Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ ተፈጥሮ በነበረ የቡድን ፀብ ምክንያት ታስረው የነበሩ ወጣቶች ተለቀቁ

ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ ተፈጥሮ በነበረ የቡድን ፀብ ምክንያት ታስረው የነበሩ ወጣቶች ተለቀቁ

ቀን:

‹‹ኢትዮጵያዊያን በማኅበራዊ ድረ ገጾች የሚለቀቁ የሐሰት ወሬዎችን መጠንቀቅ አለብን››

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር

እሑድ መጋቢት 8 ቀን 2011 ዓ.ም. ከ10፡00 ሰዓት አካባቢ በአንድ የታክሲ ሾፌርና በጫት ነጋዴዎች መካከል የተፈጠረው ጊዜያዊ አለመግባባት፣ በነጋታው ሰኞ መጋቢት 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ወደ ቡድን ፀብ በመሸጋገሩና ኹከት በመፈጠሩ ምክንያት ታስረው የነበሩ ወጣቶች ተለቀቁ፡፡

- Advertisement -

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ አየር አምባ ትምህርት ቤት አካባቢ ተፈጥሮ የነበረው የግለሰቦች ግጭት ወደ ቡድን ፀብ ከፍ ቢልም፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ፈጥነው በመድረስ ፀቡን ማስቆማቸውንና በወቅቱ 231 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውለው እንደነበር ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ቀደም ሲል በቡድን ፀቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸው 72 ተጠርጣሪዎችን በማስቀረት፣ 159 ተጠርጣሪዎችን ወዲያውኑ መልቀቁንም በኮሚሽኑ የኢንዶክትሪኔሽንና ሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የፀቡ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ አምስት ሴቶችና 67 ወንዶች ላይ በተደረገ ምርመራ የፀቡ መነሻና የደረሰው ጉዳት ታይቶ፣ በድጋሚ በተመሳሳይ ድርጊት ላይ እንዳይሳተፉ በመምከር ከእስር እንዲፈቱ መደረጋቸውን ምክትል ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ በእስር ያደሩት ወጣቶች ከእስር ከተፈቱ በኋላ ማክሰኞ መጋቢት 10 ቀን 2011 ዓ.ም. ረፋዱ ላይ የተወሰኑ ወጣቶች በአካባቢው ተሰባስበው ረብሻውን እንደገና ለመጀመር የሞከሩ ቢሆንም፣ ፖሊስ አስቀድሞ መረጃው ደርሶት ስለነበር በፍጥነት በመድረስ እንዲበተኑ ማድረጉን ኮማንደር ፋሲካ ገልጸዋል፡፡

 በአካባቢው በተከሰተው የቡድን ግጭት የሦስት ተሽከርካሪዎች መስተዋት፣ ሦስት በመስተዋት የተሸፈኑ የጫት ቤቶችና በአካባቢው የሚገኘው የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከአንድ የመስኮት መስታወት በስተቀር በሰው ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳልደረሰ ኮማንደሩ አስረድተዋል፡፡

በዕለቱ በጫት ነጋዴዎችና በታክሲ ሾፌሩ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ፖሊስና የአካባቢው ሽማግሌዎች ጭምር የአካባቢውን ወጣቶች በመምከር ማስማማት የተቻለ ቢሆንም፣ በማኅበራዊ ድረ ገጾች የተለቀቀው ሐሰተኛ ወሬ ግለሰባዊ ግጭቱን አገራዊ አድርጎት እንደነበረ ኮማንደሩ ገልጸዋል፡፡

በጣም አሳዛኝና ኢትዮጵያዊያንን የማይገልጽ ድርጊት በየዕለቱ በተለይ በፌስቡክና በተለያዩ ድረ ገጾች እየተለቀቀ በመሆኑ ሁሉም ወገን ሊጠነቀቅ እንደሚገባ የጠቆሙት ኮማንደር ፋሲካ፣ ይኼንን ግለሰባዊ ግጭት ወደ ዘር ግጭት ለመውሰድ የተደረገው ጥረት አስተማሪ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአካባቢው እንኳን የዘር ግጭት ሊነሳ ቀርቶ ያሰበው እንኳን በሌለበት፣ የፖለቲካ ድርጅት ባንዲራ የያዙ ወጣቶች እንደተሳተፉ ተደርጎ በማኅበራዊ ድረ ገጾች ተቀነባብሮ ተለቆ መታየቱ አሳፋሪና ማንንም የማይወክል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ዜጎች በተለያዩ ድረ ገጾች የሚለቀቁና የሚናፈሱ ወሬዎች ሁሉ እውነት እንዳልሆኑ መገንዘብና መጠንቀቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...