Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ተመዝጋቢዎች መቆጠብ ያለባቸው የገንዘብ መጠን ይፋ ሆነ

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ተመዝጋቢዎች መቆጠብ ያለባቸው የገንዘብ መጠን ይፋ ሆነ

ቀን:

ለ40/60 እና ለ20/80 ፕሮግራሞች 3.3 ቢሊዮን ብር ተደጉሟል ተብሏል

የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ በሚወጣባቸው 18,576 የ40/60 ባለ አንድ፣ ባለ ሁለትና ባለ ሦስት መኝታ ቤት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ የሚካተቱት ተመዝጋቢዎች፣ እስካሁን መቆጠብ ያለባቸው 40 በመቶ የገንዘብ መጠን ይፋ ሆኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሰናይት ዳምጠው (ኢንጂነር) እንዳስታወቁት፣ መንግሥት ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ የተቀናጀ የቤቶች ልማት ፕሮግራም ተግባራዊ በማድረግ ላይ ነው፡፡ በ20/80 ፕሮግራም ረቡዕ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕለት ለ13ኛ ጊዜ በዕጣ የሚያከፋፈላቸው ቤቶች ብዛት 32,653 ናቸው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ በዕጣ የሚከፋፈሉት የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ብዛት 18,576 መሆኑን ጠቁመው፣ በሁለቱም ፕሮግራሞች የተመዘገቡ ቤት ፈላጊዎች የቅድሚያ ክፍያ ማለትም 20 በመቶና 40 በመቶ የሚሆነውን ቅድሚያ ክፍያዎችን ሳያቋርጡ የቆጠቡ፣ ወይም እስከ ታኅሳስ ወር 2011 ዓ.ም. የቆጠቡ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

የ40/60 ተመዝጋቢዎች ለባለ አንድ መኝታ ቤት 65,058 ብር፣ ለባለ ሁለት መኝታ ቤት 100,000 ብር፣ ለባለ ሦስት መኝታ ቤት ደግሞ 154,560 ብር የቆጠቡ መሆን እንዳለባቸው የቢሮ ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡ የቤቶቹ ስፋት እንደ ቅደም ተከተላቸው 60 ሜትር ካሬ፣ 80 ሜትር ካሬና 100 ሜትር ካሬ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡

መንግሥት የመሠረተ ልማትና የሊዝ ዋጋን ሳይጨምር ለ20/80 እና ለ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ ድጎማ ማድረጉን የቢሮ ኃላፊዋ አስረድተዋል፡፡

እንደ ቢሮ ኃላፊዋ ገለጻ፣ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዋጋ በካሬ ሜትር 6,922 ብር ነው፡፡ በመሆኑም 60 ካሬ ሜትር ባለ አንድ መኝታ ቤት ጠቅላላ ዋጋው 415,320 ብር ይሆናል፡፡ 80 ሜትር ካሬ ባለ ሁለት መኝታ ቤት 553,760 ብር ሲሆን፣ 100 ሜትር ካሬ ባለ ሦስት መኝታ ቤት 692,200 ብር መሆኑ ታውቋል፡፡

የመጀመርያ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዋጋ ከሁለተኛው ዙር ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ ቢሆንም፣ ምክንያቱ ደግሞ የካሬ ሜትር ልዩነት ስላለው ነው ተብሏል፡፡ የመጀመርያው ዙር ባለ አንድ መኝታ ቤት እንደተገነባ ሲነገር ቆይቶ ዕጣው ሊወጣ ቀናት ሲቀሩት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ በነበሩት አቶ አባተ ስጦታው አማካይነት፣ ‹‹ባለ አንድ መኝታ ቤት የለም፤›› መባሉ ይታወሳል፡፡ ለዜጎች እየተሠራ በዜጎች ላይ መቀለድና ማናለብኝነት ጎልቶ የታየበት እንደሆነ በወቅቱ ተመዝጋቢዎች አምርረው መናገራቸውንና በመንግሥት አመራሮች ላይ እምነት ማጣታቸውን መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ባለ ሁለት መኝታ ቤት 100 ሜትር ካሬ፣ ባለ ሦስት መኝታ ቤት 150 ሜትር ካሬና ባለ አራት መኝታ ቤት 170 ሜትር ካሬ ስፋት የነበራቸው ሲሆን፣ ጠቅላላ ክፍያውም እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ደርሶ እንደነበር በወቅቱ መዘገባችን አይዘነጋም፡፡ ረቡዕ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በዕጣ የሚከፋፈለው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ስፋት ከመጀመርያው ዙር የቀነሰ በመሆኑ ጠቅላላ ክፍያውም ዝቅ ያለ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት በመጀመርያው ዙር በዕጣ የተካተቱት መቶ በመቶ ሙሉ ክፍያውን ቀድመው መቆጠብ የቻሉ ወይም በአንድ ጊዜ መክፈል የቻሉ የነበሩ ቢሆንም፣ ሁለተኛውን የዕጣ አወጣጥ ለየት የሚያደርገው 40 በመቶ የቆጠቡ ሁሉ በዕጣው ውስጥ የሚካተቱ መሆናቸውን የቢሮ ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡ ይኼ በመሆኑም ገንዘብ እያላቸው በራሳቸው አቅም መገንባት ወይም መግዛት የሚችሉ፣ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ነዋሪዎች ዕድል እንዳያሳጡ ማድረግ በዋናነት ተጠቃሽ መሆኑን አክለዋል፡፡

በ1996 ዓ.ም. ተመዝግበውና በድጋሚ በ2005 ዓ.ም. ተመዝግበው ላለፉት 15 ዓመታት በመጠባበቅ ላይ ያሉትን ጨምሮ 947,000 ነዋሪዎች በ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች አሉ፡፡ ከባለ ሦስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች በስተቀር ረቡዕ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በሚወጣው ዕጣ የሚሳተፉት ነባሮቹ ወይም በ1996 ዓ.ም. እና በድጋሚ በ2005 ዓ.ም. የተመዘገቡ ብቻ መሆናቸውን የቢሮ ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡

ባለ ሦስት መኝታ ቤት የተመዘገቡ ግን ሙሉ በሙሉ በዕጣው ውስጥ እንደሚካተቱ አክለዋል፡፡

ቀደም ብሎ ለ12 ጊዜያት 175,000 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ የተሰጡ ሲሆን፣ በ13ኛው ዙር 32,653 ቤቶች በዕጣ እንደሚሰጡ ታውቋል፡፡ በመሆኑም ቤቶቹ ስቱዲዮ፣ ባለ አንድ መኝታ፣ ባለ ሁለት መኝታና ባለ ሦስት መኝታ ሲሆኑ፣ የዋጋ ተመናቸው እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡

 

 

 

 

የቤቶች ዓይነት

(20/80)

 

የቤቶች ሥፋት (በካሬ)

 

ለዕጣ የቀረቡ የቤቶች ብዛት (32,653)

 

ለዕጣ ብቁ ለመሆን መቆጠብ የሚገባው የብር መጠን (እስከ ታኅሳስ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ

 

የ13ኛው ዙር (2011) የቤቶች የማስተላለፊያ ዋጋ

100%

20%

ስቱዲዮ

30

1,248

6,040

135,338

13,534(10%)

ባለ 1 መኝታ ቤት

55

18,823

10,960

248,105

49,624

ባለ 2 መኝታ ቤት

75

7,127

22,560

338,345

67,669

ባለ 3 መኝታ ቤት

105

5,455

29,340

473,655

94,737

የ13ኛው ዙር የ20/80 የማስተላለፊያ ዋጋ በአንድ ካሬ ሜትር = 4511.27 ብር

የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቀደም ባሉት ዙሮች ይወጡ ከነበሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዋጋ አንፃር ጭማሪ የተደረገባቸው ቢሆንም፣ የመሠረተ ልማትና የሊዝ ዋጋን እንደማይጨምር ቢሮ ኃላፊዋ ጠቁመዋል፡፡

የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በካሬ ሜትር 4,511 ብር ሲሆኑ፣ መንግሥት በእያንዳንዱ ካሬ ሜትር ላይ 1,000 ብር ድጎማ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

በአጠቃላይ መንግሥት ከ13,600 በላይ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችና ከ39,000 በላይ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በግንባታ ላይ እንደሆኑ ከ2009 ዓ.ም. ጀምሮ ቢቆይም፣ ረቡዕ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሹማምንት በተገኙበት ዕጣ ይወጣባቸዋል የተባሉት 51,229 ቤቶች ናቸው፡፡ እነዚህም ቢሆኑ ግንባታቸው 85 በመቶ የተጠናቀቁና እስከ 2012 ዓ.ም. አጋማሽ ድረስ ግንባታቸው ይጠናቀቃል የሚል ግምት መያዙ ተጠቁሟል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...