Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናዓቃቤ ሕግ በኢምፔሪያልና በሪቬራ ሆቴሎች ላይ ባቀረበው ክስ ለቀረበበት መቃወሚያ ምላሽ ሰጠ

ዓቃቤ ሕግ በኢምፔሪያልና በሪቬራ ሆቴሎች ላይ ባቀረበው ክስ ለቀረበበት መቃወሚያ ምላሽ ሰጠ

ቀን:

የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ በኮርፖሬሽኑ የተለያየ ኃላፊነት የነበራቸው ዘጠኝ ተከሳሾች፣ ከኢምፔሪያል ሆቴልና ከሪቬራ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤቶች ጋር በጥቅም በመመሳጠር ግዥ እንዲፈጸም ተደርጓል በሚል በቀረበው ክስ ላይ፣ ተከሳሾቹ ያቀረቡትን መቃወሚያ በመቃወም ዓቃቤ ሕግ ምላሽ ሰጠ፡፡

ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ሥልጣናቸውን ያላግባብ መገልገላቸውንና ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማለት በአማራጭ ክስ ሊቀርብባቸው እንደማይገባ መቃወሚያ ማቅረባቸውን የጠቆመው ዓቃቤ ሕግ፣ በወንጀል ሕግ ድንጋጌ ላይ መገለጹንና ወደፊትም በማስረጃ ማሰማት ሒደት የሚጣራ በመሆኑ፣ መቃወሚያው ውድቅ እንዲደረግለት ጠይቋል፡፡ ጄኔራሉ ያላግባብ ስለመጠቀማቸው በግልጽ ስላለመጠቀሱና ሆቴል እንዲገዛ የማዘዝ ሥልጣን ይኑራቸው ወይም አይኑራቸውም ስላልገለጹ የቀረበውን መቃወሚያ በሚመለከት፣ ዓቃቤ ሕግ የዋና ዳይሬክተሩ ሥልጣን ከምን እንደሚመነጭ የሚገልጽ ሰነድ ከክሱ ጋር ማያያዙንና የወንጀል ሕግ አንቀጽ 407 (1ሀ እና ለ) እና (3)ን መመልከት አስፈላጊ መሆኑን፣ ወደ ፊትም በማስረጃ መሰማት ሒደት ምላሽ እንደሚያገኝ ገልጿል፡፡

የሆቴልና የፋብሪካ ግዥን በሚመለከት በኮርፖሬሽኑ የግዥ መመርያ ያልተሸፈነ ስለሆነ ሕግ መተላለፋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አለማመላከቱን የቀረበውን መቃወሚያ በሚመለከት፣ ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመበት ዓላማ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 183/2002 አንቀጽ (5) በዝርዝር ሠፍሮ ስለሚገኝ መቃወሚያ የሚያስነሳ ባለመሆኑ መቃወሚያው ውድቅ እንዲደረግ ዓቃቤ ሕግ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡ ሆቴልና ፋብሪካ አንድ ላይ ጨረታ ስለመውጣቱ በማስረጃ ማሰማት ሒደት የሚነሳ መሆኑን አክሏል፡፡ ሌሎች መቃወሚያዎች የፍሬ ነገር ክርክሮች በመሆናቸው በመጀመርያ መቃወሚያ የሚቀርብ አለመሆኑን ገልጿል፡፡

- Advertisement -

በአቶ ዓለም ፍፁም የቀረበው መቃወሚያ ‹‹ታይልና ማት›› የተባሉት ማሽኖች በርክክብ ወቅት ይሠሩ እንደነበርና የደረሰውም ጉዳት የፍትሐ ብሔር ጉዳይ ስለመሆኑ በመግለጽ የቀረበውን መቃወሚያ በሚመለከት፣ ዓቃቤ ሕግ የፍሬ ጉዳይ ክርክር መሆኑን ጠቅሶ በቅድመ መቃወሚያ የሚቀርብ አይደለም እንዲባልለት ጠይቋል፡፡  

የካፒታል ጌይን ታክስና የገቢ ግብር ታክስ የሚሉት ቃላት አሻሚ ስለመሆናቸው የቀረበው መቃወሚያ ወደፊት በማስረጃ የሚታይ መሆኑን፣ ነገር ግን ተከሳሹን የሚመለከቱ መሆናቸውን በክሱ በግልጽ መብራራቱን ጠቁሟል፡፡ በተከሳሽ የቀረቡት አብዛኛዎቹ መቃወሚያዎች በፍሬ ነገር ክርክር የሚቀርቡና በማስረጃ ማሰማት ሒደት የሚታዩ በመሆናቸው፣ ተቃውሞው ውድቅ እንዲደረግለት ዓቃቤ ሕግ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

ከኢምፔሪያል ሆቴል ሽያጭ ጋር በተያያዘ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ተሳትፏቸው በእጅ አዙር ይሁን በቀጥታ እንዳልተገለጸ ለቀረበው መቃወሚያ መልስ የሰጠው ዓቃቤ ሕግ፣ ማስረጃዎቹ ተከሳሹ ውል መፈጸማቸውንና ክፍያ መቀበላቸውንና በቀጥታ ተሳታፊ መሆናቸውን የሚያሳዩ በመሆኑ መቃወሚያው አግባብነት እንደሌለው ገልጿል፡፡

ሌላው አቶ ኤርሚያስ ያነሱት ተቃውሞ የአክሰስ ሪል ስቴት ሥራ አስኪያጅ ሆነው አክሰስ ሳይከሰስ እሳቸው ሊከሰሱ እንደማይገባ መሆኑን ሲሆን፣ ዓቃቤ ሕግ አብራርቷል፡፡

በወንጀል ሕግ አንቀጽ 34 ድንጋጌ መሠረት፣ አንድ በሕግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት ክስ ሊቀርብበትና ሊቀጣ የሚችለው በሕግ ላይ በግልጽ ተደንግጎ ሲገኝ ነው፡፡ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 407 ደግሞ በሕግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት ሊከሰስና ሊቀጣ እንደሚችል ባለመደንገጉ በድርጀቱ ላይ ክስ አልቀረበበትም፡፡ ድርጀቱ አልተከሰሰም ማለት ግን ወንጀል የፈጸመው ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አይከሰስም ማለት ባለመሆኑ፣ አቶ ኤርሚያስ በወንጀሉ ስለመሳተፋቸው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 እና ተከታዮቹን ማየት በቂ በመሆኑ መቃወሚያው አግባብ አለመሆኑን አስረድቷል፡፡

በወንጀል ሕግ አንቀጽ 23(2) ድንጋጌ መሥፈርት መሠረት፣ የቀረበባቸው ክስ የወንጀል ማቋቋሚያ ሐሳብ ክፍል ስላለመሟላቱ የቀረበው መቃወሚያ አግባብነት የሌለው መቃወሚያ በመሆኑ ውድቅ እንዲደረግት ጠይቋል፡፡ በአጠቃላይ ሁሉም ተከሳሾች ያቀረቡት መቃወሚያ አግባብነት የሌለው በመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ውድቅ በማድረግ ምስክሮቹን እንዲያሰማ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ዓቃቤ ሕግ ጠይቋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...