Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊሠራተኞችን ወደ ዓረብ አገሮች ለመላክ መንግሥታት ስምምነት ቢፈጽሙም አስፈጻሚው ግራ እያጋባቸው መሆኑን...

ሠራተኞችን ወደ ዓረብ አገሮች ለመላክ መንግሥታት ስምምነት ቢፈጽሙም አስፈጻሚው ግራ እያጋባቸው መሆኑን ኤጀንሲዎች ገለጹ

ቀን:

በተለያዩ የሥራ መስኮች ሠራተኞችን ወደ ዓረብ አገሮች ለመላክ በኢትዮጵያ መንግሥትና በአራት የዓረብ አገሮች መንግሥታት መካከል ስምምነት ተደርጎ በየፓርላማቸው የፀደቀ ቢሆንም፣ አስፈጻሚው የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ግራ እያጋባቸው መሆኑን የውጭ ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ገለጹ፡፡

ሐሙስ ጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀውን የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ስምምነት ጨምሮ፣ ሠራተኞችን ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ከጆርዳንና ከኳታር ጋር የሥራ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ስለሠራተኞች ምልመላ፣ የጤና ምርመራ፣ ሥልጠናና ሌሎች መሟላት ያለባቸው ነገሮችን በሚመለከት በአዋጅ ቁጥር 923/2008 ላይ መሥፈርቶች የተቀመጡ ቢሆንም፣ መሥፈርቶቹን የሚጥስና ተግባራዊ ለማድረግ የሚያዳግት መግለጫ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባለሥልጣናት እየተሰጠ በመሆኑ ግራ መጋባታቸውን ኤጀንሲዎቹ አስታውቀዋል፡፡

- Advertisement -

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ወደ ጆርዳንና ኳታር ሠራተኞችን መላክ እንደሚቻል የገለጸ ቢሆንም፣ ወደ እነዚህ አገሮች ለመላክ የሚያስችለውን ፈቃድ የወሰደ ላኪ ኤጀንሲ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ በአዋጁ እንደተደነገገው የላኪ ኤጀንሲ ባለቤት ወይም ተወካይ ሠራተኞችን ወደሚልክባቸው አገሮች መግባትና መውጣት ስለመቻሉ ከመድረሻ አገሮች ማረጋገጫ ማግኘት ቢኖርበትም፣ አንድም የኤጀንሲ ባለቤትም ሆነ ተወካይ ያገኘ እንደሌለ አክለዋል፡፡ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ሠራተኞችን ለመላክ ፈቃድ የወሰዱ ኤጀንሲዎች ቢኖሩም፣ ሠራተኞቹ ከመሄዳቸው በፊት ማድረግ ስላለባቸው የጤና ምርመራ በሕጉ በመደንገጉ፣ በትክክለኛ መንገድ የተመረጡትን የጤና ተቋማት ከማወቅ ጋር በተያያዘ መሥራት እንዳልቻሉም ተጠቁሟል፡፡ ከተቀባይ አገሮች ቪዛ ለመቀበል መጀመርያ የተመለመሉት ሠራተኞች ጤናቸውን መመርመርና ማረጋገጥ፣ ሥልጠና መስጠት ቅድሚያ የሚሰጣቸው መስፈርቶች ቢሆኑም፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ‹‹ሠራተኞችን መላክ ይቻላል›› በማለት ተጨባጭ ሁኔታዎችን ሳያረጋግጥ የሰጠው መግለጫ ትክክል ባለመሆኑ ሊስተካከል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተመረጡ የጤና ተቋማት መኖራቸው ቢታወቅም፣ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን በአዲስ አበባ 59፣ በክልሎች ደግሞ 12 የጤና ተቋማት መመረጣቸውን በማሳወቅ ምርመራ ማድረግ እንደሚችሉ መግለጫ በመስጠቱ፣ ሕጋዊው የትኛው ሊሆን እንደሚችል ማወቅ እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡ ሌላው ኤጀንሲዎቹ የገለጹት ግራ የመጋባታቸው ዋና ምክንያት፣ ተቀባይ አገሮች የጤና ተቋማትን በራሳቸው መርጠው በድረ ገጾቻቸው ይፋ ማድረጋቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሳዑዲ ዓረቢያ 11 የጤና ተቋማትን የመረጠች ሲሆን፣ ተቋማቱም ከአምስት ዓመታት በፊት ይሠሩ የነበሩና በጂሲሲ (ጋምካ) ተመርጠው የነበሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ጆርዳንም ሰባት የሕክምና ተቋማትን መምረጧንና ሌሎቹ አገሮችም የመረጡ ቢሆንም ገና ይፋ አለማድረጋቸውን ኤጀንሲዎቹ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም የሚመለከተው አስፈጻሚ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤትም ሆነ መንግሥት፣ በጉዳዩ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሕጉን በተከተለ አሠራር እንዲተገበር እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡

ኤጀንሲዎቹ የሚያቀርቡትን አቤቱታ በሚመለከት ማብራሪያ ለማግኘት ለሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት ዳይሬክተሩን አቶ ብርሃኑ አበራና ለኮሙዩኒኬሽን ኃላፊው አቶ አሰፋ ይርጋለምን ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም፣ ለተላከላቸው አጭር የጽሑፍ መልዕክትም ሆነ ስልካቸውን በማንሳት ምላሽ ሊሰጡ ስላልቻሉ አልተሳካም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...