Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ በ46 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመሥረቱን ጠቅላይ ዓቃቤ...

የሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ በ46 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመሥረቱን ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ

ቀን:

በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማና በተለያዩ የክልሉ ከተሞች፣ ዞኖችና ወረዳዎች ከሐምሌ 26 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በተፈጸሙ ግድያ፣ አካል ማጉድል፣ መድፈር፣ ቃጠሎና ማፈናቀል ጋር በተያያዘ የቀድሞ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ 46 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመሥረቱን ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡

በክልሉ በደረሰው ከፍተኛ ዕልቂት 50 ሰዎች ተገድለው በጅምላ መቀበራቸውን፣ ቁጥራቸው ያልታወቁ የሃይማኖት ተቋማት፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የግል ተቋማትና መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ላለፉት አምስት ወራት በተደረገ ምርመራ መረጋገጡንም ዓቃቤ ሕግ ገልጿል፡፡

የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱናና የድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ምክትል ዳሬክተር አቶ ተመስገን ላጲሶ ዓርብ ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደገለጹት፣ በተያዙና በእስር ላይ በሚገኙት ላይ ምርመራው የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ ከተፈጸመው የወንጀል ድርጊት አንፃር ወደ ጎረቤት አገር በሸሹ ተጠርጠሪዎች ላይ ምርመራው ይቀጥላል፡፡

- Advertisement -

በተጠርጣሪዎቹ ላይ የተመሠረቱት የክስ ዓይነቶች ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማፍረስ ማነሳሳት፣ አስገድዶ መድፈርና ሌሎችም መሆናቸውን ኃላፊዎቹ ገልጸው፣ ጥር 20 ቀን 2011 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክስ መዝገብ እንደሚከፈት አረጋግጠዋል፡፡

በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ ሲደረግባቸው የነበሩት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ (አብዲ ኢሌ)፣ የሕፃናትና ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ወ/ሮ ረሃማ መሐመድ፣ የዳያስፖራ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ አብዱራዛቅ ሳኒ፣ የፖሊስ ኮሚሽነሩ አቶ ፈርሃን ጣሂርና ሁለት ሄጎ የሚባል ቡድን አባላት የነበሩ ወጣቶች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 40 ተጠርጣሪዎች ከአገር መውጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በሌሉበት ክስ የተመሠረተባቸው ሲሆን፣ የተወሰኑት ከኢትዮጵያ ጋር ጥሩ ግንኙነትና እስረኛን አሳልፎ ለመስጠት ስምምነት ያላቸው በመሆኑ፣ በቅርቡ ተላልፈው እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡ ቀሪዎቹንና ወደ ሌላ አገር የሄዱትን ደግሞ ማንም አገር የወንጀል ተጠርጣሪን ይዞ ስለማያቆይ፣ በመነጋገር የሚመጡበትን ሒደት ለማመቻቸት እየተሠራ መሆኑንም አክለዋል፡፡

ተጠርጥረው ያልተከሰሱ የክልሉ ባለሥልጣናት መኖራቸውን የገለጹት ኃላፊዎቹ፣ ያለመከሰስ መብታቸውን ለማስነሳት ከክልሉ መንግሥት ጋር እየተነጋገሩም መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በክልሉ የተፈጸመውን ጉዳይ በሚመለከት ፍርድ ቤት እየተከታተለው መሆኑን፣ ለሚደረገው ምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ቆይቶ ክስ ሊመሠረት ሲል መግለጫ መስጠት በፍርድ ቤት ሥራ ላይ ጫና መፍጠርና ከፍርድ ቤት ነፃነት ጋር ስለመጋጨቱ ተጠይቀው፣ ‹‹በእኛ እምነት አይጋጭም፡፡ መግለጫ የምንሰጠው በራሳችን የደረስንበትን መረጃ ይዘን ሕዝብ እንዲያውቅ ለማድረግ ነው፡፡ ወደፊትም በዚሁ ነው የምንቀጥለው፡፡ ፍርድ ቤቶች በነፃነትና በገለልተኛነት ስለሚሠሩ ምንም የሚያጋጨው ነገር የለም፤›› ብለዋል፡፡

ምርመራው ከአምስት ወራት በላይ መፍጀቱ ዜጎች የተፋጠነ ፍትሕ ከማግኘታቸው ጋር ስለመጋጨቱ ተጠይቀው፣ ችግሩ የተፈጠረው በግለሰቦች ተነሳሽነት ብቻ ሳይሆን፣ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ጭምር በመሆኑ ውስብስብና አስቸጋሪ ስለሆነ ጊዜ ሊወስድ እንደቻለ ተናግረዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...