Saturday, June 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንና ስኳር ኮርፖሬሽን በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩ 16 ግለሰቦች...

ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንና ስኳር ኮርፖሬሽን በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩ 16 ግለሰቦች ክስ ተቋረጠ

ቀን:

የስኳር ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት በሞት ተለዩ

በሐምሌ ወር 2009 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው ላለፉት 17 ወራት በእስር ላይ ሆነው ሲከራከሩ የከረሙት፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣንና የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች የነበሩ 16 ግለሰቦች ክስ ተቋርጦ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ የተሰጠላቸው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር በነበሩት አቶ ዚያድ ወልደ ገብርኤል መዝገብ የተካተቱት (የአቶ ዚያድ ክስ ቀደም ብሎ መቋረጡ ይታወሳል) አቶ አብዶ መሐመድ፣ አቶ በቀለ ንጉሤ፣ አቶ ገላሶ ቦሬ፣ ሚስተር ያንግ ሬንኋ (ያልተያዙ)፣ ሚስተር ኬን ሮበርትስ (ያልተያዙ)፣ አቶ ከበደ ወርቅነህ፣ አቶ እስክንድር ሰይድ፣ አቶ አማረ አሰፋ፣ አቶ ደረጀ ኪዳኔ (ያልተያዙ)፣ አቶ ገብረአናንያ ፃድቅና አቶ አማረ አሰፋ ናቸው፡፡ ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ደግሞ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ዘነበ ይማም፣ አቶ እንዳልካቸው ግርማ፣ አቶ ሀየሎም አብዶና አቶ በለጠ ዘለለው ናቸው፡፡

ክሱ እንዲቋረጥ የጠየቀው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6(3ሠ) በተሰጠው ክስ የማቋረጥ ሥልጣን ሲሆን፣ ክሱን ሲመረምርና ሲያከራክር ለከረመው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት፣ ፍርድ ቤቱ የክርክር ሒደቱ እንዲቋረጥ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ‹‹ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ክሱ እንዲነሳ ተወስኗል›› በማለት በምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ገለታ ሥዩም ፊርማ በቀረበ ጥያቄ ክሱ ተቋርጦላቸው ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ ተከሳሾቹ ከመንገድ ግንባታ፣ ከሕገወጥ ጨረታ፣ ከሕገወጥ ግዥና ከሌሎች የወንጀል ድርጊቶች ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ጉዳት በሕዝብና በመንግሥት ላይ አድርሰዋል ተብለው የቀረበባቸውን ዝርዝር የክስ ሒደት በወቅቱ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን፣ የአገዳ ተክልና የፋብሪካ ግንባታ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አበበ ተስፋዬ (ኢንጂነር)፣ አብረዋቸው ተከሰው የነበሩ ጓደኞቻቸው ክሳቸው ተቋርጦ ሲፈቱ እሳቸው ሐሙስ ጥር 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የሪፖርተር ምንጮች ተናግረዋል፡፡ አቶ አበበ ሕይወታቸው ያለፈው በሕክምና ሲረዱ በነበሩበት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ መሆኑንም አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...