Monday, June 17, 2024

የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ ቢሯቸው ገባች

[ክቡር ሚኒስትሩ በቅርቡ አምባሳደር ከሆኑ ጓደኛቸው ጋር እየተነጋገሩ ነው]  

 • እንዴት ነህ ወዳጄ?
 • ምነው ግብዣው ላይ ቀሩ ክቡር ሚኒስትር?
 • የምን ግብዣ?
 • ሆቴል እኮ ነው የደገስኩት፡፡
 • ልጅህን ዳርካት እንዴ?
 • ኧረ ሠርግ አይደለም፡፡
 • ታዲያ መቼም ቤትህን አስመርቀህ ሆቴል አትጠራም ብዬ ነዋ?
 • የቤት ምርቃትም አይደለም፡፡
 • የምን ድግስ ነው ታዲያ?
 • የሹመቴን ነዋ ክቡር ሚኒስትር?
 • አምባሳደርነቱን?
 • አዎን ክቡር ሚኒስትር?
 • አምባሳደርነት ምን ያስደግሳል ብለህ ነው?
 • እኔማ በፊት እኮ ህልሜ ሁሉ አምባሳደር መሆን ነበር፡፡
 • ለምን?
 • በቃ ብዙ ጥቅማ ጥቅሞች አሉታ፡፡
 • ስማ ከአምባሳደርነት ይልቅ እዚህ ባለህ ሹመት እኮ ብዙ ጥቅማ ጥቅሞች ነበሩህ፡፡
 • አዎ የዚህኛው ግን ያስፈራል እኮ?
 • እንዴት?
 • ያው የጊዜ ጉዳይ እንጂ መያዝዎት አይቀርማ፡፡
 • ታዲያ አምባሳደርነት ምን ያስገኝልሃል?
 • ከቀረጥ ነፃ መብቱ በጣም ነው የሚያቋምጠኝ፡፡
 • እ…
 • በአቋራጭ እንደ እናንተ መሆኔ አይቀርም፡፡
 • እንዴት ሆኖ?
 • የቀረጥ ነፃ መብቴን ተጠቅሜ በአጭር ጊዜ ነው ሆቴል ለመገንባት ነው ያሰብኩት፡፡
 • በቀረጥ ነፃ ብረት ልታስገባ?
 • ምን ችግር አለው ክቡር ሚኒስትር?
 • ሌላስ?
 • በዚያ ላይ በርካታ ባለሀብቶች ወደ አገር ቤት ስልክ ከእኔ ጋር እንዲሠሩ አስቤያለሁ፡፡
 • እሺ፡፡
 • ኢንቨስተሮቹም ሲመጡ የምገነባው ሆቴል እንዲያርፉ ነው የማደርገው፡፡
 • ሌላስ?
 • እኔማ በጡረታዬ ጊዜ ጥሩ የምዝናናበት አገር እንዲደርሰኝ ፀልዬ ነበር ፀሎቴም ሰምሯል፡፡
 • ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠሩትን ስብሰባ ተካፍለህ ነበር?
 • አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ታዲያ አሁን የምትላቸው ነገሮች የህልም እንጀራ ናቸው እኮ?
 • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
 • አምባሳደርነት እንደ ድሮው የጡረተኛ ቦታ አይደለማ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር እኛ እኮ ለአገራችን የለፋን ዜጎች ነን፡፡
 • ታዲያ ምን ይፈጠር?
 • አሁን አገራችን ልትጦረን ይገባል?
 • ታዲያ አምባሳደርነትን ማን ነው መጦሪያ ያደረገው?
 • መንግሥት ነዋ፡፡
 • ከዚህ በኋላ ግን ያ አካሄድ አያስኬድም፡፡
 • እና እንደተባለው የሥራ ቦታ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ስማ የሪፎርሙ አምባሳደር መለኪያው አንድ ነገር ነው፡፡
 • ምንድነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ፐርፎርም ማድረግ!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚስታቸው ጋር እያወሩ ነው]

 • ይህች አገር ወዴት እያመራች ነው?
 • ምን ሆንክ ደግሞ?
 • ከተማው እኮ ቀጥ ሊል ነው፡፡
 • ምን ተፈጥሮ?
 • ከተማው ውስጥ እንቅስቃሴ የለም፡፡
 • ምንድነው የምታወራው?
 • በከተማው የለሽም እንዴ?
 • ምን እያልክ ነው?
 • ከተማ ውስጥ ነዳጅ የለም፡፡
 • ምን ተፈጥሮ?
 • መኪናዬ መንገድ ላይ ቀጥ ብላብኝ ነበር፡፡
 • ወጥቼ ገፋሁ እንዳትለኝ?
 • እኔማ ማደያ የሚደርስ ነዳጅ ገዛሁ፡፡
 • ከየት?
 • ከጥቁር ገበያ ነዋ፡፡
 • አንተ እኮ ተጠናውቶሃል አይደል?
 • ምኑ?
 • አሁንም ከጥቁር ገበያ ሥራ አልተላቀክም?
 • እኔ እኮ የመኪናዬ ጉዳይ አሳስቦኝ አይደለም፡፡
 • ምንድነው የሚያሳስብህ?
 • ስሚ የነዳጅ መጥፋት ቢዝነሳችንን በጣም ነው የሚጎዳው፡፡
 • እ…
 • ቦቴ መኪናችን እኮ ነዳጅ እንደያዘ ታግቶ ቆሟል፡፡
 • ወይ ጣጣ፡፡
 • በዚያ ላይ በትራንስፖርት ቢዝነስ ውስጥ ስላለን በቀጣይ እንዲህ ዓይነት የነዳጅ እጥረት ይጎዳናል፡፡
 • ምን ተሻለ ታዲያ?
 • ይህ የነዳጅ እጥረት ወደፊትም የሚቀጥል ይመስለኛል፡፡
 • ለምን?
 • እንደተረዳሁት በነዳጅ እጥረት ውስጥ በአጭሩ የሚከብሩ ሰዎች አሉ፡፡
 • አልገባኝም?
 • እኔ እኮ በጥቁር ገበያ አንድ ሊትር ቤንዚን 100 ብር ነው የገዛሁት፡፡
 • ምን እያልክ ነው ታዲያ?
 • የነዳጅ ቦቴ ስላለን ለምን የወረርናት መሬት ላይ አንከፍትም?
 • ምንድነው የምንከፍተው?
 • የነዳጅ ማደያ ነዋ፡፡
 • የማደያ ቢዝነስ አያዋጣም ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡
 • ስነግርሽ አይገባሽም እንዴ?
 • ምኑ?
 • ከዚህ በኋላ በተደጋጋሚ ግጭቶች ስለሚኖሩ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ አይቀሬ ነው፡፡
 • ማለት?
 • ስለዚህ እኛ ነዳጅ የምናቀርበው ለመደበኛ ተሽከርካሪዎች አይደለም፡፡
 • ታዲያ ለማን ነው?
 • እንደነገርኩሽ የእኛ ነዳጅ ማደያ የምትከፈተው ሁሌም በእጥረት ጊዜ ነው፡፡
 • ትርፉ ጥሩ ስለሆነ?
 • አዎን፣ አሁን እንዴት እንደምንሸጥ ገባሽ?
 • እንዴት ነው?
 • በጥቁር ገበያ!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከትንሹ ልጃቸው ጋር እያወሩ ነው]

 • ምን ሆነህ ነው ፊትህ እንደዚህ የበላለዘው?
 • በጣም የሚያናድድ ነገር ነው ዳዲ፡፡
 • ምን ተፈጥሮ ነው?
 • ያው ከክፍል አንደኛ እንደምወጣ ታውቃለህ?
 • ከዚህ ጋር ምን አገናኘው?
 • ቆይ አትቆጣ ዳዲ፡፡
 • እኮ ምን እንደተፈጠረ ንገረኛ?
 • እኛ ክፍል አንድ አዲስ ተማሪ መጣ፡፡
 • ከየት ነው የመጣው?
 • ከመንግሥት ትምህርት ቤት ነው፡፡
 • ለምን መጣ?
 • ያው እኛ ትምህርት ቤት የገባው ስኮላርሺፕ አግኝቶ ነው፡፡
 • ጎበዝ ተማሪ ነው ማለት ነው?
 • እንደሰማሁት በጣም ጎበዝ ተማሪ ነው፡፡
 • ታዲያ ምን ተፈጠረ?
 • እኛ ክፍል ሲገባ ፈራሁኝ ዳዲ፡፡
 • ለምንድነው የምትፈራው?
 • እኔ ሁሌ አንደኛ መውጣት ነዋ የለመድኩት፡፡
 • አሁንስ ማን ከለከለህ ታዲያ?
 • አዲስ የመጣው ልጅ ሊበልጠኝ ይችላል ብዬ ፈራሁ፡፡
 • እሺ፡፡
 • ከዚያማ ትምህርት ቤቱ ውስጥ ዘመቻ ከፈትኩበት፡፡
 • የምን ዘመቻ?
 • የመጣበት ትምህርት ቤት እንዲመለስ ነዋ፡፡
 • ምን ብለህ?
 • ለትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ደኅንነት ያሠጋል ብዬ ነዋ፡፡
 • ከየት ነው እንደዚህ ዓይነት ነገር የምትማረው?
 • ከእናንተ ነዋ፡፡
 • ምን?
 • ምነው ዳዲ?
 • ስማ ምን እንደምትመስል ዓይተኸዋል?
 • ልጁ እኮ ትልቅ ነው፡፡
 • ስለዚህ ነገም አይቀርልህም፡፡
 • ለዚህ ነበር አንተን የፈለግኩህ፡፡
 • እኔ ምንም አላደርግልህም ራስህ ይቅርታ ጠይቀው፡፡
 • በፍጹም አላደርገውም ዳዲ፡፡
 • ለምን?
 • ለማንም ተንበርክኬ አላውቅም፡፡
 • እንግዲያው ነገም ያቀምስሃላ?
 • ታዲያ አንተ ለምን አትመድብልኝም?
 • ምን?
 • አጃቢ!

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ ቢሯቸው ገባች]

 • ዛሬ ምን ተገኘ በጣም ዘንጠሻል?
 • በዓል መሆኑን ረሱት እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
 • በዓሉ አለፈ አይደል እንዴ?
 • የትኛው በዓል?
 • የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ነዋ፡፡
 • እኔ ደግሞ ገናን የሚሉኝ መስሎኝ ነበር፡፡
 • እኔማ የአገር ልብስ ለብሰሻል ብዬ ነው፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ሲባል አልሰሙም?
 • የጥምቀት በዓልን እኔም እወደዋለሁ፡፡
 • ለምን?
 • ከሕይወቴ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ስላለው ነዋ፡፡
 • እንዴት?
 • ተጠምቄያለኋ፡፡
 • በእግዚአብሔር ያምናሉ እንዴ?
 • በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ተጠምቄያለሁ፡፡
 • እ…
 • የጥምቀት በዓል ሁሉን አቀፍ ነው፡፡
 • እንዴት?
 • በመጥምቁ ዮሐንስ የተጠመቀውም፣ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ የተጠመቀውም፣ በሙስና የተጠመቀውም ሊያከብረው ይችላል፡፡
 • እየቀለዱ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • የእውነቴን ነው የምልሽ፡፡
 • ለማንኛውም ላስፈቅድዎት ነበር፡፡
 • ምንድነው የምታስፈቅጂኝ?
 • ታቦት ለመሸኘት ልሄድ ነበር?
 • ችግር የለውም አብረን እንወጣለን፡፡
 • እርስዎም ይሸኛሉ እንዴ?
 • አዎን፡፡
 • እኔ አላምንም ታቦት ሊሸኙ?
 • ታቦት አይደለም የምሸኘው?
 • ታዲያ ማንን ነው?
 • ጓደኛዬን፡፡
 • ወዴት?
 • ወደ ቂሊንጦ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን ቅሬታውንም አልሰማሁም። እንዴት? አልሰማሁማ? የምን ቅሬታ ቀርቦባቸው ነው? ሰሞኑን ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ውድና ቅንጡ አውሮፕላን ተከራይተዋል የሚል ቅሬታ...