Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም የ100 ሺሕ ብር ዋስትና ተፈቀደላቸው

የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም የ100 ሺሕ ብር ዋስትና ተፈቀደላቸው

ቀን:

የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው በ100 ሺሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰነ፡፡

የቀድሞ የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር አቶ ኢሳያስ ተጠርጥረው በእስር የቆዩት ኢትዮ ቴሌኮም በሶማሌ ክልልና በባሌ ዞን የሚያስተክለውን የሞባይል ኔትወርክ ማስፋፊያ ማማ ተከላ ያለጨረታ ለሜቴክ ሰጥተዋል በሚል ነበር፡፡

አቶ ኢሳያስ በሌላቸው ሥልጣን ውል በማሻሻል 202 ሚሊዮን ብር የነበረውን ውል ወደ 321 ሚሊዮን ብር አድርገዋል በሚል ነበር የተጠረጠሩት፡፡

- Advertisement -

ከወንድማቸው ጋር ተመሳጥረው ድርጊቱን ፈጽመዋል ተብሎ ተጠርጥረው የታሰሩ ቢሆንም፣ ፖሊስ ይህንን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ የዋስትና መብታቸው ሊከበር ይገባል ሲል የፌዴራል ከፍተኛ ፍድር ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ሰኞ ጥር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪው ከአገር እንዳይወጡ ዕግድ እንዲደረግ ለኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች ዋና መምሪያ ይጻፍ ብሏል፡፡ ፖሊስ ይህንን እንዲያረጋግጥና ከእስር እንዲፈቱም ተብሏል፡፡

ይሁንና፣ ፖሊስ ይግባኝ እላለሁ ይጻፍልኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...