Monday, June 17, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የአፍሪካ ንግድና ፋይናንስ ዓለም አቀፍ ጉባዔ በአዲስ አበባ ይስተናገዳል

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋና ከሚገኘው ‹‹Rescue shipping and investment Agency›› ጋር በመተባበር የመጀመርያውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ንግድና የፋይናንስ ጉባዔ በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡

ጉባዔው ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገሮችን የሚወክሉ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የትልልቅ ኩባንያዎች ባለቤቶችና ኃላፊዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ከሚያዝያ 3 እስከ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ እንደሚካሄድ ንግድ ምክር ቤቱ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በጉባዔው የንግድና የፋይናንስ ፖሊሲዎችና የማኔጅመንት ተሞክሮዎች ቀርበው ለግብዓትነት የሚረዱ ሐሳቦችም ላይ ውይይትና ግምገማ እንደሚካሄድ ንግድ ምክር ቤቱ ይጠቅሳል፡፡ በአፍሪካ አገሮች መካከል የሚካሄደው የእርስ በርስ የንግድ ልውውጥ አነስተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፣ አኅጉራዊና ክልላዊ አደረጃጀቶች የሚያበረክቱት አስተዋጽኦም በጉባዔው ቅኝት ይደረግበታል፡፡ በአፍሪካ የሚታየውን ዝቅተኛ የንግድ ትስስር መንስዔዎችና ምክንያቶች ከመፍትሔዎቹ ጋር በጉባዔው ውይይት እንደሚደረግባቸውም ይጠበቃል፡፡ የአፍሪካ ነፃ የንግድና የገበያ ቀጣናን ለመመሥረት የተቀመጠው ግብ ስለሚሳካበትና ሊያጋጥሙት በሚችሉት ፈተናዎች ብሎም ችግሮችን ለመቋቋም የአፍሪካ መንግሥታትና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች ሚናም በጉባዔው ለውይይት ከተመረጡት አጀንዳዎች መካከል ተካቷል፡፡

በጉባዔው ላይ በንግድና በፋይናንስ አማራጮች ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸውም ቀርበው በአገርና በአኅጉር ደረጃ ውይይት እንደሚደረግባቸው ተጠቅሷል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የምዕራብ አፍሪካ አገሮች የኢኮኖሚ ትብብር (ኢኮዋስ)፣  የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ትብብር (ሳዴክ) እንዲሁም የአፍሪካ ንግድና ልማት ባንክን ጨምሮ ሌሎችም አኅጉር አቀፍ ተቋማት ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ኩባንያዎች የገንዘብ ተቋማትና ሌሎችም በኮንፈረንሱ የሚዳሰሱ የንግድና የገንዘብ ፖሊሲዎችና አፈጻጸሞች ላይ የሚነሱ ሐሳቦችን ለመከታተልና ተሞክሮዎችን ለመቅሰም ዕድል እንደሚያገኙ ያስታወቀው ምክር ቤቱ፣ የኢትዮጵያ የንግድና የፋይናንስ ዘርፍ ተዋንያን  እንዲሁም በተጓዳኝ የንግድ ሥራዎች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አካላት በኮንፍረንሱ እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች