ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል በአዲስ የተቋቋመው የሪፐብሊክ የጥበቃ ኃይል፣ ታኅሣሥ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በተገኙበት በአዲስ አበባና በዳርቻዋ ወታደራዊ ትርዒቱን አቅርቧል፡፡ እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ፣ የሪፐብሊክ የጥበቃ ኃይል በከፍተኛ ሥልጣን ላይ ያሉትን ኃላፊዎች ከማንኛውም ሥጋትና ጥቃቶች ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆነውን ማንኛውንም ዘዴ መጠቀም ዋነኛ ተግባሩ ነው። ባለፉት ስድስት ወራት ይህ ኃይል ራሱን በሠለጠኑ የደኅንነት ባለሙያዎችና በተገቢው መንገድ ተግባሩን ለማከናወን የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን እያደራጀና ሥልጠናዎች እያደረገ መቆየቱን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘነው መረጃ ያመላክታል። ፎቶዎቹ የኩነቱን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -
ፌርማታ ፅሁፎች
ትኩስ ፅሁፎች
- Advertisement -
- Advertisement -