‹‹በኮምፒውተር፣ በላፕቶፕ፣ በታብ፣ በሞባይል፣ በየትምና መቼም ለማንበብና ለመቀባበል ይቻል ዘንድ መጻሕፍትን በሲዲ ዳግም ጀባ ብያለሁ፤›› የሚለው ኤልያስ ማሞ ‹‹ሪፖርቱ እና ሌሎች›› በሚል ርዕስ የ23 ወጎች መድበሉን በሲዲ ያሳተመው መሰንበቻውን ነው፡፡ ደራሲው ቀደም ሲል እንጦሽ፣ አባወራው እና ሌሎች ወጎች፤ እንዲሁም ውቤከረሜላ፣ ጉጉት እና እርካታ ረዥም ልብ ወለዶችን ለአንባቢያን አቅርቧል፡፡