በኢትዮጵያ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ገፀ ባህርይ ፈጥሮ፣ ‹‹የብርሃን ናፍቆት› በሚል ርዕስ በ2001 ዓ.ም. ረዥም ልብ ወለድ ያስነበበው በብዕር ስሙ መሰንበቻውን አቤል እ. ‹‹ሰውዬው›› በሚል ርዕስ አዲስ መጽሐፍ አውጥቷል፡፡ መጽሐፉ ስለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የመሪነት ዝንባሌ፣ ክህሎት፣ ውሳኔ አሰጣጥ፣ የሥራ ባህል፣ አካባቢ ጥበቃና ማኅበራዊ ኃላፊነት፣ የሥራ ተግባቦትና አጠቃላይ የሥራ ፍልስፍና ካየውና ከተረዳው አንፃር የዳሰሰበት መሆኑን ገልጿል፡፡ በመጽሐፉ ርዕስ በታካይነት ‹‹መደመር ወይስ መደናገር የዳይሬክተሩ ድብቅ ማስታወሻ›› ይዟል፡፡