13ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀንን አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ ኅዳር 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በተካሄደው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት የቡና ጠጡ ባህላዊ መስተንግዶ የተከናወነ ሲሆን በዚህም ከአሥር ሺሕ ሰው በላይ ታድሞበታል ተብሎ ተገምቷል፡፡ ለቡና ሥነ ሥርዓቱም 76 ድንኳኖች ተጥለዋል፡፡ ክብረ ቀኑ እስከ ቅዳሜ ኅዳር 29 ቀን ድረስ በተለያዩ ሲምፖዚየሞችና ኮንሰርቶች ተካሂዷል፡፡ የተለያዩ ብሔረሰቦችን የሚወክሉ ኢትዮጵያውያን በባህል ልብስ አሸብርቀው ያከበሩት የዘንድሮው የብሔረሰቦች ቀን መሪ ቃል ‹‹በብዝኃነት የደመቀ ኢትዮጵያዊ አንድነት›› የሚል ነው፡፡ ፎቶዎቹ የበዓሉን የመክፈቻ ቀን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡