አዲስ አበባ የሚገኘው የባንግላዴሽ ኤምባሲ ‹‹የባንግላዴሽ ገጽታዎች›› በሚል መሪ ቃል የአገሪቱን ባህልና ትውፊት የሚያስተዋውቅ በባህላዊና ዘመናዊ ሙዚቃ የታጀበ መሰናዶውን ኅዳር 14 ቀን 2011 ዓ.ም. በጌት ፋም ሆቴል አቅርቦ ነበር፡፡ ባህር ተሻግረው የብስ አቋርጠው ከአገራቸው የመጡ የባህል ሙዚቃ ጓዶችና ታዋቂ ድምፃውያን የዝግጅቱ አካል ነበሩ፡፡ በሥነ በዓሉ ላይ በኢትዮጵያ የባንግላዴሽ አምባሳደር ሚስተር ሞኒሩል ኢዝላምን ጨምሮ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሹማምንትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተውበታል፡፡ ፎቶዎቹ የነበረውን ሥነ በዓል ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡