Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአሠልጣኝ ጃማ ኤደን መታሰር ሥጋት ፈጥሯል

የአሠልጣኝ ጃማ ኤደን መታሰር ሥጋት ፈጥሯል

ቀን:

ሰውዬው እንግሊዛዊው ጃማ ኤደን ይባላሉ፡፡ በአትሌቲክሱ ዘርፍ የመካከለኛ ርቀት አሠልጣኝ ናቸው፡፡ እሳቸው ካሠለጠኗቸው አትሌቶች መካከል የወቅቱ የረዥም ርቀት አሸናፊው ሞ ፋራህ እንዲሁም ኢትዮጵያዊቷ ገንዘቤ ዲባባ ይጠቀሳሉ፡፡ ነገር ግን ከትናንት በስቲያ ሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. በስፔን የፀረ አበረታች ንጥረ ነገር ግብረ ኃይል ድንገት ካረፉበት ሆቴል በቁጥር ሥር አውሏቸዋል የሚለው ዜና ተደምጧል፡፡ ይህም በርካታ የመነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳዮችን አስነስቷል፡፡ በኢትዮጵያም ይፋ ያልወጡ ሥጋቶችና ድንጋጤዎች ተፈጥረዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በጃማ ኤደን ከሚሠለጥኑት አንዷ የዓለም ሻምፒዮናዋ ገንዘቤ ዲባባ መሆኗ ነው፡፡

የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) የፀረ አበረታች ንጥረ ነገር ኤጀንሲ (ዋዳ) ቀደም ሲል ይፋ ባደረገው ዘገባው፣ በአትሌቲክሱ የበርካታ አገሮች አትሌቶች በአበረታች ንጥረ ነገር መጠርጠራቸው ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ከስድስት የማያንሱ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት አትሌቶችም የተከለከሉ አበረታች ንጥረ ነገር ተጠቅመዋል በሚል ጊዜያዊ ዕገዳ ተጥሎባቸው ጉዳያቸው በመጣራት ላይ ይገኛል፡፡

የዓለም አቀፉ የፀረ አበረታች ንጥረ ነገር ኤጀንሲ ክትትልና ቁጥጥር አንዴ ቀዘቀዝ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሞቅ እያለ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ባለፈው ሰኞ ከስፔን እንደተሰማው ዘገባ ከሆነ፣ ጉዳዩን እንደገና ውስብስብና አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡ እንደሚታወቀው በትውልድ ሶማሊያዊ በዜግነት እንግሊዛዊ መሆናቸው የሚታወቁት ጃማ ኤደን በስፔን የካታላን ከተማ በሆነችው ሳቤዴል በአይኤኤኤፍና በስፔን የፀረ አበረታች ንጥረ ነገር ግብረ ኃይል በቁጥጥር ሥር ውለው ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢና ውስብስብ እንዲሆን ያደረገው ደግሞ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከተለያዩ አገሮች የተሰባሰቡ ከ26 በላይ አትሌቶች በከተማዋ መገኘታቸው መሆኑም ተነግሯል፡፡

ለጊዜው ስሙ ባልተጠቀሰው ሞሮካዊ ፊዚዮቴራፒስት ክፍል ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋቸው የተነገረላቸው እንግሊዛዊው ጃማ ኤደን የኳታር፣ የጂቡቲንና የሶማሊያ አትሌቶች የመካለኛ ርቀት አሠልጣኝ ሆነው ለዓመታት መቆየታቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡

ስለተፈጠረው ሁኔታ ሪፖርተር ከገንዘቤ ዲባባና በዙሪያዋ ካሉ ሰዎች መረጃ ለማግኘት ሞክሮ ሊሳካ አልቻለም፡፡ እንደ ጃማ ኤደን ሁሉ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ በማሠልጠን ላይ የሚገኙ በርካታ ሙያተኞች ከሪፖርተር በጉዳዩ ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ  በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ከሚሰሙት በስተቀር የተጨበጠ ነገር እንደሌላቸው ነው ያስረዱት፡፡ ይሁንና አበረታች ንጥረ ነገር በተለይ ለአትሌቲክሱ ዘርፍ አደገኛ እየሆነ መምጣቱን በይፋ ያወጀው ዋዳ ምርመራውንና ክትትሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት አስታውቋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹ከኦነግ ሸኔ ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት አለን›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ

መንግሥት ከ‹‹ኦነግ ሸኔ››ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት...

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...