Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየኢትዮጵያ ስካውቶች በዓለም ስካውት ጃምቡሬ ሊሳተፉ ነው

የኢትዮጵያ ስካውቶች በዓለም ስካውት ጃምቡሬ ሊሳተፉ ነው

ቀን:

ከአራት ካምፖች አንዱ በአክሱም ተሰይሟል

ዘንድሮ በአሜሪካ በሚካሄደው የዓለም ስካውት ጃምቡሬ የኢትዮጵያ ስካውቶች ሊካፈሉ ነው፡፡ በአሜሪካ ምዕራብ ቨርጂኒያ ግዛት በመጪው ሐምሌ 2011 ዓ.ም በሚካሄው ዓመታዊ ትርዒት ከ169 አገሮች ከ40 ሺሕ በላይ ስካውቶች ይሳተፉበታል፡፡

የኢትዮጵያ ስካውት ማኅበር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሻምበል ጳውሎስ ወልደ ገብርኤል እንደገለጹት፣ በቨርጂኒያ በሚካሄደው ጃምቡሬ ስድስት ዐበይት ሠፈሮችን ያካተቱ አራት ንዑሳን ካምፖች ይኖራሉ፡፡ አንደኛው ካምፕ የተሰየመው በአክሱም ሲሆን ሌሎቹ በህንድ ታጅ ማሃል በሚገኘው አግራ ፎርት እየተባለ በሚጠራው ምሽግ፣ በግሪክ አክሮፖሊስ፣ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ እስያዋ አንኮር ተሰይመዋል፡፡

- Advertisement -

አሜሪካ፣ ካናዳና ሜክሲኮ በጋራ በሚያዘጋጁት በዚሁ ጃምቡሬ ላይ የካምፖቹ ስያሜ የተሰየመው የመንግሥታቱ የባህል ድርጅት ዩኔስኮ፣ የዓለም ድንቅ ቅርስ ብሎ ከመዘገባቸው አስደናቂ ቅርሶች ውስጥ መርጦ መሆኑን ሻምበል ጳውሎስ አስረድተዋል፡፡

የስካውቶቹ ስብስብ የየአገራቸውን ባህል በመግለጽና በማስተዋወቅ ከፍተኛ የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ከአሁን በፊትም በስዊድን፣ በጃፓን፣ በአይቮሪኮስት፣ በቡሩንዲና በኬንያ በተከናወኑት 21ኛ፣ 22ኛ እና 23ኛ ጃምቡሬዎችና የወጣቶች ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ሹሩባ አሠራር፣ የልዩ ልዩ ብሔረሰቦች ዘፈን፣ ውዝዋዜ፣ የአልባሳትና የቡና አፈላል ሥርዓት በኢትዮጵያ ስካውቶች ቀርቦ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ስካውት ማኅበር በአንጎላ በ2004 ዓ.ም. በተካሄደው 15ኛው የአፍሪካ ስካውት ጉባዔ ወቅት የአፍሪካ ስካውቶችን እንቅስቃሴ እንዲወክል በአፍሪካ ኅብረት በቋሚነት ተመርጧል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ስካውት ማኅበር የመጀመርያውን፣ ሁለተኛውንና ሦስተኛውን አገር አቀፍ ጃምቡሬ በጃንሜዳና በቀድሞ አውሮፕላን ማረፊያ፣ አራተኛውን በቢሾፍቱ፣ አምስተኛውን በትግራይና ስድስተኛውን በድሬዳዋ ከተማ ማካሄዱ አይዘነጋም፡፡

የሰባተኛውን አገር አቀፍ ጀምቡሬ በአዲስ አበባ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ፣ ይህም ጃምቡሬ የኢትዮጵያ ስካውት የ100ኛ ዓመት መታሰቢያ በመሆኑ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው ሻምበል ጳውሎስ ተናግረዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ስካውት ማኅበር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የስካውት ትምህርት በኢትዮጵያ የተጀመረው የቀድሞው ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በ1911 ዓ.ም. አልጋ ወራሽ በነበሩበት ጊዜ ሲሆን፣ ንጉሠ ነገሥት ከሆኑ በኋላ የማኅበሩ የበላይ ጠባቂ ሆነው በልጃቸው ልዑል መኮንን ኃይለ ሥላሴ እንዲመራ መደረጉ ይታወሳል፡፡

ማኅበሩ በርካታ ወጣቶችን በትምህርት ቤቶች በማሰባሰብ እንቅስቃሴውን በመላ አገሪቱ በማስፋፋት ላይ እያለ በ1928 ዓ.ም. ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት የስካውት እንቅስቃሴ ተገትቷል፡፡ በወቅቱ 120 የሚሆኑ ወጣት ስካውቶች የአገራቸውን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከአርበኞች ጎን በመቆም የተሳተፉ ሲሆን፣ አብዛኞቹ የሕይወት መስዋዕትነት መክፈላቸውና ቀሪዎቹም ከአርበኞች ጋር በድል መመለሳቸውን ታሪክ ያወሳል፡፡

ማኅበሩ በ1942 ዓ.ም. በንጉሠ ነገሥቱ ፈቃድና ትዕዛዝ በመንግሥት ማስታወቂያ ቁጥር 135/42 ሐምሌ 21 ቀን 1942 ዓ.ም. በነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 11 ‹‹የኢትዮጵያ ቦይ ስካውት ማኅበር ቻርተር›› በሚል ሕጋዊ ሰውነት ተሰጥቶት ሲቋቋም በ1961 ዓ.ም. ደግሞ በዓለም ስካውት ድርጅት መመዝገቡ ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...