Thursday, March 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየቤተሰብ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

የቤተሰብ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

በሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ አጠቃላይ ዓመታዊ የዋና ዋና ሰብሎች ምርታማነትን ወደ 406 ሚሊዮን ኩንታል ለማሳደግና የምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ በማረጋገጥ፣ ድህነትን ለማስወገድ እንደሚሠራ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ዴኤታ ካባ ኡርጌሳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ 

ዶ/ር ካባ እንዳሉት፣ ይህን ለማሳካት የግብርና ኤክስቴንሽን ፓኬጅን በመከለስና በመፈተሽ አዳዲስ በምርምር የተገኙ አሠራሮች፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በየደረጃው በሚገኙ አርብቶና አርሶ አደሮች ዘንድ ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ ነው፡፡

አሁን የተደረሰበትን 21 ኩንታል ከሔክታር የማግኘት ሥራም በዋና ዋና ሰብሎች ላይ በማከናወን በ2012 ዓ.ም. በሁለተኛው የልማት ዕቅዱ መጨረሻ 29 ኩንታል በሔክታር ለማድረስ እየተሠራ መሆኑን አክለዋል፡፡

የዓለም የምግብ ቀን በአዳማ ከተማ በሎሜ ወረዳ ‹‹የዛሬ ጥረታችን ለነገ ስኬታችን በ2030 ረሃብን እናጥፋ›› በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በዓለም ለ38ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ36ኛ ጊዜ ሲከበር የዓለም አቀፍ የምግብና የእርሻ ድርጅት፣ አጋር ድርጅቶችና ሌሎች ባለድርሻዎች ተገኝተዋል፡፡

የዓለም የምግብ ቀን ሲከበር እየቀነሰ የነበረው ረሃብ መልሶ ማገርሸቱን ተገልጿል፡፡ ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ በ2030 ረሃብን ዜሮ ለማድረግ የተቀመጠውን አጀንዳ ስኬት ሥጋት ላይ ጥሎታል፡፡ በኢትዮጵያ ደረጃ አጀንዳውን እናሳካዋለን ያሉት ዶ/ር ካባ ይህ የሚሆነው ግን እንዲሁ በማለም ብቻ ሳይሆን በመሥራት ነው ሲሉ አክለዋል፡፡   

የኦሮሚያ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በ2030 ረሃብን ከዓለም ለማጥፋት የታቀደውን ክልሉ ያሳካዋል ወይ ተብሎ ሪፖርተር ላቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹የአገራችን የግብርና ፖሊሲ ይህንን ለማሳካት የሚያስችል ሲሆን፣ እንደ ክልል ደግሞ ይህንን ፖሊሲ በማስፈጸምና የራሱንም ፕሮግራም በመቅረፅ እየሠራንበት በመሆኑ ዕቅዱን እናሳካለን የሚል ግምት አለኝ፤›› ብለዋል፡፡

በዕለቱ በመስክ ጉብኝት ከተካሄደባቸው አንዱ በአዳማ ከተማ በሎሜ ወረዳ የሚገኘው የሎሜ ገበሬዎች ማኅበር ነው፡፡ ይህ ማኅበር ምርጥ የስንዴ ዘርን በማምረት የሚያሠራጭ ሲሆን፣ በተጓዳኝ ደግሞ ስንዴን በማምረት፣ በመፍጨት ዱቄቱን ለገበያ እያቀረበ ይገኛል፡፡ በቅርቡም የዳቦ ምርት ማምረትና ማከፋፈል መጀመሩን ከስንዴ በተጨማሪ ጤፍን ጨምሮ ለገበያ እንደሚያቀርብና ምርቱን ከሚያቀርብባቸው አንዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡   

መንግሥት ይህንን ጥረት ለማሳካት በሁለተኛው ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዘመን አሁን የደረስንበትን የዋና ዋና ሰብሎች ምርት በመጨመር በዕቅዱ መጨረሻ ዘመን 406 ሚሊዮን ኩንታል በማድረስና ግብርናችን ወደ ኢንዱስትሪ የሚያደርገውን ሽግግር ለማሳካት ነው፡፡

በ2011 ዓ.ም. የምርት ዘመንም በምርት ዘመን 375 ሚሊዮን ኩንታል ለማግኘት ያቀደ ሲሆን፣ ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ በሁሉም በየአገሪቱ ባሉ አነስተኛ አርሶ አደሮች መሬት ከአራት ሚሊዮን ሔክታር በላይ በመስኖ በማልማት በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየሠራን እንገኛለን፡፡ ይህንንም ለማሳካት ከፍተኛ የቴክኖሎጂና የፋይናንስ ዕገዛ እንፈልጋለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...