Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትአራተኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ሻምፒዮናን በምልከታ

አራተኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ሻምፒዮናን በምልከታ

ቀን:

ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ያላትን ስምና ዝና እንዲሁም ውጤት ለማስቀጠል ሲባል በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የተለያዩ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማድረግ ቅድመ ማጣሪያ ውድድሮችን ማድረግ የተለመደ ተግባር ሆኖ ቆይቷል፡፡

በየዓመቱ ከሚደረጉ ቅድመ ማጣሪያ ውድድሮች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ይጠቀሳል፡፡ በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ ላይ ተተኪ አትሌቶችን ለማግኘት ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች አትሌቶች ክለቦቻቸውን በመወከል ያላቸውን አቅም ማሳየት ከጀመሩ አራተኛ ዓመታቸውን ይዘዋል፡፡ ከግንቦት 25 እስከ 29 ቀን 2008 ዓ.ም. በተደረገው 4ኛው የወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ክለቦች፣ የከተማ አስተዳደሮች፣ ክልሎችና የተለያዩ ተቋማት አሉን ብለው ያቀረቡትን አትሌቶች መመልከት ቢቻልም ሁሌም የሚስተዋለው የዕድሜ ችግር ካለፉት ዓመታት የተሻለ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ መቅረፍ ግን የተቻለ አይመስልም፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለተሳታፊ ክለቦች የውድድር ዕድልን ለመፍጠር ተፎካካሪነትን ለማዳበር እንዲሁም በዋነኝነት እ.ኤ.አ. ከጁላይ 22 እስከ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ለሚደረገው 16ኛው የዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚወክሉ አትሌቶችን ለመምረጥ ያነገበ ነበር፡፡

- Advertisement -

በፖላንድ ለሚካሄደው የዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ ከ400 ሜትር እስከ 10,000 ሜትር ርቀት እንዲሁም የሜዳ ተግባር ላይ የሚካፈሉ አትሌቶችን ሲመርጥ ሰንብቷል፡፡

በአራተኛው ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለሁሉም ተሳታፊ ክለቦች፣ የከተማ አስተዳደር እንዲሁም ክልሎች በየትኛው የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ የሚገልጽ ትክክለኛ መረጃ እንዲቀርቡ ፋክስ ቀደም ብሎ መላኩን አሠልጣኞች ተናግረዋል፡፡

የክለብ አስተዳደሮች ካስመረጧቸውና ካስመዘገቡዋቸው አትሌቶች 85 የዕድሜ ማጣራት ተደርጎባቸው መቀነሳቸውን ፌዴሬሽኑ ውድድሩ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ አብራርተዋል፡፡

ምንም እንኳ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የዕድሜ ማጣራት አድርጌያለሁ ቢልም በተለይ በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም የተገኘው ተመልካች በሚመለከተው የተወዳዳሪ የፊት ገጽታ ጥያቄ ሊያነሳ ነበር፡፡ የአምስት ሺሕ ሜትር ርቀት አትሌት የሆነችውና በሦስተኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተወዳድራ ውጤት ያልቀናት የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዴሚዋ ይታይሽ መኰንን ‹‹ባለፈው ዓመት ተመጣጣኝ የሆነ ዕድሜ ባለመኖሩ በውድድሩ ውጤት ማምጣት ከብዶኛል፡፡ በዘንድሮ ግን ትንሽ መሻሻል ስላለው ሦስተኛ ሆኜ ማጠናቀቅ ችያለሁ፤›› በማለት ተናግራለች፡፡ ከ20 ዓመት በታች የምትገኘው ይታይሽ ቀድሞ ብዙ ውድድር ላይ ተወዳድረው ልምድ ያላቸውና በትክክለኛ ዕድሜ ያልተወዳደሩ አትሌቶች ልምድ ያላቸውና ዕድል እያበላሹ ነው ባይ ነች፡፡

በዘንድሮ ውድድር ለሁለተኛ ጊዜ የተሳተፈውና በአትሌቲክሱ ብዙም ሲሳተፉ የማይስተዋሉት የሲዳማ ቡና ክለብ በተለይ በሜዳ ተግባር ላይ አበረታች ውጤት  ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ የሲዳማ ቡና ዋና አሠልጣኝ ጌታሁን ታደሰ የውድድሩን ጥሩነት ገልጸው፣ አምና ዘጠኝ አትሌቶችን በመያዙ የተሳተፉ ሲሆን፣ ዘንድሮ 47 ተሳታፊ አትሌቶችን በማምጣት በዕድሜ ጉዳይ ሰባቱ እንደተቀነሰባቸው አስረድተዋል፡፡ እንደ አሠልጣኙ አስተያየት ከሆነ የዕድሜ ማጣራቱ ሰባት ልጆች ቢቀነሱብንም ግን ይበልጥ በሌሎችም ላይ ማጣራት ማድረግ ነበረበት ብለዋል፡፡

የበቆጂ አካዴሚና የወጣቶችና ስፖርት አሠልጣኝ የሆኑት የቀነኒሳ በቀለ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ፋጡማ ሮባ፣ ጥሩነሽ ዲባባና ገንዘቤ ዲባባን እንዲሁም ሌሎች አትሌቶችን ያፈሩት አሠልጣኝ ስንታየሁ እሸቱ ለታዳጊዎች ቅድሚያ መስጠት የሁሉም ክለቦች ኃላፊነት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በአራተኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና 1094 አትሌቶች ተሳታፊ ሲሆኑ፣ የክለቦች ተሳትፎም ቀደም ብሎ ከነበረው ቁጥር ጨምሮ 46 ደርሰዋል፡፡ በተጨማሪም ከፍተኛ ፉክክር የተስተዋለበት እንደሆነ የተሳታፊ ክለብ አሠልጣኞች አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል 16 አትሌቶች ላይ ዶፒንግ ምርመራ ተደርጎላቸዋል፡፡ በምርመራ ሒደቱም የደምና የሽንት በተመረጡ አትሌቶች ላይ ተደርጓል፡፡ የዶፒንግ ምርመራ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሰለሞን መዓዛ እንደገለጹት፣ ከሆነ ምርመራውን በተገቢው መንገድ ማድረግ እንደቻሉ አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የውድድርና ተሳትፎ ባለሙያ አቶ አሰፋ በቀለ፣ በአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ አንደኛና ሁለተኛ በመውጣት አሸናፊ የሆኑ አትሌቶች ሆቴል ገብተው ልምምዳቸውን ይጀምራሉ፡፡ በተጨማሪ በዕድሜ ጉዳይ ላይ ለተነሳው ጥያቄ አሸናፊ ሆነው በተመረጡ አትሌቶች ላይ ድጋሚ ማጣራት ተደርጎ አስፈላጊውን ዝግጅት ይጀመራል ብለዋል፡፡

በአራተኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ውድድር፣ በሴት ኦሮሚያ ክልል 166 ነጥብ አንደኛ፣ አማራ ክልል 94 እንዲሁም ጥሩነሽ ዲባባ አካዴሚ በ88 ነጥብ አሸናፊ ሲሆኑ፣ በወንድ ኦሮሚያ 181 ነጥብ፣ ሲዳማ ቡና 105 እንዲሁም አማራ በ84 ነጥብ በቅደም ተከተላቸው አሸናፊ በመሆን አጠናቀዋል፡፡

በአጠቃላይ ወንድና ሴት ኦሮሚያ በ347 ነጥብ አንደኛ፣ አማራ 178 እንዲሁም ጥሩነሽ ዲባባ በ150 ነጥብ ሲቀመጡ ኦሮሚያ ሁሉም ዘርፍ ሦስት ዋንጫ በማንሳት  አሸናፊ ሆነዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...