Monday, June 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየወጣቶችን ፍላጎት የሰነቀው የመቐለ ስፖርት ማዕከል

የወጣቶችን ፍላጎት የሰነቀው የመቐለ ስፖርት ማዕከል

ቀን:

በመቐለ ከተማ ቀበሌ 17 ውስጥ የሚገኘው የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ማዕከል፣ ከተለመደው አሠራር ወጣ ባለ መልኩ ወጣቶች የቋንቋ ክህሎታቸውንና ዕውቀታቸውን እንዲያዳብሩ፣ እንዲሁም የኤችአይቪና የኮምፒውተር ትምህርትን በተመለከተ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ በቀን ከ300 እስከ 400 በሚሳተፉበት በዚህ ስፖርት ማዕከል በአሜሪካውያን ባለሙያዎች ከ14 ዓመት በላይ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ የወጣቶችን ስፖርት ሚኒስቴር ባደረገው ዓመታዊ የስፖርት ግምገማ ላይም በክልሉ ካሉ የስፖርት ማዕከሎች ቀዳሚ ሥፍራ መያዝ ችሏል፡፡ የወጣት ማዕከሉን እንቅስቃሴ በተመለከተ ዳዊት ቶሎሳ ሥራ አስኪያጁን ጆን ኒይካምፕን አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- በመቐለ የወጣቶች ስፖርት ማዕከል ሥራ እንዴት ጀመራችሁ?

ጆን፡- ኢትዮጵያ የመጣነው ከአሥራ አራት ዓመታት በፊት ነበር፡፡ እኛ የተሰማራንበት  ድርጅትም ከወጣቶችና ስፖርት እንዲሁም በጤና ጉዳይ ላይ ይሠራ ስለነበር ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ መ<span style=”font-size:12.0pt;mso-bidi-font-size:11.0pt;line-height:200%;font-family: &quot;Ge” ez-1=”” numbers”,”sans-serif”‘=””>Gለ በመጓዝ፣ ከታዳጊ ወጣቶች ጋር በተያያዘ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ተወያየን፡፡ በዚህም መሠረት ቀደም ብለን ሥራውን ለመጀመር የወጣት ማዕከሎችን ስንመለከት ምንም እንኳ አገልግሎት የሚሰጠው ማዘውተሪያ ሥፍራ ቢኖርም በአግባቡ ግን አገልግሎት እየሰጠ ስላልሆነ በዚያ ዙሪያ መሥራት እንዳለብን ተመካክረን የፕሮጀክት ዕቅድ አስገብተን ፈቃድ አገኘን፡፡ ከዚያም ቀበሌ 17 የሚገኘውን የስፖርት ማዕከል በመረከብና የተለያዩ ማቴሪያሎችን በማስገባት አገልግሎት መስጠት ጀመርን፡፡

- Advertisement -

ሪፖርተር፡- በዚህ ማዕከል ምን ዓይነት አገልግሎቶች ይሰጣሉ? ምን ያህል ተጠቃሚዎችስ አሉ?

ጆን፡- በማዕከሉ በአጠቃላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ይጎበኙናል፡፡ ለምሳሌ በቀን ከ300 እስከ 400 ተገልጋይ ይስተናገዳል፡፡ አንዳንዴም እስከ 1,000 ወጣቶች የተለያዩ የስፖርት ዓይነቶችን ለማግኘት ይጎበኙናል፡፡ በቤት ውስጥና ከቤት ውጭ በሚሰጡ አገልግሎቶች ተጠቃሚ ናቸው፡፡ በዚህ መሠረት አንድ ወጣት ወደ ስፖርት ማዕከሉ ሲመጣ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ የእግር ኳስ፣ ከቤት ውጭ የሚሰጥ አገልግሎት ሲያገኝ፣ በቤት ውስጥ ደግሞ የጠረጴዛ ቴኒስ፣ ባድሜንተን፣ ዳርትና ዳማ የመሳሰሉ ጨዋታዎችን ማግኘት ይችላል፡፡ በተጨማሪ ወደ ማዕከሉ የሚመጡት ታዳጊ ወጣቶች የእርስ በርስ ትውውቅ እንዲኖራቸውና ባህላቸውን እንዲያዳብሩ ተሰብስበው ሐሳብ የሚለዋወጡበት መድረክ ተፈጥሮላቸዋል፡፡ የእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚማሩበት የትምህርት ክፍለ ጊዜ፣ የሙዚቃ፣ ኮምፒውተር፣ ቴኳንዶ፣ ሰርከስና ድራማ እንዲሁም የቤተ መጻሕፍት አገልግሎቶችን ያገኛሉ፡፡

ሪፖርተር፡- በፊት ከነበረው ማዕከል ጋር ሲተያይ እናንተ መሥራት ከጀመራችሁ በኋላ ምን አዲስ ነገር ጨምረናል ብላችሁ ታስባላችሁ?

ጆን፡- እኛ በማዕከሉ ታዳጊ ወጣቶችን ተቀብለን መሥራት ከመጀመራችን በፊት ልጆቹ ማዘውተሪያ ቦታ በማጣታቸው በተለያዩ አልባሌ ቦታዎች ነበር የሚውሉት፡፡ በአግባቡ የሚፈልጉትን ነገር ማግኘት አይችሉም ነበር፡፡ ከመዝናኛ ቦታ ይልቅ መጠጥ የበዛባቸው ቦታዎች የሚያዘወትሩ ነበሩ፡፡ እንዲሁም ታዳጊዎች ከትምህርት ቤት መልስ ብዙም የሚያሳልፉበት ቦታ አልነበረም፡፡ አሁን ግን ይኼን የስፖርት ማዕከል ይመርጡታል፡፡ ምክንያቱም የፈለጉትን ስፖርት መርጠው ይጫወታሉ፡፡ ጓደኞቻቸውን ማግኘት ይችላሉ፡፡ ቋንቋ መማር ይችላሉ፡፡ ስለዚህ መጥፎ ቦታ ወይም ወደ መጠጥ ሥፍራዎች አይሄዱም ማለት ነው፡፡ በእውነቱ ከሆነ ልጆቹ ይኼንን ቦታ ይመርጡታል፡፡ በማዕከሉ ያለፉ ልጆችም በተለያየ መንገድ ተጠቃሚ ሲሆኑ አይተናል፡፡ ለምሳሌ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የገቡ ወጣቶች ነበሩን፡፡ የትምህርት ጊዜያቸውን ጨርሰው ሲመጡ ቤተሰቦቻቸውን ከጠየቁ በኋላ ሁለተኛ ቤታቸው ይኼ ማዕከል ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በማዕከሉ ተጠቃሚ ከሆኑ ታዳጊዎችና ወጣቶች መካከል በተለያዩ ውድድሮች ላይ የመካፈል ዕድል ያጋጠመው አለ?

ጆን፡- በተለያዩ አገር አቀፍ እንዲሁም የወረዳ ውድድሮች ላይ የመሳተፍ ዕድል አለ፡፡ ለምሳሌ በጠረጴዛ ቴኒስ ብዙ ጊዜ ከተማውን በመወከል ስንወዳደር ወጣቶች ከመዝናናት ባሻገር ውድድርም እንዲካፈሉ ዕድል ይመቻችላቸዋል፡፡ በተጨማሪም የእኛ ዋና ዓላማ ስፖርቶችን በኢትዮጵያ ማስፋፋት ነው፡፡ ስለዚህም ውድድሮች ላይ እንዲሳተፉ አጋጣሚዎቹን ለወጣቶቹ በማመቻቸት ተፎካካሪ አትሌቶች መፍጠር ግባችን ነው፡፡ በተጨማሪ ደግሞ የዚህ ማዕከል መኖር ብቃታቸውን በየጊዜው እንዲያሻሽሉና ውድድሮች ላይ እንዲሳተፉ ያደርጋቸዋል፡፡ ወደዚህ ማዕከል የሚመጡትን ተጠቃሚዎች በባለሙያዎች ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ በክልል በሚደረጉ ውድድሮች ላይ የእኛን ታዳጊዎች ወደፊት ትልቅ ቦታ እንደሚደርሱ በተሳተፍንባቸው ውድድሮች ላይ ማየት ችለናል፡፡

ሪፖርተር፡- ወጣቶቹ የእናንተን የስፖርት ማዕከል የሚመረጡበት ምክንያት ምንድነው ብለው ያስባሉ?

ጆን፡- ዋነኛ ምክንያቱ እኛ ድርጅቱን ስናቋቁም ለትርፍ አለመሆኑ ነው፡፡ ያንን ዓላማ አድርገን ቢሆን ኖሮ ተጠቃሚዎቻችን ጥቂት ይሆኑ ነበር፡፡ ምክንያቱም ክፍያውን  ጥቂቶቹ ብቻ የመክፈል አቅም ስለሚኖራቸው፡፡ በአካባቢው ላሉት የማዕከሉ ተጠቃሚዎች ፕሮግራሞችን በመቅረፅ በፈለጉት ስፖርት ላይ እንዲሳተፉ ዕድል ፈጥሮላቸዋል፡፡ ለተገልጋዮቹ ምቹ ሁኔታን ብቻ መፍጠር ሳይሆን፣ በየቀኑ እነሱን እየተከታተልን የተመቻቸ አካባቢ በማደላደልና ከኅብረተሰቡ ጋር እንዴት መገናኘት እንዳለባቸው፣ እንዲሁም ችግርን በምን ዓይነት መንገድ መፍታት እንደሚኖርባቸው እንዲማሩ ይደረጋል፡፡ ስለዚህ ወጣቶቹን በስፖርቱ ማሳተፍ ብቻ ሳይሆን ፍላጎታቸውን ማዳመጥ፣ መንከባከብና ቅድሚያ ለእነሱ መስጠትን ያካተተ ነው፡፡ ስለዚህ እነሱ እኛን የመረጡበት ምክንያት ይኼ ይመስለኛል፡፡

ሪፖርተር፡- ባለፉት 14 ዓመታት ውስጥ ምን ዓይነት ድጋፍ ተደርጎላቸው ያውቃል? በተለይ ከኢትዮጵያ መንግሥት?

ጆን፡- የሚያስፈልጉ የስፖርት ማቴሪያሎችን እኛው ነን ያሟላነው፡፡ እነዚህን ማቴሪያሎችን የምናሟላው፣ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች በምናገኘው ገንዘብ ነው፡፡ ይሁን እንጂ መንግሥት ለሌሎች የስፖርትና የወጣቶች ማዕከላት እንደዚህ አስፈላጊውን ሁሉ ማሟላት አለበት፡፡ በተጨማሪም ኅብረተሰቡና ወላጆችም ኃላፊነት ሊወስዱ ይገባል፡፡ በዚህ ማዕከል መሥራት ከጀመርን ምንም ዓይነት የማቴሪያል ድጋፍ ተደርጎልን አያውቅም፡፡

ሪፖርተር፡- እስካሁን ባሳለፋችኋቸው ጊዜያት ውስጥ ያጋጠማችሁ ችግርና ከመንግሥት ጋር ያላችሁ ግንኙነት ምን ይመስላል?

ጆን፡- ከመንግሥት ጋር ጥሩ የሚባል ቅርርብ አለን፡፡ ለምንጠየቃቸው ነገሮች ድጋፍ ያደርጉልናል፡፡ ግን ከውጭ አገር የእኛን ማዕከል መርዳት የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡም ፍላጎታቸውን በተግባር ያሳያሉ፡፡ ማዕከሉ ላይ የሚገኙት ፈቃደኞች የተለያዩ ልምዳቸውን ለወጣቶቹ ያካፍላሉ፡፡ በተጨማሪም የቋንቋ ክህሎታቸውን ማሻሻል ይችላሉ፡፡ እነዚህ ፈቃደኛዎች ግን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በነፃነት ለመንቀሳቀስና ለመሥራት ሲቸገሩ ይስተዋላል፡፡ በዚህም ምክንያት የበለጠ መሥራት የነበረብንን ሥራ መሥራት አልቻልንም፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...