Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበፓርኪንሰን ዙሪያ ያጠነጠኑት ሁለቱ መጻሕፍት

በፓርኪንሰን ዙሪያ ያጠነጠኑት ሁለቱ መጻሕፍት

ቀን:

‹‹በፓርኪንሰን ላይ የሚነሱ 100 ጥያቄዎችና መልሶቻቸው›› እንዲሁም የፓርኪንሰን ፔሸንትስ ሳፖርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ›› በሚሉ ርዕሶች የታተሙ ሁለት የአማርኛ መጻሕፍት ባለፈው ሳምንት ለምረቃ በቅተዋል፡፡ በፓርኪንሰን ላይ የሚነሱ 100 ጥያቄዎችና መልሶቻቸው የሚለው መጽሐፍ የትርጉም ሥራ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ በችግሩ ዙሪያ ስለሚሠራው ድርጅት አመሠራረትና ዕድገት የሚያብራራ ነው፡፡

የፓርኪንሰን ፔሸንትስ ሳፖርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ክብረ ከበደ ያሳተሟቸው መጻሕፍት መታሰቢያነታቸው በመረጃ እጥረት ለሚሰቃዩ የፓርኪንሰን ሕሙማን፣ ሕመማቸው ፓርኪንሰን መሆኑን ሳያውቁ ለሚሰቃዩና ለአስታማሚ ቤተሰቦቻቸው ነው፡፡

አብርሃም ሌበርማን (ኤምዲ) ከማርሺያ ማክሰል ጋር በመተባበር ‹‹100 ኩዌሽችንስ ኤንድ አንሰርስ አባውት ፓርኪንሰን ዲሲስ›› በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛ ያሳተመውና ወደ አማርኛ የተተረጎመው መጽሐፍ እንደሚያስነብበው፣ ፓርኪንሰን ሁሉንም አገሮች በእኩል ደረጃ ያጠቃል፡፡ ልዩነቱ የፓርኪንሰን ተጠቂዎች በበለፀጉ አገሮች ተመዝግበው ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ መታወቁና በማደግ ላይ ባሉ አገሮች የሚገኙት ግን አለመታወቃቸው ነው፡፡

- Advertisement -

በሰሜን አሜሪካ ብቻ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የፓርኪንሰን ሕሙማን ይኖራሉ፡፡ በዓለም ደግሞ በዓመት በአማካይ 50,000 ሰዎች በፓርኪንሰን ይጠቃሉ፡፡ ዕድሜ ሲጨምርም በፓርኪንሰን የመያዝ ዕድል ይጨምራል፡፡

የፓርኪንሰን ሕመምን ለማወቅ ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ድረስ ይወስዳል፡፡ አንዳንዴም እስከ አሥር ዓመት ሊቆይ ይችላል፡፡

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በእርሻ የሚተዳደሩና ገጠር የሚኖሩ ሰዎች በሌላ የሥራ መስክ ከሚተዳደሩ ሰዎች በበለጠ በፓርኪንሰን የመጠቃት ዝንባሌ እንዳሳዩ መጽሐፉ አመላክቷል፡፡ ምክንያቱም ለእርሻው አስፈላጊ ከሆኑ ፀረ ዓረምና ፀረ ተባይ ኬሚካሎች ጋር ግንኙነት ወይም ንኪኪ ስለሚኖራቸው ነው፡፡

ፓርኪንሰን በቫይረስ አማካይነት ሊከሰት ይችል ይሆናል የሚል ግምት መኖሩን መጽሐፉ ጠቁሞ፣ በአንድ ወቅት (1908 እስከ 1909) ተከስቶ የነበረና ለአሥር ዓመታት የቀጠለው ስሊፒንግ ሲክነስ (Sleeping Sickness) የተያዙ ሰዎች የፓርኪንሰን ሕሙማን ሆነው እንደተገኙ አስረድቷል፡፡ የረጋ ደም ለማስወገድ ቀዶ ጥገና ሕክምና የተደረገላቸው ሰዎችም በፓርኪንሰን ሊያዙ ይችላሉ፡፡

በቦክስ ዓለም የነበሩ አሁንም በሙሉ ጤንነት ላይ የሚገኙ ቢኖሩም ቦክስ ፓርኪንሰን ሊያስከትል እንደሚችል የተገመተው ቦክሰኛው መሐመድ ዓሊ (ካሽየስክሌ) በፓርኪንሰን ከተያዘ በኋላ ነው፡፡ በርካታ ቦክሰኞችም በተለያየ መጠን በንግግር ችሎታ መቀነስ፣ በሰውነት መጫጫን ወይም በመገታተር፣ በመርሳትና ወይም በሌላ የሥነ ልቦና ቀውስ ችግሮች ይሰቃያሉ፡፡

ለፓርኪንሰን የተለያዩ መድኃኒቶች ከመፈልሰፋቸው እ.ኤ.አ. ከ1959 በፊት በፓርኪንሰን የታመመ ሰው በአማካይ የሚኖርበት ዕድሜ በፓርኪንሰን ከተያዘ ጀምሮ ከአምስት እስከ 15 ዓመታት ነበር፡፡ ፓርኪንሰን በራሱ ገዳይ ስላልሆነ ሕመምተኞች የሚሞቱትም በተለያየ ምክንያት ነው፡፡ በፓርኪንሰን የተያዘ ሰው እንቅስቃሴው እየተገደበ ነው፡፡ ጊዜው እየረዘመ ሲሄድ መንቀሳቀሱ ይበልጥ ይቀንሳል፡፡ በዚህ ምክንያት አንዳንዶቹ ለመመገብ ይቸገራሉ፡፡ ተጠንቅቀው ቢመገቡ እንኳን ይታነቃሉ ወይም ትንታ ይይዛቸዋል፡፡ 

በፓርኪንሰን ሕመም መጠቃትን የሚያሳዩ የመጀመርያ ምልክቶች አራት ሲሆኑ፣ አንድ ሰው ፓርኪንሰን ሕመምተኛ ነው ለማለት ከአራቱ ቢያንስ ሁለት ምልክቶች መታየት ይኖርባቸዋል፡፡ እነርሱም መንቀጥቀጥና የሰውነት መጫጫን ወይም መገታተሮች ናቸው፡፡ መንቀጥቀጥ የሚከሰተው በአብዛኛው ጊዜ በእጆች ላይ ሲሆን በተወሰኑት ደግሞ በእግር ወይም በአገጭ ሊከሰት ይችላል፡፡ የሰውነት መጫጫን ደግሞ በጡንቻ መድረቅ ወይም አለመፍታታት ሊከሰት ይችላል፡፡ ለመራመድ አለመቻልና ሲቆሙ ዘርግቶ ለመቆም መቸገር የፓርኪንሰን ምልክት ነው፡፡

ለመናገር፣ ለመራመድ፣ አለማሽተት ወይም የማሽተት ችግሮች፣ እንዲሁም የሕመም ስሜት መሰማት (ስቃይ) በጣም ትንንሽና ያልተስተካከለ የእጅ ጽሑፍና ገላጭ ያልሆነ ስሜት አልባ የፊት ገጽታ በፓርኪንሰን መጠቃትን የሚያሳዩ ሌሎች ምልክቶች እንደሆኑ መጽሐፉ ይተርካል፡፡ 

በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ወ/ሮ ክብረ እንደገለጹት፣ የፓርኪንሰን ፔሸንትስ ሳፖርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ያተኮረውን መጽሐፍ ለማሳተም ያነሳሳቸው የኦርጋናይዜሽኑ ታሪክ ከእሳቸው ታሪክ የተቆራኘ በመሆኑ ነው፡፡ የትርጉሙን ሥራ ያከናወኑት ደግሞ በኢትዮጵያ በአማርኛም ሆነ በሌሎች የአገሪቱ ቋንቋዎች ስለ ፓርኪንሰን የተጻፈ ነገር ስለሌለ ነው፡፡ ይህም የፓርኪንሰን ሕሙማን ሆኑ ሌሎች ስለፓርኪንሰን ማወቅ የሚፈልጉ ሰዎች የሚያነቡት እንዲኖራቸው በማሰብ ነው፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...