Tuesday, February 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊቀይ መስቀል ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልገኛል አለ

ቀይ መስቀል ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልገኛል አለ

ቀን:

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከምሥራቅ ወለጋ 75 ሺሕ፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከማሼ ዞን 15 ሺሕ፣ እንዲሁም ከጌድኦ የተፈናቀሉ በአጠቃላይ ከ90 ሺሕ በላይ ሰዎችን ለማቋቋም ከ523 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልገኛል አለ፡፡

የማኅበሩ የሀብት ልማት ማሰባሰብ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድአወክ አበዜ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በእነዚህ አካባቢዎች ለተፈናቀሉት ከ90 ሺሕ በላይ ዜጎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ሰብዓዊ ዕርዳታዎችን ለማቅረብ እንዲያስችለው ከኅብረተሰቡና ከለጋሽ ድርጅቶች ዕርዳታ እንዲጠይቅ መገደዱን ገልጸዋል፡፡

በተያያዘ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አንድ አምቡላንስ ከእነ ሙሉ መገልገያው ለማኅበሩ ለመስጠት ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከ400 በላይ አምቡላንሶች ሲኖሩት አንዱ አምቡላንስም በዓመት ከአምስት ሺሕ በላይ ለሆኑ ሰዎች አገልግሎት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቤተክህነት ባቀረበችው የይግባኝ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለዕሮብ ተቀጠረ

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሀገወጥ ነው በተባለው አዲሱ ሲኖዶስና...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...