Sunday, May 19, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁለተኛው ዙር ዘመቻ ያላግባብ ተይዘዋል ያላቸውን ካባዎችን መንጠቅ ጀመረ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ባካሄደው ሁለተኛ ዙር ዘመቻ፣ በሕገወጥ መንገድ ተይዘዋል ያላቸውን የድንጋይ ካባዎች መንጠቅ ጀመረ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በተለይ በስድስቱ የማስፋፊያ ቦታዎች ባለቤት በሆኑ ክፍላተ ከተሞች የሚገኙ ሰፋፊ የድንጋይ ማውጪያ ካባዎች ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ካባዎቸ በበላይነት የሚተዳደሩት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ሥር ነው፡፡

ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ሥልጣን በተረከቡበት ወቅት፣ የድንጋይ ማውጫ ካባዎች ያሉበት ሁኔታ ኦዲት እንዲደረግ ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር፡፡

በዚህ መሠረት ኮሚቴ ተቋቁሞ በተካሄደው ጥናት፣ ያላግባብ የተያዙ በአሥር ሺዎች የሚቆጠር ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ቦታዎች ተለይተዋል፡፡

እነዚህ ቦታዎች የተያዙት በመንግሥት ተቋማት በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፣ በአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፣ የመሠረተ ልማት ተቋማት በሰጡት ድጋፍ በግል ኮንትራክተሮች ነው ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ዓለሚ አሰፋ (ኢንጂነር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ያላግባብ የተያዙ የድንጋይ ማውጫ ካባዎች ተለይተው ዕርምጃ እየተወሰደ ነው፡፡

‹‹አስተደደሩ በድጋሚ የሚረከባቸውን ካባዎች ለወጣቶች ያስተላልፋል፤›› በማለት ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀጣዩን የአስተዳደሩ የትኩረት አቅጣጫ አመላክተዋል፡፡

በዚህ መሠረት ምክትል ከንቲባ ታከለ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ለዓመታት በሕገወጥ መንገድ ተይዞ የቆየ 38 ሺሕ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ድንጋይ ማውጫ ካባ እንዲነጠቅ በማድረግ ለወጣቶች እንዲሰጥ ወስነዋል፡፡ በ28 ማኅበራት የተደራጁ 1,040 ወጣቶች ቦታውን መረከባቸው ታውቋል፡፡

‹‹ለወጣቶች የሥራ አጥነት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ተመሳሳይ ዕርምጃ በሁሉም ክፍላተ ከተሞች ይወሰዳል፤›› ሲሉ ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ በመጀመርያው ዙር ዘመቻ ለዓመታት ታጥረው በተቀመጡ ቦታዎችና በሕገወጥ መንገድ በተያዙ የቀበሌ ቤቶች ላይ ዕርምጃ መውሰዱ አይዘነጋም፡፡

በሁለተኛው ዙር ደግሞ ባለቤት አልባ ሕንፃዎች፣ ሼዶች፣ ማምረቻዎች፣ ሆቴሎችና የድንጋይ ካባዎች ኦዲት ከተደረገ በኋላ ዕርምጃ እንዲወሰድ መመርያ ተሰጥቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች