Tuesday, May 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየሕዝብ ቅሬታዎችን እንዲፈታ የተቋቋመው ጽሕፈት ቤት ደንብና መመርያ ሊሻሻል ነው

የሕዝብ ቅሬታዎችን እንዲፈታ የተቋቋመው ጽሕፈት ቤት ደንብና መመርያ ሊሻሻል ነው

ቀን:

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትን ጭምር እያጥለቀለቀ የሚገኘውን የሕዝብ አቤቱታ በተገቢው መንገድ እንዲፈታ የተቋቋመው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገድ ጽሕፈት ቤትን የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ፣ ደንብና መመርያ የሚያሻሽል ኮሚቴ ተቋቋመ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ጽሕፈት ቤት፣ በተለይም መሬትና መሬት ነክ ይዞታዎችን የተመለከቱ በርካታ ቅሬታዎች ቢቀርቡለትም፣ በተገቢው መንገድ እየፈታ ባለመሆኑ ቅሬታዎች ጎልተው መሰማት ጀምረዋል፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታት ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የሰው ኃይል ለውጥ ያደረጉ ሲሆን፣ በቅርቡ የከተማው ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ዋና ዳይሬክተር የነበሩትን አቶ መኮንን አምባዬ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አድርገው ሹመዋል፡፡

- Advertisement -

አቶ መኮንን ጽሕፈት ቤቱን ከመረመሩ በኋላ በተሟላ መንገድ የኅብረተሰቡን ቅሬታ ለመፍታት አቅም ሊኖረው ይገባል የሚል አቋም ላይ በመድረሱ፣ ከአስተዳደሩ ጋር በመነጋገር ጽሕፈት ቤቱ የሚገለገልባቸው ደንብና መመርያዎች ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡

አቶ መኮንን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ደንብና መመርያው ላይ ማሻሻያ ተደርጎ ለካቢኔ ይቀርባል፡፡ ካቢኔው ሲያፀድቀውም ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሆኖ የሚሾም አመራር ትልልቅ አገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ እንዳያተኩርና በስትራቴጂክና በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጊዜውን እንዳይጠቀም ከሚያደርጉ ጉዳዮች መካከል፣ የሕዝብ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው፡፡

በተለይ ከመሬትና መሬት ነክ፣ እንዲሁም ከመኖሪያ ቤቶች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ በርካታ ቅሬታዎች ይቀርባሉ፡፡

ቀደም ሲል በነበረው አደረጃጀት ጽሕፈት ቤቱ የሚቀርቡለትን ቅሬታዎች ራሱ ከመፍታት ይልቅ ወደ ሌሎች አስፈጻሚዎች መልሶ ይመራቸዋል፡፡ በዚህ ችግር ምክንያት ነዋሪዎች ከአስተዳደሩ መዋቅሮች አልፈው የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጽሕፈት ቤት እያንኳኩ ነው፡፡ እንዲሻሻሉ እየተደረጉ ያሉ ደንብና መመርያዎች፣ ጽሕፈት ቤቱ ራሱ ጣልቃ በመግባት ችግሮችን የመፍታት አቅም እንዲላበስ ያደርገዋል ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...