Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊካርታ የመከነባቸውን ሰፋፊ ቦታዎች የጎበኙ ታዋቂ ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳርን ውሳኔ...

ካርታ የመከነባቸውን ሰፋፊ ቦታዎች የጎበኙ ታዋቂ ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳርን ውሳኔ ደገፉ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰሞኑን የሊዝ ውላቸው ተቋርጦ ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ ያደረጋቸውን ሰፋፊ መሬቶች ያስጎበኛቸው ታዋቂ ሰዎች፣ የአስተዳደሩን ውሳኔ ደገፉ፡፡

ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከኪነ ጥበብ፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ከስፖርትና ከመሳሰሉት የተውጣጡ ታዋቂ ሰዎች ሚድሮክ አጥሮ ያቆያቸውን የፒያሳና የሸራተን ማስፊፊያ፣ ሜክሲኮ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የሚገኙ ቦታዎችን፣ ቦሌ መድኃኔዓለም ከቀነኒሳ ሆቴል ጀርባ በዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን፣ እንዲሁም አራት ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ በግለሰቦች የተያዙ ቦታዎች ጎብኝተዋል፡፡

ጎብኚዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሰደውን ዕርምጃ በማድነቅ፣ የሕዝብ ሀብት የሆነው መሬት ያለ ግንባታ ለዓመታት ታጥሮ መቀመጡ አግባብ አይደለም ብለዋል፡፡

- Advertisement -

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሥር የሚገኘው የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጥላሁን በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት፣ እንገነባለን በማለት መሬት ለዓመታት አጥረው የያዙ አካላት ለኅብረተሰቡ ያልተጨበጠ ተስፋ ሲሰጡ ነበር ብለዋል፡፡ ‹‹ያልተጨበጠ ተስፋ ደግሞ አገሪቱን ወደ ኋላ ጎትቷታል፤›› በማለት የተናገሩት አቶ ተስፋዬ፣ ‹‹አስተዳደሩ ታጥረው ለዓመታት የተያዙትን ቦታዎች የግድ ማስመለስ ስለነበረበት ይኼንን ትልቅ ውሳኔ አስተላልፏል፤›› ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ መስከረም 12 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ሚድሮክን ጨምሮ በግል፣ በመንግሥትና በዲፕሎማቲክ ተቋማት ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ 154 ቦታዎች የሊዝ ውል ተቋርጦ ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

አይነኬ የተባሉት ቦታዎች በድምሩ 412.68 ሔክታር ስፋት ያላቸው ሲሆን፣ ቦታዎቹ ለተሻለ ልማት እንደሚውሉ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ለጎብኚዎቹ ገልጸዋል፡፡

ከ2003 ዓ.ም. በኋላ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ኦዲት ሲያካሂድ የመጀመርያው ነው፡፡ ከስምንት ዓመታት በፊት የተካሄደው የመሬት ኦዲት በሪል ስቴት ኩባንያዎች ላይ ብቻ ያነጣጠረ ሲሆን፣ ምክትል ከንቲባ ታከለ (ኢንጂነር) ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የተካሄደው የመሬት ኦዲት ግን ሁሉንም ዘርፎች የዳሰሰ መሆኑ ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...