Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር በአዲስ ተሿሚ ሊተኩ ነው

በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር በአዲስ ተሿሚ ሊተኩ ነው

ቀን:

በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ (አምባሳደር)፣ በአቶ ሱሌይማን ደደፎ (አምባሳደር) እንዲተኩ መመደባቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡

ባለፉት 27 ዓመታት በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ተልዕኮ ውስጥ ቆይታ የነበራቸው አቶ ብርሃነ ላለፉት ሁለት ዓመታት ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት እያገለገሉ ከሚገኙበት ቻይና እንዲመለሱ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መጠራታቸው ታውቋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአምባሳደር ብርሃነ በተጨማሪ በብራዚል፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ በካናዳና በሌሎች አገሮች የሚገኙ አምባሳደሮች ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ጥሪ ማድረጉን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዚህ መሠረት ተተኪ አምባሳደሮች እየተመደቡ መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ አቶ ሱሌይማን በቻይና እንደሚመደቡ ጠቁመዋል፡፡ አቶ ሱሌይማን በናይጄሪያ፣ በጂቡቲና በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ሠርተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ጉዳዮች ዳይሬክተር በመሆን እያገለገሉ ነው፡፡

በሌላ በኩል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ ያለው አባተ፣ በብራዚል ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው እንደሚመደቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አቶ ያለው ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር በመሆን ከጥቂት ሳምንታት በፊት፣ በፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ሹመት ከተሰጣቸው ስምንት የቀድሞ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት መካከል አንዱ ናቸው፡፡

አቶ ያለው የቀድሞ የማዕድን ሚኒስቴር የነበሩትንና በአሁኑ ወቅት በብራዚል ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው እየሠሩት የሚገኙትን ወ/ሮ ስንቅነሽ እጅጉን በመተካት ነው፣ በብራዚል የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተመደቡት፡፡

በሌላ በኩል በግብፅ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ታዬ አፅቀ ሥላሴን፣ አቶ አዛናው ታደሰ እንዲተኳቸው መመደባቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

አቶ አዛናው በዲፕሎማሲው ዘርፍ የረዥም ዓመታት ልምድ ያካበቱ መሆናቸውን፣ ለዓመታት በጄኔቫ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ተቋማት ጉዳዮች  ዳይሬክተር በመሆን እያገለገሉ ነው፡፡

በተመሳሳይ ዜና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ በታንዛኒያ ኤምባሲ እንደሚከፍት ለማወቅ ተችሏል፡፡ አዲስ በሚከፈተው በዚህ ኤምባሲ በቅርቡ የአምባሳደርነት ሹመት ያገኙት አቶ ዮናስ ዮሴፍ እንደሚመደቡ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በደቡብ ኮሪያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ሽፈራው ጃርሶ ወደ ሱዳን መዘዋወራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...