Tuesday, May 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናበአንበሶች ሞት ምክንያት የማዕከሉ ዳይሬክተር ከሥልጣን ተነሱ

በአንበሶች ሞት ምክንያት የማዕከሉ ዳይሬክተር ከሥልጣን ተነሱ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ሐሙስ ነሐሴ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ስድስት ኪሎ የሚገኘውን አንበሳ ግቢ ከጎበኙ በኋላ፣ ዋና ዳይሬክተሩን ሙሴ ክፍሎም (ዶ/ር) ከሥልጣን አሰናበቱ፡፡

የምክትል ከንቲባው የጉብኝት ምክንያት ስድስት ኪሎ የሚገኙ ነዋሪዎች ከቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥልጣን ዘመን ጀምሮ፣ ከአንድ ዓመት በላይ ያቀረቡት ተደጋጋሚ ቅሬታ በመጨረሻ ተቀባይነት በማግኘቱ ነው፡፡

የአካባቢ ነዋሪዎች ቅሬታ አንበሳ ግቢ ለዕድሳት በሚል ምክንያት ከተዘጋ በኋላ፣ አንበሶቹን ጨምሮ የተለያዩ የዱር አንስሳት ህልውና አደጋ ውስጥ መግባቱ ነው፡፡

- Advertisement -

ከቅሬታ አቅራቢዎች መካከል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር አቶ አበባው አያሌው ይገኙበታል፡፡ አቶ አበባው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአንድ ዓመት ከስምንት ወራት ውስጥ የስድስት አንበሶች ሕይወት አልፏል፡፡ ከሞቱት አንበሶች መካከል ጎፈር፣ በሻዱና ወርቁ ተጠቃሾች ሲሆኑ፣ ጠንክር የሚባለው አንበሳ የሞተው በእርጅና ምክንያት ነው፡፡

አቶ አበባው እንደሚሉት አንበሶቹ የሞቱት በምግብ ዕጦት፣ በሕክምናና በእንክብካቤ ማነስ ነው፡፡ ‹‹አራት የአንበሳ ጎጆዎች ውስጥ አንበሶች የሉም፡፡ በሕይወት ያሉትም ቢሆኑ እጅግ ከመክሳታቸው የተነሳ ህልውናቸው አደጋ ላይ ነው፤›› ሲሉ አቶ አበባው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹ከአንበሶቹ በተጨማሪ ውኃ የማይበቃው አባኮዳ ያለውኃ ይገኛል፡፡ ሰማይ የማይበቃው ንሥር አሞራ በጠባብ ሥፍራ ውስጥ ይገኛል፡፡ ጭላዳ ዝንጀሮ ጀርባው ተመላልጦ ሞቱን እየጠበቀ ነው፡፡ ይህ ለምን ይሆናል?›› ሲሉ አቶ አበባው ይጠይቃሉ፡፡ ይህ የአቶ አበባው ጥያቄ የስድስት ኪሎና የአካባቢው ነዋሪዎች ጥያቄ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ምክትል ከንቲባው በአካል ተገኝተው እንስሳቱ ያሉበትን አደገኛ ሁኔታ ከተመለከቱና ከአካባቢው ማኅበረሰብ የተነሳውን ቅሬታ ካዳመጡ በኋላ መመርያ ሰጥተዋል፡፡

ምክትል ከንቲባው ማዕከሉን እየመሩ የሚገኙት ሙሴ (ዶ/ር) ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ከመወሰናቸው በተጨማሪ፣ በእንስሳቱ አስፈላጊው ነገር ሁሉ እንዲቀርብላቸው አዘዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ቦሌ በሚገኘው ፒኮክ መናፈሻ የተጀመረው ግንባታ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ መመርያ ሰጥተዋል፡፡

ከኃላፊነታቸው የተነሱት ሙሴ (ዶ/ር) ግን የቀረበባቸውን ክስ አይቀበሉትም፡፡ እሳቸው እንደሚሉት በ2010 ዓ.ም. አንድም የሞተ አንበሳ የለም፡፡ ‹‹ከ2005 ዓ.ም. እስከ 2009 ዓ.ም ድረሰ ባሉት አራት ዓመታት የሞቱት አንበሶች ቁጥር አምስት ብቻ ነው፤›› ብለዋል፡፡

በ1940 ዓ.ም. የተቋቋመው አንበሳ ግቢ ከወለጋ፣ ከኢሊባቦራና ከሲዳማ የመጡ አንበሶችን ጨምሮ ብርቅዬ የሆኑ አእዋፋትና የዱር እንስሳት አካቶ የያዘ ነው፡፡

ነገር ግን ይህ ጥንታዊ ፓርክ በአያያዝ ጉድለት ምክንያት በርካታ ችግሮች እየገጠሙት ስለሆነ፣ የእንስሳቱ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሕይወትና በሞት መካከል የሚገኙ አንበሶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

(በ2010 ዓ.ም. በአንበሳ ግቢ የሚገኙ አንበሶች ብዛትና ፆታ)

  1. ልይሽ ተረፈ – ሴት
  2. ሰናይት ወርቁ – ሴት
  3. ሰለሞን ጠንክር – ወንድ
  4. መኮንን ተጋፋው – ወንድ
  5. ብርቅዬ ጠንክር – ሴት
  6. ቀነኒሳ ወርቁ – ወንድ
  7. ኃይሌ ወርቁ – ወንድ
  8. መሠረት ወርቁ – ሴት
  9. ጥሩነሽ ቃኘው – ሴት
  10.  እጅጋየሁ ቃኘው – ሴት
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...