Saturday, May 18, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊቤቶች ኢንተርፕራይዝ በሁለት ወራት ውስጥ 17,700 የ40/60 ቤቶችን አጠናቅቃለሁ አለ

ቤቶች ኢንተርፕራይዝ በሁለት ወራት ውስጥ 17,700 የ40/60 ቤቶችን አጠናቅቃለሁ አለ

ቀን:

መሠረታዊ የአሠራር ለውጦችን እያካሄድኩ ነው ያለው የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ፣ የ40/60 ቤቶችን እየገነቡ የሚገኙ ኮንትራክተሮች የሚያነሷቸውን ችግሮች በመፍታት በሚቀጥሉት ሁለት ወራት 17,700 ቤቶችን እንደሚያጠናቅቅ አስታወቀ፡፡

ለ40/60 ቤቶች ግንባታ መጓተት ኮንትራክተሮች ከሚያቀርቧቸው ምክንያቶች መካከል የግንባታ ግብዓቶች አቅርቦት ችግር፣ የክፍያ መዘግየትና የጉልበት ሠራተኞች እጥረት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ኢንተርፕራይዙ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት በራሱና በኮንትራክተሮች መቅረብ ያለባቸውን ግብዓቶች በመለየት ኃላፊነት መለየቱን፣ ክፍያን በሚመለከት ኮንትራክተሮች ላከናወኑት ሥራ ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ በቀጥታ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፍጥነት የሚቀበሉበት አሠራር መዘርጋቱን አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

የቀን ሠራተኞችን በሚመለከት ደግሞ ተፈጥሮ የነበረው ችግር የክፍያ ማነስ ስለነበር፣ የክፍያ ማስተካከያ የተደረገ በመሆኑ ችግሩ መፈታቱን ገልጿል፡፡

ከኢንተርፕራይዙ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በነበሩት የአሠራር ችግሮች ላይ ማስተካከያ ስለተደረገ ግንባታውን ለማጠናቀቅ በስፋት እየተሠራ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን አምባዬ ሰኞ ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የግንባታ ድርጅቶች 77 በመቶ የተጠናቀቁን የ40/60 የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ቤቶች ማጠናቀቅ በርካታ ሥራዎች እያከናወኑ ነው ብለዋል፡፡

አቶ መኮንን እንደገለጹት፣ የ40/60 ቤቶች ቁጥራቸው 17,700 ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አራት ሺሕ ያህሉ የንግድ ቤቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ መኖሪያ ቤቶች ናቸው፡፡

ግንባታቸውን እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ በማጠናቀቅ መኖሪያ ቤቶችን በዕጣ፣ ንግድ ቤቶቹን ደግሞ በጨረታ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ታቅዷል፡፡

ቤቶቹ ለነዋሪዎቹ ከተላለፉ በኋላ ሊፍት የሚገጠም መሆኑን፣ ለዚህም ጨረታ በሒደት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡

ኢንተርፕራይዙ በ2011 በጀት ዓመት ስምንት ሺሕ አዳዲስ ቤቶችን ለመገንባት እየተዘጋጀ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በጠቅላላው 38,200 ቤቶችን በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ