Tuesday, December 6, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊለአዲስ አበባ ከተማ ንፁህ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የውጭ ምንዛሪ ተፈቀደ

  ለአዲስ አበባ ከተማ ንፁህ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የውጭ ምንዛሪ ተፈቀደ

  ቀን:

  የአዲስ አበባ ከተማን ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ለማሻሻል ከተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች አንዱ ለሆነው ኖርዝ አያት ፋንታ ጥልቅ ውኃ ፕሮጀክት የሚያስፈልጉ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ግዥ ለመፈጸም የውጭ ምንዛሪ እንዲፈቀድ በተደጋጋሚ ቢሞከርም ምላሽ ሳያገኝ ቆይቶ፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አዲሱ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) እና አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ባካሄዱት ውይይት የውጭ ምንዛሪ መፈቀዱ ታወቀ፡፡

  ከንቲባ ታከለና የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አወቀ ኃይለ ማርያም (ኢንጂነር) ከብሔራዊ ባንክ ገዥና ከአዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ከአቶ ባጫ ጊና ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

  በተናጠል በተካሄዱት ሁለት ውይይቶች በተለይ የብሔራዊ ባንክ ገዥ የችግሩን አሳሳቢነት እንደሚረዱና የሚያስፈልገው የውጭ ምንዛሪ እንደሚመደብ የገለጹ ሲሆን፣ አቶ ባጫ በበኩላቸው ብሔራዊ ባንክ ከፈቀደ ባንካቸው የውጭ ምንዛሪውን እንደሚያቀርብ መጠቆማቸው ታውቋል፡፡

  በዚሁ መሠረት የከተማው አስተዳደር ለኖርዝ አያት ፋንታ ጥልቅ ጉድጓድ ፕሮጀክት 22 ሚሊዮን ዶላርና አምስት ሚሊዮን ዩሮ እንዲፈቀድ ጠይቆ፣ ሰኞ ነሐሴ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. የውጭ ምንዛሪው የተለቀቀ በመሆኑ ባለሥልጣኑ የሚፈልጋቸው ዕቃዎች መግዛት እንደሚችል ማረጋገጫ ማግኘቱ ተመልክቷል፡፡

  በኖርዝ አያት ፋንታ ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ ፕሮጀክት ለ700 ሺሕ ሕዝብ የሚበቃ ከ68 ሺሕ ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውኃ ተገኝቷል፣ ይህ ፕሮጀክት አስተዳደሩ በመደበው 150 ሚሊዮን ብር በሁለት ምዕራፎች ተከፍሎ፣ በአገር ውስጥና በውጭ ኮንትራክተሮች የሲቪል ሥራው ተካሂዷል፡፡

  ‹‹የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ከውጭ ለማስገባት የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በመጥፋቱ፣ በኅዳር 2010 ዓ.ም. ወደ ሥርጭት መግባት የነበረበት ፕሮጀክት መግባት ሳይችል ቀርቷል፤›› ሲሉ አቶ አወቀ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

  የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት አለመፈቀዱ የሚያስከትለውን ችግር በሚመለከት፣ የቃሊቲ ፍሳሽ ማስወገጃ ጣቢያ በተመረቀበት ወቅት በምሬት ተናግረው ነበር፡፡

  አቶ አወቀ እንዳሉት ባንኮች በተደጋጋሚ የውጭ ምንዛሪ እንዲሰጡ ቢጠየቁም ተገቢውን ትኩረት ባለመስጠታቸው ሥራው እንዲስተጓጎል ምክንያት ሆኗል፡፡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ያጋጠመ መሆኑ ቢታወቅም፣ ባንኮች መሠረታዊ ላልሆኑ ዕቃዎች ግዥ ለተለያዩ ባለሀብቶች ከመስጠት ይልቅ ከሁሉም ነገር በላይ ለሆኑ ውኃን ለመሳሰሉ መሠረታዊ ጉዳዮች መስጠት ነበረባቸው በማለት ተናግረው ነበር፡፡

  ነገር ግን ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ በፌዴራልም ሆነ በአዲስ አበባ ከተማ ወደ ሥልጣን የመጡት አዳዲስ ባለሥልጣናት ባካሄዱት ውይይት፣ በመጨረሻ የባለሥልጣኑ የውጭ ምንዛሪ ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱን አረጋግጠዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...