Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበምሕረት አዋጁ የሚካተቱ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ማመልከት ይጠበቅባቸዋል

በምሕረት አዋጁ የሚካተቱ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ማመልከት ይጠበቅባቸዋል

ቀን:

ዓርብ ሐምሌ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ለአስቸኳይ ስብሰባ የተጠራው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው ለተያዙ፣ ለተፈረደባቸውና ሳይያዙ በውጭ አገር በስደት ለሚኖሩ ግለሰቦችና የሕግ ሰውነት ላላቸው አካላት ምሕረት እንዲደረግላቸው አወጀ፡፡ ምሕረት እንዲሰጥ አዋጁ በዘረዘራቸው የወንጀሎች ድርጊቶች ተጠቃሚ መሆን የሚችሉ፣ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ማመልከት እንደሚጠበቅባቸው ተደንግጓል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ወንጀሎች የታሳተፉና የሚፈለጉ ሰዎችን ለአገራዊ መግባባትና ፖለቲካዊ መረጋጋት ሲባል ምሕረት እንዲደረግላቸው በመወሰን፣ በሰኔ ወር 2010 ዓ.ም. መጨረሻ ሳምንት ረቂቅ የምሕረት አዋጅ ልኮ የነበረ ቢሆንም፣ የፓርላማው የሥራ ጊዜ ሰኔ 30 ቀን አብቅቶ ለእረፍት በመበተኑ ነው ለአስቸኳይ ስብሰባ ከእረፍት እንዲመለስ የተጠራው፡፡

ለአስቸኳይ ስብሰባ የተሰየመው ፓርላማ የቀረበውን ምሕረት መስጫ ረቂቅ ሕግ በመመልከት በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ውስጥ ለተሳተፉ ሰዎች ምሕረት በመስጠት በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ማስፈን፣ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ማድረግና አጋጥሞ በነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች የተሳተፉ ሰዎችን ድርጊት ለመሰረዝ ምሕረት መስጠቱ አስፈላጊነት ላይ ተግባብቷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዚህ መሠረት ከግንቦት 30 ቀን 2010 .. በፊት የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶችን፣ ማለትም በሕገ መንግሥቱና በሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ላይ የሚደረግ ወንጀል፣ የሕገ መንግሥታዊ ሥልጣንን ተግባራዊነት ማሰናከል፣ የጦር መሣሪያ ይዞ ማመፅ፣ የእርስ በርስ ጦርነት ማስነሳት፣ የአገሪቱን የፖለቲካና የግዛት አንድነት መንካት፣ የአገር መከላከያ ኃይልን መጉዳት፣ የአገር ክህደት የፈጸሙና ከመከላከያ ሠራዊት የመኮብለል ወንጀል የፈጸሙ የምሕረቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

 በተጨማሪም ከጠላት ጋር በመተባበር የሐሰት ወሬዎች ማውራትና ማነሳሳት፣ ለፀረ ሽብርተኝነት የወጣ አዋጅን መተላለፍና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን የመተላለፍ ወንጀሎችም ምሕረት እንዲሰጥባቸው ከተዘረዘሩ የወንጀል ድርጊቶች መካከል ይገኙበታል፡፡ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን በመተላለፍ የሰው ሕይወት ያጠፋ ግን የምሕረቱ ተጠቃሚ መሆን አይችልም፡፡

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 28(1) መሠረት የሰው ዘር በማጥፋት፣ ያለ ፍርድ የሞት ቅጣት ዕርምጃ በመውሰድ፣ በማስገደድ ሰውን የመሰወርና ኢሰብዓዊ ድብደባ የመፈጸም ወንጀሎች በምሕረት የማይታለፉ መሆናቸው በመደንገጉ፣ በምሕረት መስጫ አዋጁ አልተካተቱም። በዚህ መሠረት በቀረበው የምሕረት መስጫ አዋጅ የተዘረዘሩ የወንጀል ድርጊቶች የሚመለከተው በሙሉ ‹‹ወደ አገር መግባቱን፣ ወደ ማኅበረሰቡ መቀላቀሉን፣ ሰላማዊ ኑሮ ለመምራት መወሰኑንና አጠቃላይ የምሕረቱ ተጠቃሚ መሆኑን ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ወይም ለክልል የፍትሕ ቢሮዎች አዋጁ ከፀደቀበት ቀን አንስቶ ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ በአካል ወይም በተወካዩ አልያም ማናቸውንም የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅበታል፤›› በማለት ይደነግጋል።

በዚህ አዋጅ ምሕረት የተሰጠ ቢሆንም፣ ምሕረት ከተሰጠበት ወንጀል ጋር ተያይዞ በፍርድ ቤት እንዲወረስ ውሳኔ የተሰጠበት ንብረት በምሕረቱ ምክንያት እንደማይመለስ ተደንግጓል። አንድ የምክር ቤቱ አባል ድንጋጌውን ተገቢ አድርገው የተከራከሩ ሲሆን፣ ምሕረት የሚሰጠው በቀጥታ ለወንጅሉ እንጂ ፍትሐ ብሔራዊ ይዞት ላለው የንብረት ጉዳይ የማይመለከት እንደሆነ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል። በዚህ መሠረት ምሕረት መስጫ አዋጁ በአንድ ድምፀ ተአቅቦና በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል። በአዋጁ መሠረት ምሕረቱ አዋጁ ከፀደቀበት ቀን አንስቶ ተግባራዊ ይሆናል።

ለአስቸኳይ ስብሰባ የተጠራው ፓርላማ በተጨማሪ ያፀደቀው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቀረቡ ስምንትቦርድ አባላትን ነው።

የቦርዱ ሰብሰባቢ እንዲሆኑ የተሰየሙት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ሲሆኑ፣ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦች የቦርድ አባላት ተደርገዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...