Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናአዲስ አበባ በምክትል ከንቲባ ልትመራ ነው

  አዲስ አበባ በምክትል ከንቲባ ልትመራ ነው

  ቀን:

  በቅርቡ በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር መሠረት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ያልሆኑ ምክትል ከንቲባ ተሾሙ፡፡ በምክትል ከንቲባነት የተሾሙት አቶ ታከለ ኩማ (ኢንጂነር) ሲሆኑ፣ እሳቸው የከተማውን ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማን በተመተካት ኃላፊነቱን ማክሰኞ ሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ ተረክበዋል፡፡

  አቶ ታከለ የኦሮሚያ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የነበሩ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የሱሉልታ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅና የሆለታ ከተማ ከንቲባም ነበሩ፡፡ የሰበታ ከተማ ኢንዱስትሪና ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የኦሮሚያ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሠርተዋል፡፡

  በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተሻሻለው የከተማው ቻርተር መሠረት ምክትል ከንቲባ ከምክር ቤት አባላት ውጪ እንዲሾም በመወሰኑ፣ አቶ ታከለ የከተማው ምክር ቤት አባል ስላልሆኑ በውሳኔው መሠረት ምክትል ከንቲባ ሆነው የከንቲባውን ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ ተረክበው ይመራሉ፡፡

  በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ እንዲሁም የከተማው መንገዶችና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሰለሞን ኪዳኔ (ዶ/ር) ተሹመዋል፡፡ ሁለቱ ተሿሚዎች የትኞቹን ዘርፎች እንደሚመሩ አልታወቀም፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...