Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየዓለም ዋንጫ ዝግጅትና መጠናቀቂያ በፊፋ አንደበት

የዓለም ዋንጫ ዝግጅትና መጠናቀቂያ በፊፋ አንደበት

ቀን:

ለወር የዘለቀው የዘንድሮ 21ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምንጊዜም ስኬታማ ዓለም ዋንጫ ተብሎለታል፡፡ ከዝግጅት እስከ ውድድርና ያልተጠበቁ ውጤቶች ቀዳሚ ተጠቃሽ እውነታዎች የሩሲያው ዓለም ዋንጫ በበርካታ ማኅበረሰብ ዘንድ አድናቆትን አትርፏል፡፡ የመጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ሲደርስም ዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የተከናወኑ ጨዋታዎችን በተመለከተና የኃያሏ አገር ዝግጅቶችን የሚገመግመው አካል ለጋዜጠኞች የእስካሁኑ ሒደት ላይ ተመርኩዞ በሁለት ምዕራፍ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው የቀድሞ አንጋፋ ተጫዋቾች ዘጠኝ አሠልጣኞች በተከናወኑት 62 ጨዋታዎች ላይ የታዘቡትንና የተመለከቱትን ሒደት ይፋ አድርገዋል፡፡ በ21ኛው ዓለም ዋንጫ ቅድሚያ ግምት ተሰጥቷቸው ወደ አገራቸው ያቀኑት በተለይ የደቡብ አሜሪካዎቹ አገሮች ብራዚልና አርጀንቲና ትልቁን ደረጃ ይዘዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የአውሮፓ ብሔራዊ ቡድኖች ገኖ መውጣት አግራሞትን የጫረ አጋጣሚ እንደሆነ የፊፋ የቴክኒካል ገምጋሚ ቡድን ሐምሌ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. በሞስኮ ሉዚኒክ ስታዲየም በሰጡት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል፡፡

የፊፋ ቴክኒካል ግምገማ አካል የሆኑት የቀድሞ ተጫዋቾችና በአሠልጣኝነት ሙያ ውስጥ ያላለፉ እንዲሁም በዓለም ዋንጫ የረዥም ጊዜ ልምድ ያላቸው ካርሎስ አልቤርቶ ፓሬራ፣ ማርኮቫን ባስታን፣ ቡራ ሚልስታኖቪች፣ አፍሪካዊው ኢማኑኤል ኢሙኒኪና አንዲ ሮክስበርግ ነበር ማብራሪያ ሲሰጡ የነበረው፡፡

ሩሲያ በዓለም ዋንጫው በቂ ዝግጅት ያደረገችና ለሌሎችም ምሳሌ እንደምትሆን አስተያየታቸውን የሚጀምሩት ባለሙያዎቹ፣ የዘንድሮው ውድድር ከፍተኛ ፉክክር የታየበትና ለመገመትም አዳጋች እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ለዚህም ደግሞ ብሔራዊ ቡድኖች በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውና እግር ኳስ እየተለወጠ የመምጣቱ ማሳያ እንደሆነ ይጠቅሳሉ፡፡

በተለይ የዓለም ዋንጫው በአውሮፓ ብሔራዊ ቡድኖች የበላይነት መጠናቀቁ ምናልባትም የአሠልጣኝ ፔፔ ጋርዲዮላ የአጨዋወት ተፅዕኖ ወደ ዓለም ዋንጫውም መዝመቱ ሳይሆን አይቀርም የሚሉት የፊፋ የቴክኒክ ጥናት ቡድን አባል አንዲ ሮክስበርግ ናቸው፡፡ ለዚህም ማሳያነት በርካታ ተጫዋቾች በጨዋታቸው ላይ የአሠልጣኝ ፍልስፍና ተንፀባርቋል የሚል እምነት አላቸው፡፡

እንደ ባንባስተን ኦርናንድ ከሆነ ደግሞ ለብሔራዊ ቡድናቸው ውጤት እያመጡ ያሉት ተጫዋቾች በአዕምሮ በቂ ዝግጅት ያደረጉና ፈጣን የሆኑ፣ ውሳኔያቸው ላይ ጥንቃቄ የሚያደርጉና በክህሎታቸው በመተማመን አገራቸውን ለፍጻሜ ማድረስ አስችሏቸዋል ብለዋል፡፡

የፊፋ ፕሬዚዳንት ስለ ዓለም ዋንጫው

የፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ሐምሌ 6 ቀን በሰጡት መግለጫ ላይ የ21ኛው ውድድር ከጠበቁት በላይ እንደሆነ ተናግረው፣ በሩሲያው መስተንግዶ ትልቁን ድርሻ የወሰዱትን በጎ ፈቃደኞችን በማመስገን ነበር የጀመሩት፡፡ ‹‹የምንጊዜም ስኬታማ የዓለም ዋንጫ›› ሲሉም አሞካሽተዋል፡፡ ሩሲያም ከዚህ የዓለም ዋንጫ ውድድር ጎን ለጎን የእግር ኳስ መናኸሪያነቷን ታስመሰክራለች ብለዋል፡፡ በዚህ ዓለም ዋንጫ ትንሽ ትልቅ የሚባል ቡድን አለመኖሩን ያሳየ ነው ብለዋል፡፡

‹‹የ21ኛው የዓለም ዋንጫ ዝግጅት ሁለት ነገሮችን ቀይሯል፡፡ ይኼውም አንደኛው ሩሲያን ቀይሯል፡፡ ሁለተኛው የተገነቡት ስታዲየሞች ጥራትና የእግር ኳስ ደረጃ ወደ ላይ ከፍ ማድረግ አስችሏል፤›› በማለት የፊፋው ፕሬዚዳንት ኢንፋንቲኖ ይገልጻሉ፡፡ በዚህም በርካታ አገሮች ለሩሲያ የነበራቸውን አመለካከት እንዲቀይሩ አስገድዷቸዋል ባይ ናቸው፡፡ ሌላው ለዓለም ዋንጫው ውበት የሰጠና 99 ከመቶ የዳኝነቱን ሒደት ያቃለለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የ21ኛው የዓለም ዋንጫ ከሁሉም ዓለም አገሮች የተወጣጡ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተመልካቾች የታደሙበት፣ ከሦስት ቢሊዮን በላይ ሕዝብ የተመለከተውና ከሦስት ሚሊዮን በላይ ተመልካች የፊፋ ድረ ገጽ የጎበኘበት ነው፡፡

ከዚህ ባሻገር በዚህ ዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ ወጣቶች በአብዛኛው  መሳተፋቸው ማሳያው በየብሔራዊ ቡድኑ ዕድሜያቸው በአማካይ ከ20 እስከ 26 የሆኑ መሰለፋቸው ነው፡፡ ከ30 ዓመት በላይ የሆኑት ቁጥራቸው አናሳ ሆኖ ታይቷል፡፡ በተለይ የአፍሪካ ናይጄሪያና ሴኔጋል በቀጣይ ብቃት ያላቸው ተጫዋቾችን ማፍራት እንደሚችሉ ታምኗል፡፡ የፈረንሣዩ ኪሊን ማፔ፣ የእንግሊዙ ኤሪክ ሳደር አርኖልድ፣ ሙሳ ዋጌ ከሴኔጋልና ኤክለፍ ኪም ከሞሮኮ በ19 ዓመት ዕድሜ ውስጥ ተመዝግበዋል፡፡

የፊፋው ፕሬዚዳንት ስለቀጣዩ የኳታር ዓለም ዋንጫ ሲያስረዱ ፊፋ አዲስ በቀረበው የብሔራዊ ቡድኖች ቁጥር ጭማሪ መሠረት ከአዘጋጁ አገር ጋር በመወያየት ቁጥሩን ከ32 ወደ 48 ለማሳደግ የሚመክርና የሚያሳውቅ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዳዊት ቶሎሳ፣ ከሩሲያ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...