Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትባለሙያዎች ስለዓለም ዋንጫው ይናገራሉ

ባለሙያዎች ስለዓለም ዋንጫው ይናገራሉ

ቀን:

21ኛው ዓለም ዋንጫ በሩሲያ አዘጋጅነት መካሄድ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ወደ ማጠናቀቂያውም ተቃርቧል፡፡ ከሁሉም አኅጉሮች ተወጣጥተው በሩሲያ የተገኙት 32 ብሔራዊ ቡድኖችም በየጊዜው ከውድድሩ ተሸኝተው፣ በመጨረሻዎቹ አራት ተፋላሚ ቡድኖች ፍጻሜው የሚጠበቀው የዓለም ዋንጫ መርሐ ግብር ላይ እንገኛለን፡፡

የዘንድሮውን ዓለም ዋንጫ ከሌሎቹ ጊዜያት የሚለይባቸውን በርካታ ክስተቶች ሲያስተናግድ ቆይቷል፡፡ የጀርመን፣ የስፔን፣ የአርጀንቲና ከውድድሩ በጊዜ የመሰናበታቸው ጉዳይ አነጋጋሪነቱን ቀጥሏል፡፡

ይኼንን ተከትሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ በእግር ኳሱ ትልቅ ዕውቅናን ያተረፉ አንጋፋ የእግር ኳስ ጋዜጠኞችና ባለሙያዎች አስተያየታቸውንና የወደፊቱን ግመታቸውን እያስቀመጡ ነው፡፡ የአፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች ከየወድድሩ በጊዜ መሰናበት ሚስጥርና ይታዩባቸው ስለነበሩ ክፍተቶችም ሐሳባቸውን ይሰነዝራሉ፡፡

ከዚህም ባሻገር እንደ አስተናጋጇ ሩስያ ያሉት፣ ብዙም ግምት ያልተሰጣቸው አገሮች የተሻለ ውጤት ማስመዝገባቸውም ያልተጠበቀ ክስተት ነበር፡፡ በዓለም ዋንጫው ፈረንሣይ፣ ብራዚል፣ ኡራጓይ፣ እንግሊዝ ቀዳሚ ግምት ካገኙት ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡

ለተመልካችም ሆነ ለእግር ኳስ ተንታኞች የትኛው አገር የውድድሩ አሸናፊ ይሆናል በሚለው ጥያቄ ላይ ደረትን ሞልቶ የሚናገር ማግኘት ከባድ ነበር፡፡ የተጠበቁትና ትልቅ ግምት የተሰጣቸው ቡድኖች ባልተጠቁት አገሮች ሲፈተኑ፣ አልፎ ተርፎም ሲሸነፉ ታይተዋል፡፡ ዕድሜው ወደ 50ዎቹ መጨረሻ የሚጠጋው አንጋፋው ጋዜጠኛ ፍራንሲስ፣ ለስፔኑ ሞንዶ ዴፖርቲቮ የስፖርት ጋዜጣ ከ15 ዓመት በላይ ጽፏል፡፡ ባለፉት አሥር የዓለም ዋንጫዎችም ለመካፈል ችሏል፡፡ እንደ ፍራንሲስ አስተያየት ከሆነ፣ እግር ኳስ በየጊዜው እየተለወጠ አሁን ያለበት ዘመን ላይ ደርሷል፡፡

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን ከውድድር መሰናበት ተከትሎ አስተያየቱን የሚሰጠው ሌላው ጋዜጠኛ ፋብዮ ሊኖል በበኩሉ፣ ሊዮኔል ሜሲ ለክለብ ሲጫወትና ለብሔራዊ ቡድን ሲጫወት ሁለት ሰው ነው በማለት ገልጾታል፡፡ ‹‹ሜሲን በብሔራዊ ቡድን ውስጥ ስትመለክተው ሌላ ሰው ነው፡፡ ስገምት ጫናው እሱ ላይ የበዛ ይመስለኛል፡፡ በማራዶና ጥላ ሥር መታየቱ ደግሞ  በራስ መተማመኑን የበለጠ ያሳጣው ይመስለኛል፤›› በማለት አስተያየቱን ለሪፖርተር ገልጿል፡፡

የጀርመን ብሔራዊ ቡድንን በተመለከተም ለግማሽ አልያም ለዕሩብ ፍጻሜ የተዘጋጁ እንጂ ለጥሎ ማለፍ የተዘጋጁ አይመስሉም ነበር በማለት ፋብዮ ሊኖል አስተያየቱን ያክላል፡፡

ስፔንን በመለያ ምት ማሸነፍ የቻለችው ሩስያ፣ በብዙዎቹ ዘንድ ክስተት ሆናለች፡፡ ለአዘጋጇ አገር በስታዲየም ተገኝቶ ድጋፍ ከመስጠት ሲያመታ የሰነበተው የሞስኮ ከተማ ነዋሪም በብሔራዊ ቡድኑ ውጤት በደስታ ሲፈነጥዝና ባልተመለደ ዕርካታ ሲምነሸነሽ ከርሟል፡፡

ስፔንን በከፍተኛ የመከላል ሥልት ከውድድር ውጪ ማድረግ የቻሉት ሩሲያዎች በሕዝባቸው ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትን ማትረፍ ችለዋል፡፡

በሴንት ፒተርስበርግ ዕለታዊ የስፖርት ጋዜጣ ላይ የሚጽፈው ማክሮቭ አሌክሳንደር፣ ሩስያ ያልተጠበቀ ውጤት ስለማስመዝገቧ በማብራራት አስተያየቱን ይጀምራል፡፡ ሌላው ቀርቶ ዝግጅቱ እንኳ እንደማይሳካለት በብዙዎች ነዋሪዎቿና በምዕራቡ ዓለም አገሮች ሲፌዝባት የነበረችው ሩስያ፣ ከጥሩ ዝግጅትና ብቃት ካለው ብሔራዊ ቡድን ጋር መገኘቷ፣ ለወደፊቱ የእግር ኳሷ ዕድገት ተስፋ የሚሰጥ አካሔድ እንዳሳየች ማክሮቭ ያምናል፡፡

በዳዊት ቶሎሳ፣ ከሩሲያ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹ከኦነግ ሸኔ ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት አለን›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ

መንግሥት ከ‹‹ኦነግ ሸኔ››ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት...

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...