Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዓመታዊ ጉባዔውን አካሄደ

ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዓመታዊ ጉባዔውን አካሄደ

ቀን:

ፌዴሬሽኖች እኩል ልንታይ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ 43ኛ መደበኛ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ያስተናገደበት መድረክ ከወትሮው በተለየ ለጠቅ ያለ ውይይትና ብርቱ ሐሳቦችን ያንሸራሸረ ነበር፡፡ በጉባዔው ከተስተናገዱ ሐሳቦች ውስጥ፣ የቶኪዮ ኦሊምፒክና የዝግጅት ምዕራፎችን እንዲሁም ተቋሙ በሆቴልና በስፖርት መሠረተ ልማት ሊያከናውናቸው ባቀደው ክንውን ዙሪያ የተመለከቱት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በአዲስ አበባ ሒልተን ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም.  በተከናወነው በዚሁ ጉባዔ ካለፈውና ከቀጣዩ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምና ዕቅድ ሪፖርት በተጨማሪ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ሊሠራቸው ይገባል ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያ በትኩረት ተነጋግሯል፡፡ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መነጋገሪያ እየሆነ በሚገኘው የአትሌቶች መወዳደሪያና ማዘውተሪያ እጥረት አኳያ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው የጎላ ድርሻ ሊኖረው እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡

ጉባዔው በሰፊው የመከረባቸውና በስፋት የተሳተፈባቸው ሐሳቦች በተከናወነበት መድረክ፣ በየአራት ዓመቱ በሚካሄደው የኦሊምፒክ ተሳትፎ ላይ ስላለው ዝግጅትና ስለሚደረገው እንቅስቃሴ ዙሪያ የተነሱት ሐሳቦች የስፖርን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚያመላክቱም ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ የኦሊምፒክ ተሳትፎ ሲቃረብ ብቻ ‹‹ሠርገኛ መጣ. . .›› ዓይነት ከሚመስል ሩጫና ወከባ ወጥቶ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ከወዲሁ አቅዶ መንቀሳቀስ እንዳለበት ጭምር ሐሳቦች ተነስተው ተንሸራሽረዋል፡፡

ከገንዘብና ቁሳቁስ ድጋፍ ጋር ተያይዞ፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች እኩል ሊታዩ እንደሚገባ እስካሁን ባለው ሁኔታ ግን፣ ከአትሌቲክስና እግር ኳስ ውጪ የቀሩት ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ትኩረት አያገኙም በሚል ከቀረቡት ቅሬታዎች ይጠቀሳሉ፡፡ የኦሊምፒክ ኮሚቴው ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር)፣ የቀረቡት ቅሬታዎችና አስተያየቶች፣ ትክክለኛና ተገቢ መሆናቸውን አመልክተው፣ ቢሆንም ተቋሙን በኃላፊነት መምራት በጀመሩ ማግስት እያንዳንዱ ብሔራዊ ፌዴሬሽን ከኦሊምፒክ ኮሚቴው  የ100 ሺሕ ብር ድጋፍ እንደተደረገለት፣ በቅድሚያ ግን ለእያንዳንዱ ፌዴሬሽን 50 ሺሕ ብር  ድጋፍ መደረጉን አስረድተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም ‹‹ገንዘቡ ለምንና እንዴት ጥቅም ላይ እንደዋለ የቀረበ ሪፖርት የለም፡፡ አሁንም ተቋማቱ በዕቅድ ክንውኖቻቸው መጠን ሪፖርቶቻቸውን ማቅረብ እስከ ቻሉ ድረስ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ንብረቶች የእያንዳንዱ ብሔራዊ ፌዴሬሽን ንብረቶች ናቸው፤›› ብለዋል፡፡

ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ለመሠረተ ልማት ግንባታ በሚል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደብረ ዘይት መንገድ በሚገኘው ሪቼ በተረከበው መሬት ላይ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ማስገንባት ይችል ዘንድ የሆቴሉን ዲዛይን ጭምር ለጉባዔው ይፋ ተደርጎ አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...