Saturday, November 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  የቱርክ ኩባንያ በትግራይ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነባ ነው

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  በቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጠይብ ኤርዶጋን ቀጥተኛ መመርያ የቱርክ ግዙፍ ኩባንያ ተርክሽ ሆልዲንግ ኤኤስ፣ በትግራይ ክልላዊ መንግሥት ግዙፍ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነባ መሆኑ ታወቀ፡፡

  የተርክሽ ሆልዲንግ ኩባንያ ኃላፊዎች ከትግራይ ክልል ከተማ ልማት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ጋር በጉዳዩ ላይ መነጋገራቸውና ለፕሮጀክቱ 300 ሔክታር መፈቀዱ ታውቋል፡፡

   የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዚዳንትና የከተማ ልማት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አዲስ ዓለም ባሌማ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከኩባንያው ኃላፊዎች ጋር ንግግር ተደርጎ የቦታ መረጣ ተካሂዷል፡፡

  የኩባንያው ኃላፊዎች የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዕቃዎችን ለማምረት ፍላጎት እንዳላቸው እንደገለጹላቸው፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡

  የቱርክ ፕሬዚዳንት ትግራይ ለሚገኘው ጥንታዊው ነጋሽ መስጊድ ልዩ ፍላጎት አላቸው ተብሏል፡፡ የኩባንያው ኃላፊዎች አዲስ አበባ በመጡበት ወቅት ከፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በጥንታዊው ነጋሽ መስጊድ ጉዳይና የኢንዱስትሪ ፓርክ በትግራይ እንዲገነባ ከፕሬዚዳንት ኤርዶጋን መመርያ እንደተሰጣቸው አንስተው መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

  ተርክሽ ሆልዲንግ በቱርክ ከሚገኙ ግዙፍ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በተለይ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ስመ ጥር መሆኑ ይነገራል፡፡

  ተርክሽ ሆልዲንግና አንድ ግዙፍ የቱርክ ባንክ ባካሄዱት ጥናት መሠረት ኢትዮጵያ ውስጥ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዕቃዎችን ለማምረት ዕምቅ ሀብት መኖሩ ስለተረጋገጠ፣ እንዲሁም ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ከዚህ በመነሳት መመርያ ስለሰጡ ኩባንያው ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

  ተርክሽ ሆልዲንግ በሴራሚክ፣ በወረቀት፣ በብረታ ብረትና በተለያዩ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ምርቱ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም እነዚህን ምርቶች ለማምረት ፍላጎት እንዳለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች