Wednesday, June 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትአራት ዓመት ጠብቀው አህጉር የሚሻገሩ ደጋፊዎች

አራት ዓመት ጠብቀው አህጉር የሚሻገሩ ደጋፊዎች

ቀን:

እንዲህ እንደ ዛሬው ቴክኖሎጂ ባልረቀቀበት ዘመን በአራት ዓመት አንዴ ብቅ የሚለውን የፊፋ ዓለም ዋንጫ መመልከት ቀላል አልነበረም፡፡

በሁሉም ዕድሜ የሚወደደው ዓለም ዋንጫ በሁሉም ሰው ልብ  ውስጥ የራሱን ትዝታ ጥሎ አልፏል፡፡ ውድድሩን በቴሌቪዥን መስኮት ለመመልከት የጎረቤቱን ቤት ደጅ ያልጠና አልነበረም፡፡ በተለይ በጊዜው ቴሌቪዥን ያላቸውን ሰዎች የማየት ፍቃድ ለማግኘት ብዙ ትዕዛዞችን መወጣት ያስፈልጋል፡፡ ምንም እንኳ በኢትዮጵያ ያለው ልምድ ከሌላው ዓለም ጋር ተነጻጻሪ ባይሆንም፣ የእግር ኳስ ፍቅር ያላቸው ሰዎች የማይረሳ ትውስታ ይኖራቸዋል፡፡

በሩሲያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ከተጀመረ ቀናት ተቆጥረዋል፡፡ ሐሙስ ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በሩሲያ ሞስኮ ሉዝኒኪ ስቴዲየም የተጀመረው ዓለም ዋንጫ አራት ዓመታትን በጉጉት ሲጠባበቁ የነበሩ ተመልካቾች ወደ ከተማዋ መግባት የጀመሩት ቀደም ብለው ነበር፡፡

አህጉር አቋርጠው ወደ ከተማዋ ከሚፈልሱት ተመልካቾች ለአዘጋጅዋ አገር ውበት ባይሰጡ ሞስኮ አዘጋጅ አገር እንኳን አትመስልም፡፡ ምንም እንኳ የሩሲያ ተመልካቾች በብሔራዊ ቡድናቸው ተስፋ የቆረጡና እግር ኳስ ለእነሱ እንዳልተፈጠረ አድርገው ቢያምኑም፣ እንግዶቻቸውን ተቀብሎ በማስተናገዱ ላይ ግን እንከን አይወጣላቸውም፡፡

ወደ ዓለም ዋንጫ ካለፉት ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች በተጨማሪም ወድድሩን ለመመልከት ሩስያ የከተሙትን ጨምሮ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተመልካቾች በከተማዋ መክተማቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በውድድሩ መቃረቢያ ወቅት የትኬት ሽያጩ መጠናቀቁን ያስታወቀው ፊፋ፤ ተጨማሪ ትኬቶች መጠየቁን አስታውቋል፡፡ ለዚህም የትኬት መሸጫ ሱቆችንና ድረ ገጾች ላይ በተመልካች ጥያቄ ተጨናንቀዋል፡፡

በውድድሩ ዋዜማ ቀደም ብሎ በሩሲያ ታላቁ ክፊሚሊን ቤተ መንግሥት አካባቢ በቀለማትና በብሔራዊ ባንዲራዎች የተዋቡ የተለያዩ አገሮች ተመልካቾች ፌሽታ የተለየ ነበር፡፡ ለአንድ ወር 64 ጨዋታዎችን በ11 ከተሞችና 11 ስታዲየሞች ላይ የሚሰናዱ ሲሆን፣ ለእነዚህም ሩሲያ ፈጣን የከተማ ቀላል ባቡሮቿን ዝግጁ አድርጋለች፡፡ በ17.1 ሚሊዮን ስኴር ኪሎ ሜትር የቆዳ ስፋት ያላት ሩሲያ 364.9 ኪሎ ሜትር ርዝመት ድረስ ባቡሮችዋ አቀላጥፈው ከቦታ ቦታ ተመልካቹንና የከተማውን ነዋሪ እንደ ፍላጎታቸው ያጓጉዛሉ፡፡

ተመልካቾችም ብሔራዊ ቡድናቸውን ለመደገፍ ባቡርን ብቸኛና ተመራጭ አድርገውታል፡፡ እ.ኤ.አ. 1935 በ11 ኪሎ ሜትር 13 ጣቢያዎችን የሚሸፍን የነበረው የከተማዋ ቀላል ባቡር፣ አሁን ቁጥሩን ወደ 214 ጣቢያዎችና 364.94 ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ ከፍ አድርጎታል፡፡

በጣቢያዎቹ መካከልም 1.7 ኪሎ ሜትር ርቀት ሲኖረው፣ ከሁለት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ይደርሳሉ፡፡ በሩሲያ ዋና ከተማ የሚገኘውና 80 ሺሕ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያለው ብሔራዊ ሉዝኒኪ ስታዲየም ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ የከተማዋን ፈጣን ባቡር ለሚጠቀሙ ተመልካቾች ያለምንም ክፍያ ከፍት ይደረጋል፡፡ አራት ዓመታትን በጉጉት ሲጠባበቁ የነበሩት የየአገሮቹ ተመልካቾችም ለዓለም ዋንጫ ትልቅ ጉጉትና ፍቅር እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡

ውድድሩን ለመታደም በሩሲያ ከታደሙት ተመልካቾች መካከል የፔሩ ደጋፊዎች ቁጥር ከ35 ሺሕ እንደሚበልጥ ተገልጿል፡፡ እነዚህ አህጉር አቋርጠው የመጡ ተመልካቾች ይኼን ዕድል ለመጠቀም በየዓመቱ ሲቆጥቡ የነበሩትን ገንዘብ በደስታ ሲያጣጥሙት ይስተዋላል፡፡ ከውጤቱ ባሻገር እየተዝናኑ፣ የአገራቸውን ባህልና ትውፊት በማሳወቅ በደስታ ያሳልፋሉ፡፡ ድልና ሽንፈት የአንድ ሳንቲም  ሁለት ገጽታ እንደሆነ  ያምናሉ፡፡

እሑድ ሰኔ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. በምድብ ስድስት ጨዋታ በሜክሲኮ 1ለ0 ሽንፈት የቀመሰችው የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮናዋ ጀርመን ውጤት ያልተጠበቀ ነበር፡፡ ትዳራቸውን ከሁለቱም አገሮች የመሠረቱት ጥንዶቹ የየራሳቸውን ትውልድ አገር ቢደግፉም ውጤቱ ግን ሜዳ ውስጥ የሚቀር እንጂ የእነሱን ደስታ የሚነካ እንዳልሆነ ይገልጻሉ፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ሪፖርተር በጨዋታ ወቅትና ከጨዋታው በኋላ ባደረገው ቅኝትና ቃለ ምልልስ የተመልካቾች ምላሽ እግር ኳስ መሸነፍና ማሸነፍ ባህሪው እንደሆነ ተመልከቷል፡፡ የ2018 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ለመታደም ወደ ሩሲያ የመጡት ተመልካቾች በተለያዩ የሩሲያ ከተሞች ተዘዋውረው ለመመልከት እስከ 1360 ኪሎ ሜትሮች ድረስ ይጓዛሉ፡፡ ለአንድ ጨዋታ በአማካይ እስከ 13,804 ብር ይከፍላሉ፡፡

በፈጣን ባቡር ለመጠቀምም ከ5,000 ሺሕ ብር ያላነሰ ክፍያን ይጠይቃቸዋል፡፡ እስከ ውድድሩ መጠናቀቂያ ድረስ ብሔራዊ ቡድናቸውን ለማበረታታት አህጉር ያቋረጡት እነዚህ ተመልካቾች ለውጪው ምንም ደንታ የላቸውም፡፡

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ሦስት ጊዜ መመልከት የቻሉት ፍራንኮ ቶማስና ጆህኪን ቲያጎ ከውጤቱ ይልቅ ተጫዋቾቻቸውን ድጋፍ በመስጠትና በሄዱበት ቦታ ሁሉ እየዞሩ መደገፍና ማበረታታት ቀዳሚ ሥራቸው እንደሆነ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ያልሆኑ ግን ውድድሩን ለመመልከት የመጡ የቻይና፣ የካናዳ፣ የኤሜሬት፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የአሜሪካና የሌሎችም አገሮች ተመልካቾች ወደ ሥፍራው አምርተዋል፡፡ ኑሮውን በካናዳ ያደረገው ዴቪድ ዊሊያም ምንም እንኳ አገሩ ለውድድሩ የማለፍ ዕድል ባታገኝም ዓለም ዋንጫ ላይ መገኘት በራሱ ትልቅ ደስታ እንደሚፈጥር ለሪፖርተር አስረድቷል፡፡

ሰባተኛ ቀኑን የያዘው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ፣ የጥሎ ማለፍ፣ የሩብ ፍጻሜና ግማሽ ፍጻሜ እንዲሁም የፍጻሜ ጨዋታዎች እስከ ሐምሌ 8 ቀን ይከናወናሉ፡፡ ጨዋታዎቹ ሲከናወኑ ደጋፊዎች የዘረኝነት ቃላትን ከተጠቀሙ ግጥሚያውን እስከ ማቋረጥ ሊደርስ እንደሚችል ፊፋ አስታውቋል፡፡

በሩሲያ ስታዲየሞች ከሚታየው የፖለቲካው ጫና የፈጠረው ብሽሽቅ በስተቀር የከፋ ነገር እንደሌለም እየተገለጸ ይገኛል፡፡ የዓለም ዋንጫ በተለይ ተመልካቾች ለብሔራዊ ቡድናቸው ያላቸው ፍቅርና እግር ኳስ በዚህ ደረጃ የማደጉ ምስጢር በኢትዮጵያ ላለው የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለትና እንቅስቃሴ ለመማር መልካምና ትልቅ አጋጣሚ እንደሚፈጥር ውድድሩን የታደሙ ኢትዮጵያውያን ተናግረዋል፡፡

በዳዊት ቶሎሳ፣ ከሞስኮ ሩሲያ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ገዳ ቢዝነስ ግሩፕ በቅርቡ ለሚጀምረው እርሻ ከ500 ሔክታር በላይ መሬት አዘጋጅቻለሁ አለ

ገዳ ስታር ቢዝነስ ግሩፕ አክሲዮን ማኅበር በቅርቡ አስጀምራለሁ ላለው...

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...