Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

​ሐውልቱ የታሪክ እምብርቱ

ትኩስ ፅሁፎች

በአዲስ አበባ ከተማ በአራዳ ጊዮርጊስ (ፒያሳ) አካባቢ በአርበኞች መንገድ አማካይ ቦታ ላይ፣ ከሰባ ዓመታት በፊት የቆመው የሰማዕቱ አርበኛ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ላለፉት ሦስት ዓመታት ከቦታው አልነበረም፡፡ በመዲናይቱ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ሳቢያ በጊዜያዊነት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ቆይቶ ነበር፡፡ የባቡሩ ፕሮጀክት በመጠናቀቁም የአቡነ ሐውልት በዕለተ ሰንበት ጥር 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቀደመው ስፍራው በክብር ተቀምጧል፡፡ ፎቶዎቹ የአተካከሉን ሒደትና ታዳሚዎችን ሕፃንዋን ጨምሮ በከፊል ያሳያሉ፡፡ በሥነ በዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በስተቀኝ ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን የጥንታዊ ኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት፣ ኢንጂነር ጌታቸው ማሕተመ ሥላሴ፣ ልቡል ራስ መንገሻ ሥዩም፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ኢንጂነር ዓይሻ መሐመድ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር፣ አቶ ድሪባ ኩማ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ፣ ሐጅ ሙሐመድ አሚን ጀማል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንትና ወ/ሮ ታደለች ዳለቾ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ ይታያሉ፡፡ (ፎቶ በሔኖክ ያሬድ)

*******

‹‹የእኛ ጎልያድ››

ከቢሮ ባልደረቦቼ ጋር ሻይ ልንጠጣ ወጣ ብለን ነበር፡፡ ሻይ ቤቱ በረንዳ ሥር ነጠላ፣ ሰፊና ረጅም ቀሚስ በሹራብ ለብሰው አጭር ታኮ ጫማ ያጠለቁ በዕድሜ ሐምሳ ገደማ የምገምታቸው ሴት የበረንዳው ጠርዝ ላይ ተቀምጠው፣ ሰው እንዲሰማው ያቀዱት በማይመስል ግን ደግሞ ላስተዋለው ልብን በሚሰብር ሥልት ይንሰቀሰቃሉ፡፡ ይኼን እያዩ ቁጭ ብሎ ሻይ መጠጣት የሚቻል ባለመሆኑ ከባልደረቦቼ ጋር ጠጋ አልናቸውና ‹‹ምነው እማ… ምን ገጠምዎትና እንዲህ ያለቅሳሉ?›› ብለን ጠየቅን፡፡ ደንግጠው ቀና አሉና፤ ‹‹አይ ልጀቼ… ልረብሽ ብዬ አልነበረም… ላስቸግር ብዬ አልነበረም…›› ብለው እንደ አዲስ መንሰቅሰቅ ጀመሩ፡፡ ሴቲቱ ለልመና አልወጡም፡፡ ለታይታ አልወጡም፡፡ ብሶታቸውን የሚደብቁበት ቦታ አጥተው በአደባባይ እያነቡ ነበር፡፡ አሁን ይባስ ትኩረቴን ሳቡትና፤ ‹‹መች ተረበሽን አልን እኛ…? አላስቸገሩንም እኮ…! እንደው ሲያለቀሱ ስናይዎት ምን ሆኑ ልንል ብለን ነው…›› አልኳቸው፡፡ ‹‹ቤቴን አፈረሱብኝ… ቀበሌዎች… በሦስት ቀን ማሳሳቢያ ቤቴን እላዬ ላይ አፈረሱብኝ›› አሉን፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ አሁን አሁን በገፍ የምንሰማው እሮሮ ስለነበር መደንገጥ አልቻልንም፡፡ ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዳለው ‹‹የብዙኃኑ መሠረታዊ ፍላጎት እየቀሙ ለጥቂቶች ቅንጦት ማዋልን፤›› እየለመድነው ስለመጣን መደንገጥ አልቻልንም፡፡ እንደዚህ እንደዚህ መከራና እሮሮን ስንለምድ ያስጠላኛል፡፡ በከፋ ነገር መደንገጥ ስናቆም ይቀፈኛል፡፡ ቀስ በቀስ ሰው መሆናችን እየተነጠቅን መሆኑን አስብና ክፉኛ ይጨንቀኛል፡፡ ‹‹እውነት በሦስት ቀን ብቻ? ምትክ ቤትስ አልተሰጠዎትም እማማ?›› አላቸው ባልደረባዬ:: ‹‹በዚህ ዕድሜዬ ለምን እዋሻለሁ…? አላውቃችሁ አታውቁኝ…! በርና መስኮት የሌለው… ውኃ መብራት ያልገባለት… የት እንደሆነ እንኳን የማናውቀው … ያውም የዶሮ ቆጥ የመሰለ የቤት አፅም ነው ተሰጠኝ የሚሉህ…? ለምን እዋሻለሁ…?›› ብለው መለሱለት፡፡ እንዳስቆጣቸው ግልጽ ነበር፡፡ ‹‹አይ… እንደዛ ማለቱ አይደለም እማማ… ለምን ይዋሻሉ…? ነገሩን በደንብ ለማወቅ ነበር እኮ… ይልቅ እሰቲ ኑ… እዚህች ጋር… ሻይ እየጠጣን ያጫውቱናል ነገሩን›› ሌላኛዋ ባልደረባዬ ናት፡፡ ‹‹ወይ ልጄ! እናንተን የማጫውትበት ጊዜ የለኝም እኔ… ምን ታመጡልኛላችሁ ባጫውታችሁ…? ምን ትፈይልኛላችሁ ባማክራችሁ…? ለጋዜጠኛ ነን ባዮች ተናገርን፡፡ ዜና አሟልተውብን ዝም አሉን… ዛሬ ለደሃ ማን ይቆረቆራል…? ዛሬ ለጉልበተኛ እንጂ ለደካማ ማን ይቆማል…? ለምድነው የማጫውታችሁ… ምን ልትፈይዱልኝ …?›› አሉና ዕድሜና ሰውነታቸው ከሚፈቅደው በፈጠነ ሁኔታ ፍንጥር ብለው ተነስተው አስፋልቱን ይዘው በፍጥነት ሄዱ፡፡ ያልጠበቅነው ምላሽ በመሆኑ ለጥቂት ደቂቃዎች እርስ በርስ ተያየንና ዝም እንደተባባልን ለሻይ ተቀመጥን፡፡ ‹‹እውነታቸውን ነው›› አልኩኝ ትንሽ ቆይቼ… ‹‹እውነታቸውን ነው… ምን ልንፈይድላቸው ያወሩናል…? ከንፈር መጠጣ በሻይ ምን ያደርግላቸዋል…? እውነታቸውን ነው፤›› መልስ የሰጠኝ አልነበረም፡፡ ሦስታችንም ለተበደለ መቆም የማንችል ከንቱዎች መሆናችን፣ ጉልበተኛን ሃይ ብለን ለደካሞች ተገን መሆን የማንችል ደካሞች መሆናችን አሳዝኖን ነው መሰለኝ ሻይ እየጠጣን ድብርት ተጫጫነን፡፡ አፌ ሳይሆን አንጎሌ እያዛጋ፤ ትኩስ ሻይ ባላባረረው ረጅም ድብርቴ መሀል፤ እኔና ጓደኞቼ ጎልያድን የምንዋጋ የዚህ ዘመን ዳዊቶች ብንሆን ተመኘሁ፡፡ ለእንዲህ ያሉት ተበዳዮች ሲባል፣ የግዙፉንና አስፈሪውን ጎልያድ ግንባር በወንጭፍ መትተን የምንዘርር ዳዊቶች ብንሆን ተመኘሁ፡፡ ግን ምን ያደርጋል…! የእኛ ዘመን ጎልያድ ቁመቱ ስድስት ክንድ ከስንዝር መሆኑ ሳያንስ ባለሰይፍ መሆኑ ሳያንስ፣ ወንጭፉም ድንጋዩም በእጁ ነው፡፡

  • ከሕይወት እምሻው ፌስቡክ

*******

ፕሬዚዳንት አልሲሲ ቀይ ምንጣፍ በለበሰው ጎዳና በመኪናቸው ተጓዙ

የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ ኤልሲሲ በኪሎ ሜትር በሚለካውና ቀይ ምንጣፍ በለበሰው መንገድ ላይ ባለፈው ቅዳሜ (ጥር 28 ቀን 2008 ዓ.ም.) መጓዛቸው በጋዜጠኞችና በማኅበራዊ ሚዲያ አክቲቪስቶች ዘንድ መደናገጥና ቁጣን አስነሳ፡፡ ቁመቱ አራት ሺሕ ሜትር ጎኑ ደግሞ ስምንት ሜትር የሆነው ቀይ ምንጣፍ 1.6 ሚሊዮን የግብፅ ፓውንድ እንደሚያወጣም ታውቋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው፣ ቀይ ምንጣፍ በለበሰው መንገድ ላይ ፕሬዚዳንቱ የተጓዙት፣ ከካይሮ በስተደቡብ በሚገኘው ኦክቶበር ስድስት ከተማ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን መርቀው ሲከፍቱ ነው፡፡

ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ምንጣፍ ላይ በተሽከርካሪያቸው ሲጓዙና ፕሮጀክቶቹንም መርቀው ሲከፍቱ በአገሪቱ ቴሌቪዥን ታይቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለፈው ዓመት ባወጣው ሪፖርት፣ ከአጠቃላዩ የግብፅ ሕዝቦች መካከል 25 በመቶ ያህሉ ከድህነት ወለል በታች ይገኛሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ የአልሲሲ በመኪና ሆኖ በቀይ ምንጣፍ መሄድ የፖለቲካና የማኅበራዊ ድረ ገጽ አቀንቃኞችን፣ አስቆጥቷል፡፡

የሱፍ ሁሴኒ የተባሉ  ታዋቂ ሾው አቅራቢ፣ መንገዱን ቀይ ምንጣፍ ከማልበስ ይልቅ ለድሆች ለክረምት የሚሆናቸው ብርድ ልብስ መስጠት የተሻለ ነበር፡፡ መንገዱ ቀይ ምንጣፍ እንዲለብስ ፕሬዚዳንቱ አያዙም፡፡ ይህን የፈጸሙ ሰዎች መጠየቅ አለባቸው ብለዋል፡፡

*******

ለፊልም ቀረፃ የዋለ ፍንዳታ ነዋሪዎችን አስበረገገ

በማርቲን ካምፕቤል ዳይሬክት የሚደረገውንና ጃኪ ቻንና ብሮስ ናን ዋና ተዋናይ የሆኑበት ‹‹ዘ ፎሪነር›› ፊልም የቀረፃ አካል የሆነው የአውቶብስ በቦንብ መጋየት ሲከናወን በአካባቢው የነበሩት ጉዳዩን ከሽብር ጋር በማያያዝ መበርገጋቸው ተገለጸ፡፡ ቢቢሲ እንደዘገው፣ አንዳንድ የለንደን ነዋሪዎች አውቶብሱ በፊልም ቀረፃ ላይ እንደነበር አያውቁም፡፡ አውቶብሱም የላምበት ድልድይን በማቋረጥ ላይ እያለ በቦንብ ፍንዳታ ምክንያት በእሳት ይጋያል፡፡ ፍንዳታው የተከናወነው በቁጥጥር ሥር ሆኖ ቢሆንም፣ ድምፁና የእሳቱ ነበልባል በአካባቢው የነበሩትን አስደንግጧል፡፡

በአካባቢው የፊልም ቀረፃ እንደሚካሄድ፣ ነዋሪውም እንዳይደናገጥ በሚል መረጃዎች የተሰጡ ቢሆንም፣ መረጃው ያልደረሳቸውና ፍንዳታውን ከሽብር ጥቃት ጋር በማያያዝ የተደናገጡ ብዙ ነበሩ፡፡ በአካባቢ ፖሊስና የፀጥታ ኃይሎችም ወዲያው ተገኝተዋል፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች