Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ጥርቡ ድንጋይ ምን በደለ?

ትኩስ ፅሁፎች

አዲስ አበባ ለእግረኞቿም ሆነ ለተሸከርካሪዎቿ ይበጃል ብላ ከፍተኛ ወጪ አውጥታ በየአጥቢያው፣ ከባዕድ አፍ የወረሰችውንና ‹‹ኮብልስቶን›› ያለችውን ጥርብ ድንጋይ አንጥፋ ኅብረተሰቡን ስታገለግል ቆይታለች፡፡ አሁን አሁን ደግሞ እግረኛ የሚተላለፍበትን በዋና ዋና ቦታዎች ቄንጠኛ የሆኑትን የድንጋይ ንጣፎች በማምጣት መቀየርዋ የተወደደላት ቢሆንም፤ ከመሃሉ ራቅ ባሉት አውራ ጎዳናዎች የእግረኛ መመላለሻ የሆኑትን ጥርብ ድንጋዮች ገና ሩጫቸውን ሳይጨርሱ መነጋግሎ ማንሳት ምን ማለት ነው? የሚሉ ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ በፎቶዎቹ እንደሚታየው አስኮ ጨረታ አካባቢ በጥሩ ሁኔታ የሚገኙትን በግራና በቀኝ የሚገኙትን ንጣፎች መነቃቀል ምን አመጣው? ደሞም ዝናቡ በበረታበት ወቅት ድርጊቱ መፈጸሙ፣ መንገዱ በመጨቅየቱና ውሃ በማቆሩ ለእግረኛው አዳጋች ሲሆን፣ መኪናው መንገድ ላይም እንዲወጣም እያደረገው ነው፡፡ ለማፍረስ መጣደፋቸውን ያየው አንዱ መንገደኛ ‹‹እነዚህ ሰዎች ሰኔ 30 እንዳይደርስባቸው ነውኮ ሚጣደፉት›› ሲል ተሳልቋል፡፡ 

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች