ፓርላማው ማክሰኞ ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማንሳት የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ በስምንት ድምፀ ተዓቅቦ አጸደቀ፡፡
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ስለነበሩ፣ ተጣርተው ለፓርላማው እንዲቀርቡ አፈ ጉባዔዋ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል አሳስበዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ፣ ፓርላማው ምሕረትን በሚመለከት የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ ተመልክቶ ለቋሚ ኮሚቴ ዕይታ መርቷል፡፡ አዋጁ የምሕረት ቦርድ የሚያቋቁም ሲሆን፣ ተጠሪነቱም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሆን ይደነግጋል፡፡