Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትአዲሱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሚታወቅበት የሰመራው ጉባዔ

አዲሱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሚታወቅበት የሰመራው ጉባዔ

ቀን:

ከብዙ ንትርክና አተካራ በኋላ ቀጣዩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እሑድ ግንቦት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ለመምረጥ የጠቅላላ ጉባዔ አባላቱ ሰመራ ላይ ከትመዋል፡፡

በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ጣልቃ ገብነት ምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዳግመኛ ከተዋቀረ በኋላ ውዝግብ የተነሳበትን የዕጩ ውክልናን በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎችን ሲያስተናግድ ቆይቷል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሚያዝያ 27 ቀን በካፒታል ሆቴል በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የተሰየመው የፌዴሬሽኑ አስመራጭ ኮሚቴ ለፕሬዚዳንታዊና ሥራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ የሚቀርቡ ዕጩዎችን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

አስመራጭ ኮሚቴውም ግንቦት 14 ቀን ይፋ ባደረገው ዝርዝር መሠረት ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የአዲስ አበባ፣ የትግራይና፣ የጋምቤላ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች  ኢንጂነር ፀደቀ ይሁኔ፣ አቶ ተስፋዬ ካህሳይና ኢነጅነር ቾል ቤልን የወከሉ ቢሆንም፣ በተደረገው ማጣራትና ቀን ገደብ ባለመጠበቅ በሚል የጋምቤላና የአዲስ አበባ  ተወካዮች ከውድድር ውጪ ሆነዋል፡፡

ከትግራይ ክልል ውክልናቸው መነሳቱ የተገለጸው የአቶ ተስፋዬ ካህሳይ ጉዳይን በይግባኝ አጣርቻለሁ ያለው አስመራጭ ኮሚቴው በግላቸው አራተኛ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አጽንቷል፡፡

ዓርብ ግንቦት 24 ቀን ጋዜጣዊ መግለጫ የጠራው የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴው እንዳስታወቀው፣ አቶ ተሰፋዬ ካህሳይ ከስድስት ክለቦች ድጋፍ በማግኘታቸው ምርጫው ላይ ለመሳተፍ ምንም የሚያግዳቸው ነገር ባለመኖሩ በዕጩነት ቀርበዋል፡፡

ከየክልሉ የተወጣጡ 22 የሥራ አስፈጸሚ ተወዳዳሪዎችን በተመለከተ ለሦስተኛ ጊዜ የሚወዳደሩ እንዳሉ የተጠቀሰ ሲሆን፣ አስመራጭ ኮሚቴው ‹‹ሕገ ደንቡ ላይ የጊዜ ገደብ ስላልተቀመጠና ተገቢነቱ ላይ ትኩረት አለመሰጠቱ ደካማ ጎኑ ነው›› ሲል ተናግሯል፡፡

ከአቶ ተስፋዬ ካህሳይ በፊት ፕሬዚዳንታዊ  ዕጩ ሆነው አስቀድመው ግንቦት 14 ቀን የቀረቡት ከድሬዳዋ አቶ ጁነዲን ባሻ፣ ከአማራ አቶ ተካ አስፋው፣ ከኦሮሚያ አቶ ኢሳያስ ጅራ ናቸው፡፡

በሰመራ በሚካሄደው ምርጫ ላይ 145 ድምፅ ሰጪዎች ወደ ሥፍራው ያመሩ ሲሆን፣ አሸናፊው ተመራጭም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ትልቅ የቤት ሥራ እንደሚጠብቃቸው እየተነገረ ነው፡፡ በተመልካች መካከል የሚፈጠረውን ብጥብጥ፣ የብሔራዊ ቡድን ደረጃ ማሽቆልቆል፣ የአስተዳደራዊ ክፍተቶችና ፌዴሬሽኑን በፋይናንስ የማጠናከር ሥራ በቀጣይ አራት ዓመታት መፍትሔ የሚሹ ጉዳዮች ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...