Tuesday, May 21, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኢትዮ ቴሌኮም በዘጠኝ ወራት ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • የደንደበኞቹ ቁጥር ከ62 ሚሊዮን በላይ መድረሳቸውን ጠቅሷል

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ካቀረባቸው አገልግሎቶችና የምርት አማራጮች የዕቅዱን 27.79 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስገባት እንደቻለ  አስታወቀ፡፡

ኩባንያው የዘጠኝ ወራት አፈጻጸሙን በማስመልከት ለሪፖርተር በላከው መግለጫ፣ 29.95 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ለማስገባት ቢያቅድም የዕቅዱን 93 በመቶ ያሳካ ሲሆን፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ገቢው 15 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሁሉም የአገልግሎት ዓይነቶች የኩባንያው ደንበኞች ብዛት 66.2 ሚሊዮን እንደደረሰ ሲገለጽ፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አኳያ አጠቃላይ የደንበኞች ብዛት 17 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ የኩባንያው የሞባይል ደንበኞች ብዛትም 64.4 ሚሊዮን በመድረሱ፣ ከዕቅዱ የ97 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ እንዳስቻለው ጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል የኢንተርኔትና ዳታ ተጠቃሚዎች ቁጥር 16 ሚሊዮን እንደረሰ በማስታወቅ ከዕቅዱ 77 በመቶውን እንዳሳካ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡ የመደበኛ ስልክ ደንበኞች ቁጥር 1.2 ሚሊዮን ስለመድረሱም ኩባንያው በመግለጫው አጣቅሷል፡፡

ይህ በመሆኑም ከሞባይል አገልግሎት ያገኘው ገቢ ከአጠቃላይ ገቢው 75.3 በመቶውን ሲሸፍን፣ ዳታና ኢንተርኔት 17.1 በመቶ እንዲሁም ዓለም አቀፍ አገልግሎት 5.2 በመቶ ድርሻ ይይዛሉ፡፡ የኩባንያው ያልተጣራ የትርፍ መጠን (ከታክስና ሌሎች ተቀናሾች በፊት የተገኘ ጥቅል ገቢ) 19.6 ቢሊዮን ብር እንደሚሆን ይጠበቅ ነበር፡፡ ሆኖም በአፈጻጸሙ 19.8 ቢሊዮን ብር ጥቅል ገቢ ከታክስና ሌሎች ተቀናሾች በፊት በማግኘቱ የዕቅዱን 102 በመቶ ለማከናወን እንደቻለ ኩባንያው አስታውቋል፡፡

ዘጠኝ ወራት ውስጥ ካከናወናቸው ተግባራት ውስጥ አዳዲስ ምርትና አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች ማድረስ ሲሆን፣ 26 አዳዲስ አገልግሎቶችን ለማቅረብ አቅዶ 19 አዳዲስ ምርትና አገልግሎቶችን ለገበያ አቅርቧል፡፡ በዚህም የ73 በመቶ አፈጻጸም እንዳስመዘገበ አስታውቋል፡ ለገበያ የቀረቡት ምርትና አገልግሎቶችም ኢትዮልፍ ኬር፣ ዳታ ካልኩሌተር፣ የመደበኛ ስልክ ጥቅል፣ ሀይብሪድ ሲም አካውንት፣ የማሽን ማሽን አገልግሎት፣ ኦልተርኔቲቭ ቻናል፣ የሞባይል የድምፅ ጥቅልና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

ከባድ ፈተና ሆነውብኛል ካላቸው ችግሮች ውስጥ የቴሌኮም ማጭበርበር ዓለም አቀፍ የድምፅ ጥሪዎችን በመቀነስ የሚካሄዱ ሕገወጥ ተግባራት በኩባንያው ገቢ ላይ  ተፅዕኖ ከማሳደራቸውም ባሻገር፣ ደንበኞችም ለተለያዩ የማጭበርበር ድርጊቶች መጋለጣቸውን አስታውቋል፡፡ ከኬብሎች መቆረጥ አንፃር ከተለያዩ ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በፋይበርና በኮፐር ኬብሎች ላይ የሚደርሰው ተደጋጋሚ አደጋመሠረተ ልማቱን ለአደጋ የሚያጋልጥ ተግባርም ለኩባንያው ራስ ምታት ሆኖበታል፡፡ 

በሌላ በኩል የኢንተርኔት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የግል ኩባንያዎች እንዲገቡበት በማድረግ ረገድ ከዘጠኝ ኩባንያዎች ጋር በመፈራረም፣ በኢትዮ ቴሌኮም ዋናው የዳታ ማዕከልና የፋይበር ኬብል መስመር አማካይነት እየተጠቀሙ ከሚሠሩ ኩባንያዎች ጋር ገበያውን የመጋራት ሥራ ለመጀመር መዘጋጀቱ መዘገቡ  ይታወሳል፡፡ በዚህም የመጀመሪያው በመሆን ጂቱጂ ክላሪቲ አይቲ ሶሉሽንስ የተባለ የአክሲዮን ኩባንያ አገልግሎቱን ለመጀመር መዘጋጀቱን ማስታወቁም አይዘነጋም፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች