Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናክልሎች በግል ባለቤትነት በተያዙ ንብረቶች ላይ የገቢ ግብር እንዲጥሉ ተወሰነላቸው

ክልሎች በግል ባለቤትነት በተያዙ ንብረቶች ላይ የገቢ ግብር እንዲጥሉ ተወሰነላቸው

ቀን:

  • ፍትሐዊ የልማት አውታሮች ሥርጭትን እንዲጠብቅ ለመንግሥት ማሳሰቢያ ተሰጠ

ክልሎች በግል ባለቤትነት በተያዙ ንብረቶች ላይ የገቢ ግብር እንዲጥሉ፣ ገቢውም የክልሎች እንዲሆን በመንግሥት መወሰኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የምክር ቤቱ የጋራ ገቢዎች ድልድል ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሚያዝያ 21 እና 22 ቀን 2010 ዓ.ም. መደበኛ ጉባዔውን ላካሄደው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባቀረበው የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንዳስታወቀው፣ በግል ባለቤትነት ሥር ካሉ ንብረቶች በሚገኝ ገቢ ላይ የፌዴራል መንግሥት ግብር በመጣል ገቢውን ለራሱ መሰብሰቡ ከሕገ መንግሥቱ የሚቃረን በመሆኑ፣ ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ ገቢውን የመጣልና የመሰብሰብ ሥልጣን ለክልሎች እንዲሆን በመንግሥት ደረጃ መወሰኑን አመልክቷል፡፡

በዚህ የገቢ ዓይነት ላይ የኦሮሚያ ክልል የይገባኛል ጥያቄ በማንሳት የፌዴሬሽን ምክር ቤትን መጠየቁን ቋሚ ኮሚቴው በማስታወስ፣ ሌሎች ክልሎችም በተለያዩ መድረኮች ጥያቄውን ሲያነሱ እንደነበር ገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዚህ መሠረት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጋር በመነጋገር ጥያቄው ተገቢ መሆኑ ላይ የጋራ መግባባት መደረሱን፣ ስለዚህም ማስተካከያ ተደርጎ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የተጠቀሰውን የገቢ ዓይነት የመሰብሰብና የገቢው ባለቤትም ክልሎች እንዲሆኑ ውሳኔ እንደተሰጠበት በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ክልሎች በአስተዳደር ወሰናቸው ውስጥ በግል ባለቤትነት ሥር ካሉ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር የመጣልና የመሰብሰብ፣ እንዲሁም በባለቤትነታቸው ሥር ባሉ ቤቶችና ሌሎች ንብረቶች ላይ ኪራይ ያስከፍላሉ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በሪፖርቱ ካነሳቸው የፌዴራልና የክልሎች የጋራ ገቢዎች ድልድል በተጨማሪ፣ ፌዴራል መንግሥት በክልሎች የሚገነባቸው የልማት አውታሮች ሥርጭትና ፍትሐዊነት ትልቅ ትኩረትን የሳበ ነበር፡፡

ቋሚ ኮሚቴው እንዳመለከተው በአራት ዘርፎች ማለትም በቴሌኮሙዩኒኬሽን፣ በኤሌክትሪክ፣ በመንገድና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሥርጭት የተገኙት መረጃዎች ፍትሐዊነቱን ለመገምገም የሚያስችሉና ጉድለት ያለባቸው ናቸው፡፡

በአስፈጻሚ አካላት ዘንድ የልማት አውታሮች ሥርጭት ፍትሐዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ግልጽና ተጨባጭ የሆኑ የክፍፍል መሥፈርቶችን በመቅረፅ ተግባራዊ ማድረግ ላይ የውስንነት ችግር አንዱ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

አንዳንዶቹ አስፈጻሚ ተቋማት በልማት አውታሮች ዝርጋታ ሒደት የክልሎችን ድርሻ ለመወሰን መሥፈርቶቹ እንዴት ጥቅም ላይ እንደዋሉ በግልጽ አያመለክቱም፡፡ አንዳንዶቹ ግልጽና ተጨባጭ መስፈርት የላቸውም ሲል ኮሚቴው ሪፖርት አድርጓል፡፡

በመሆኑም የልማት አውታሮቹ ክልላዊ ሥርጭት የሚደለደልበት ግልጽና ተጨባጭ መሥፈርት በማዘጋጀት፣ የፌዴራል መንግሥት ተቋማት እንዲተገብሩ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በማሳሰብ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የራሱን የክትትል ሥርዓት ቀርፆ ፍትሐዊነቱን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...